@clgjcn: Nissan N6, ¡el sedán híbrido enchufable inteligente y supercómodo! Autonomía EXTRA Larga: 180 km de autonomía totalmente eléctrica (CLTC). ¡Perfecto para tu semana de trabajo! Consumo con baja batería de sólo 2.79L/100km。 Hogar sobre ruedas: Sistema anti-mareo inteligente pionero en la industria. Asientos tipo "sofá" "Zero Pressure Cloud Carpet", con doble certificación de confort。 Rendimiento y espacio: Acelera de 0 a 100 km/h en 6.8 segundos. Dimensiones de Segmento B, espacio de Segmento C: Distancia entre ejes de 2815 mm, con amplio espacio trasero。 Tecnología inteligente: Versiones altas con pantalla central de 15.6 pulgadas y chip Qualcomm 8775. Asistencia de conducción Nivel L2 de serie en toda la gama。#NissanN6 #HíbridoEnchufable #CocheFamiliar #GranRelaciónCalidadPrecio

CL Internacional
CL Internacional
Open In TikTok:
Region: US
Sunday 30 November 2025 09:02:08 GMT
10021
57
1
64

Music

Download

Comments

user7234515413463
☠ᗷřǿᏦ廾☠ⓟⒾⓇⒶⓉⒺ₆₇ :
🥰
2025-12-29 03:02:04
0
To see more videos from user @clgjcn, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

