@admaelpray7: ፨ ተዓምረኛው ስእለ አድኅኖ፨ አንድ ቀን ማታ አምሽቼ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄድኩኝ የቤተክርቲያኑ በር ክፍት ነበር:: ወደ ውስጥም ዘልቄ ገባሁ። የጌታየ እናት የቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ሲያለቅስ አየሁት ተጠጋሁ፤ እንባዋን በጥጥ አበስኩት ነገር ግን ከእንደገና እምባ ያወጣል፤ለሶስት ጊዜ ደጋግሜ እንዲሁ አደረኩ አሁንም መልሶ እንባ ያወጣል፤ ይገርማል በሶስተኛው ግን በጉልበቴ ወድቄ ከስእሉ ፊት ተደፍቼ የጌታየ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ይቅር ትለኝ ዘንድ ተማፀንኩ:: የለመንኩትም ተፈፀመልኝ ። ከዚህ በኋላ በዚህ ደብር ብዙ ፈውስ ተደረገ። በሀገራችን በቡልጋሪያ ፤ አሁን የ18 ዓመት እድሜ የሆነው ወጣት ኢቫን (Ivan), ከሁለት ዓመት በፊት አደገኛ የሆድ ዕጢ በሆዱ ውስጥ ነበረበት:: የኢቫን እናት ይህን የድንግልን ተዓምር ሰምታ ወደ ቤተመቅደስ ይዛው መጣች፣ ለእኔ ሰጠችኝ: እኔም ልጁን በክንዴ አስደግፌ ለጥቂት ቀናት ያህል ከዚህ ተዓምረኛ የድንግል ስዕል ፊት ቆየሁ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ልጁን ወደ ምርመራ ክፍል ወሰድነው፣ ዶክተሩም መረመረው፣ በሆዱም ውስጥ የዕጢው ጠባሳ ብቻ ተገኘ። እውነት እውነት እላቹሃለሁ እስከዚህ ሰዓት ድረስ ይህ የድንግል ማርያም የምሕረት እንባ ህዝባችንን እየፈወሰ ይገኛል!!! ክብር ለወላዲተ አምላክ ለቅድስተ ቅድሳን ድንግል ማርያም ይሁን ! አመስግኑልኝ ለስሟ ዘምሩልኝ ! ከማህበራዊ ትስስር የተዋስንው

ቤዕንተ ቅዱሳን የአበው የጸሎት  ማህበር 7
ቤዕንተ ቅዱሳን የአበው የጸሎት ማህበር 7
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 03 November 2025 12:40:26 GMT
1618
175
0
17

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @admaelpray7, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About