'ልረሳሽ አልቻልኩም'🤕💔 ✍️ያልተነገረው አሳዛኙ ታሪክ....! ከናዝሬት እስከ አዲስ አበባ የዘለቀው የድምፃዊ ኤርሚያስ አስፋው የሙዚቃና የፍቅር ታሪክ !       ✨በባይተዋር ተጀምሮ በባዶ የተቋጨ ህይወት ። ተስፋ እየሰጠች በዚያ ውስጥ ፍንጥቅጣቂ ተስፋዎች መጥተው ድንገት ደግሞ ክስም ያለች ህይወት ። ድምፃዊ ኤርሚያስ አስፋው ትውልድና እድገቱ ናዝሬት ሲሆን፤ በልጅነቱ በቤተክርስቲያን ታንፆ ነው ያደገው - ዲያቆን ነበር ። ከልጅነቱ ጀምሮ ለሙዚቃ ቦታ እንዳለው ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ህያው መስክር ነን ይሉናል ። ሙዚቃን ከአፍላ እድሜው አንስቶ እያንጎራጎረ አደገ ፥ ጥላሁን ገሠሠ፣ ሙሉቀን መለሰ፣ መሃሙድ አህመድ...የእሱ ሮል-ሞዴሎቹ ናቸው ። ኤርሚያስ ልጅ ሳለ
'ልረሳሽ አልቻልኩም'🤕💔 ✍️ያልተነገረው አሳዛኙ ታሪክ....! ከናዝሬት እስከ አዲስ አበባ የዘለቀው የድምፃዊ ኤርሚያስ አስፋው የሙዚቃና የፍቅር ታሪክ ! ✨በባይተዋር ተጀምሮ በባዶ የተቋጨ ህይወት ። ተስፋ እየሰጠች በዚያ ውስጥ ፍንጥቅጣቂ ተስፋዎች መጥተው ድንገት ደግሞ ክስም ያለች ህይወት ። ድምፃዊ ኤርሚያስ አስፋው ትውልድና እድገቱ ናዝሬት ሲሆን፤ በልጅነቱ በቤተክርስቲያን ታንፆ ነው ያደገው - ዲያቆን ነበር ። ከልጅነቱ ጀምሮ ለሙዚቃ ቦታ እንዳለው ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ህያው መስክር ነን ይሉናል ። ሙዚቃን ከአፍላ እድሜው አንስቶ እያንጎራጎረ አደገ ፥ ጥላሁን ገሠሠ፣ ሙሉቀን መለሰ፣ መሃሙድ አህመድ...የእሱ ሮል-ሞዴሎቹ ናቸው ። ኤርሚያስ ልጅ ሳለ "ወደፊት ታዋቂ ዘፋኝ እሆናለሁ..." እያለ ለጓደኞቹ፣ ለአከባቢው የቅርብ ሰዎቹ ይነግራቸው ነበር ። ቤተሰቦቹ አቅመ-ደካማ በመሆናቸው "ነገ ዘፈን በምን ገንዘብ እሰራለሁ..." ብሎ ኤርሚ ይጨነቅ ነበር፤ ድምፁን የሚሰሙት ጓደኞቹ ግን ዘወትር ነገ ትልቅ ደረጃ እንደሚደርስ ያበረታቱት ነበር ። ኤርሚያስ በአንድ ወቅት አንድ በጣም የሚወዳት ልጅ ነበረች፤ እሷም እንደዚያ ትወደው ነበር ፥ ከልጅነት እስከ እውቀት ከዚያ እስከ ጉልምስና እድሜ የዘለቀው የእነ ኤርሚያስ ፍቅር ግን በሆነ ጊዜ ላይ እንደ አበባ ከስሞ እረገፈ ፥ ለተመልካቹ ይገርማል ፥ አይጠፋም ያሉት ኩራዝ ድንገት ንፋስ መጥቶ አጠፋው ፥ ኤርሚ ስብራት ውስጥ ገባ ፥ ያሳዝናል ። እሷ "እድሜ ገፋ፤ አንጋባም ወይ ?..." ትለዋለች ፥ እሱ "በቅርቡ ዘፈን አውጥቼ ከዚያም ነገሮች ሲስተካከሉ እንጋባለን" ይላታል ። ፍቅሩ፡ የሚላት ሁሉ ቅዠት መስሎ ታያት ፥ በእሱ ላይ ያላት ተስፋ ቀን ከቀን ተስፋዋን እየተሟጠጠ ይጓዝ ጀመር ። እናም እሷ ሁሉን አሰበችና አንዳች ወሰነች ለልቧ አማከረቸው፤ ወሰነች "በቃ ሌላ እድል ከመጣ አላሳልፍም..." ያለች ይመስላል ፥ በዚያው ወቅት ሌላ ሰው በድንገት አገባች ። ያቺ ቀን ለኤርሚያስ ከባድ የልብ ስብራት ውስጥ ሰነቀረው፤ ህመሙን ችሎ፣ ትዝታውን ፍቆ ለማጥፋት ሞከረ ፥ ከበደው፤ እንደምንም ቻለው ፥ ያ ሰዎችን ሱስ ውስጥ እንዳይገቡ የሚመክረው፣ የሚዘክረው ሰው እሱም አንድ ሁለት እያለ ዘለቀበት...። ኤርሚ መጠጥ መጠጣት ጀመረ...። 🥺 ጊዜው ፍቅሩን ከነጠቀው “ጊዜ” ብዙም አልራቀም ፥ በሰዎች አማካኝነት አንድ የሚዚቃ ፕሮዲሰር ያገኛል።(የበርካታ የናዝሬት ልጆችን ሙዚቃ የሰራውን ባለድንቅ ተስጦውን ጂግሳ ታደሰ) ያኔ ኤርሚ በለዘበው ደስታ፤ ህልሙ እውን የሆነ መሰለው፣ ልቡ በሀሴት ፈነጠዘች...። እናም ወደ አዲስ አበባ በመሄድ የሙዚቃ ስራዎችን - በሰዎች እገዛ፤ መጀመሪያ የሪሚክስ ስራዎችን ጀመረ፤ የጥላሁን ገሠሠ “ድማም" እና ሌሎችንም... ዘፈኖች ሪሚክስ ሰራ ፥ የኤርሚ አቅም የዋዛ አልነበረም፤ ድንቅ ነበር ። ለጥቆም፤ የአልበም ስራ ጀመረ ። አስር ትራክ ያለው አልበም “ልረሳሽ አልቻልኩም” አልበምን ሰርቶ ጨረሰ ፥ በዚህ አልበም ከልቡ አሟጦ ሊተፋት ፍፁም ያልቻለው ያቺ ለፍቅር ውቅያኖሱ፤ በድንቅ ብዕሩ ጽፎላት፣ ዜማ ቀምሮላታል፤ የስሙም መጠሪያም እንድትሆን፤ የአልበሙ መጠሪያ አደረጋት “ልረሳሽ አልችልም ?” አላት፤ መልሱም "በምንም አልተካሽ" ያላት ይመስላል ፥ እሷ ግን ላትመጣ ሄዳለች ። ታዲያ ይህ አልበም ሰርቶ ከወጣ በኋላ ኤርሚ ህልሙ በአንድ በኩል ሊቃና የመሰለው፤ ያላሰበው ቅስም ሰበሪ ነገር ደገመው ፥ ህይወት እስከወዲያኛው ለኤርሚ ዘመመች፣ ጠመመች ። የአልበሙ ካሴት ምንም ሊደመጥ አልቻለም ፥ እሱም የመጨረሻ ተስፋ ቆረጠ ኤርሚ የተባባሰ ሱስ ውስጥ ተዘፈቀ ፥ ተስፋው እስከወዲያኛው ጨለመበት ። ካሴቱን ሰብስቦ ሽንት ቤት ከተታቸው ። ቀን ቀንን ሲተካ፤ የሱም ሱስ እያየለ መጣ ። በመጨረሻም ኤርሚ በመጠጥ የተነሳ የደም ቱቦ መጥበብ ይዞት እስከ ዘላለም አሸለበ ፥ ይነጋል ያሉት ቀን እንደጨለመ ሲቀር፣ ይሆናል ያሉት ሁሉ ሳይሆን ሲቀር ። ለፍቶ፣ ታክቶ፣ ዳክሮ ፥ ሳያልፍልህ ማለፍን የሚያህል ህመምና ስብራታ የለም ! ። “ልርሳሽ አልቻልኩም ?” አልበሙ ከመውጣቱ በፊት የተለቀቀው ነጣላ ዜማው “ልረሳሽ አልቻልኩም” ነበር እንደተለቀቀ በሬዲዮና በተለያዩ አማራጮች ተወዶ ተደመጠለት ፥ ህይወቱ ካለፈ በኋላ ከአልበሙ ውስጥ “ልረሳሽ አልቻልኩም ?” የተሰኘችው ሙዚቃው እጅግ ተወዳጅነቱ ጨመረ ። “...ልቤን ከፍቅሬ ጋር እኔው ልኬልሽ ትዝታን አማጥኩልሽ (2x).... ትዝታሽ ነካክቶኝ ፍቅሬ ተቀስቅሶ መብሰክሰክ መንደዴን ማን ባየልኝ ደርሶ ። (2x) ተጫዋችነት ፈገግታዬ ጠፍቶ ባይተዋርነት ትካዜ በዝቶ ።...” ◉ ድምፃዊ ኤርሚያስ አስፋው ለሰራሃቸው ስራዎች ሁሉ ሁሌም ስትዘከር ትኖራለህ ፥ ነፍስ ይማር ! 💔🙏 ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 musictube 🇪🇹 #fyp #ኤርሚያስአስፋው #ልረሳሽአልቻልኩም #musictube369 #ethiopianmusic

About