@musictube369: 'ወኪል ነሽ'🤍🫶 ✨ሙዚቃው ቅን አሳቢ ከክፋት አዳኝ በቀላል ፊደላት ከባድ መልዕክት የተሸከሙ ናቸው እስከዛሬ ድረስ እንደ ወይን እየጣፈጡ የሚደመጡ ሙዚቃዎች ናቸው ፡፡ የሮክ እንዲሁም በዛ ያሉ የሬጌ ሙዚቃ ስልት አቀንቃኝ ፎቶግራፈር እዮብ መኮንን ዘውዴ …💔🥺 ✨ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ በጅጅጋ ከተማ ጭንግሰን ገብኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከ እናቱ አማረች ተፈራ ከ አባቱ መኮንን ዘውዴ ወደ ዓለም ብቅ የለውን ፡፡ የሬጌ የሙዚቃ ስልት አቀንቃኝ እዮብ መኮንን ዘውዴን ዛሬ ከብዙ በጥቂቱ እናወሳዋለን🙏 እዮብ መኮንን ትምህርቱን አንድ እና ሁለተኛ ደረጃ የተከታተለው በትውልድ ስፍራው ጅግጅጋ ከተማ ሲሆን በተጨማሪም ወደ አስመራ በማቅናት ትምህርቱን ተከታትሏል ፡፡ በልጅነቱ ሙዚቃ ይሰማል እንደውም ወደ ሙዚቃ አለም እንድገባ ከ ገፋፉኝ መሀል አንዱ አሊ ቢራ ነው ሌላኛው ጀማይካዊ ቦብ ማርሊ ይላል በይበልጥም ይሰማ ነበር ፡፡ 1991 አመተ ምህረት የሚኖርበት ጅግጅጋ ከተማ ወቶ ወደ ዋናይቱ  ከተማ አዲስ አበባ መጣ የነፍስ ጥሪ  ሙዚቃ ስለ ነበረች ብዙም ሳይቆይ ከ አንድ አመት በኃላ ማለትም 1992 አመተ ምህረት መድረክ ላይ ቀርቦ ያቀርባል/ሙዚቃን በአደባባይ/ ከዛም  ''ፋልኮን ክለብም በመቀላቀል ከ 1992-1997 አገለገለ ፡፡ ሙዚቃን በተረዳት መጠን ሙዚቃን ባወቃት ልክ ደግ እና ጤነኛ ሐሳብ ይዞ እስከ ዛሬ ድረስ አድምጠው የማይሰለቸኝ እንደ እናት አባታች የማንረሳው አልበም በ2000 አመተምህረት ''እንደ ቃል '' የመጀመርያ አልበም አደረሰን ፡፡ እንደ ቃል አልበም ነፍሱን ይማረውና በታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ኤልያስ መልካ 💔 ግጥም ዜማ አክሎበት እውነተኛ ታሪክ ያዘለ ሃቅ እና ገሀዱን ዓለም አንፀባራቂ አልበም ይዘው መጡ … እዮብ መኮንን በአንድ ወቅት ከጉራማይሌ ቲቪ ጋር ስለ እዚህ አልበም ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት እንዲህ ብሎ ነበር ''ሙዚቃው ለሰባት (7) ወር ያህል ፀጥ አለ መኪናዬን እየነዳው እየሄድኩ በረጅሙ በኪሎ ሜትር አልሰማሁትም ከዛ( 3)  ኪሎ ሜትር ተጓዝኩ ሰማሁት ከዛ ጋፑ እየጠበበ እየጠበበ መጣ'' ይህ አልበም ተስፋን አፈንጣቂ ፣ ፍቅርን ሰባኪ ፣ አስተማሪ ፣ እውነተኛ ገፅን ፣ በቀና መንገድ የተሞሸረ ነው ፡፡ ነቅቻለሁ ፣ ነገን ላየው ፣  ደብዝዘሽ ፣ ይዘባርቃሉ ፣ ማን እንደ ቃል ተጠቃሽ ናቸው ፡፡ ነቅቻለሁ ላይ… መቼ ተሞኘ ብልህ ነው ፍቅር ክብሩን አይጥልም ከውሸት መንደር ከ ቅብዝብዝ ጋር መች ይረጋጋል አይታለልም ሸንጋዩን ያውቃል … የፍቅርን ሐያልነት  መንቃት ከፍቅር ጋር ነው … ይቅር ባይነትን በሌላው ሙዚቃ 'እንዳጠፋሽ' ሲነግረን እንዳጠፋሽ አጥፍቻለሁ እንደ ሸፈትሽ ሸፍቻለሁ ያለ ፅድቄ ያለ ፍርድ ቆሜለሁ … በነበረኝ ሌላ አጥያት ፣ ሌላ እድፍ እራሴው ጋር ጨመርኩኝ ይቅር በይኝ …ይላል በመቀጠል የኤልያስ መልካ እውነተኛ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው አንዱ ''ደብዝዘሽ" ነው ድብቅ ውበትን ገልጦ ይናገራል ስለ ጨዋ ሴት ትክ ብሎ ላያት የምትታይ ድንቅ ሴት ፡፡ ዝምታሽ በለጣቸው ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው… አስተማሪው ይዘባርቃሉ ስለ አንተ ሳያጤኑ ሳይገባቸው ለሚዘባርቁ እና ገብቶቸው ልክነትህን የሚዘባርቁትን በሁለቱ ነገሮች ለማስታረቅ አስተማሪ እውነታዊ ስለ ሆነ አንቺ ሰማሽ የመጡትን ሲያወሩ ማያውቁትን ከረበሸሽ አስረጃቸው ንቀሽ ካልተውሻቸው … እዮብ መኮንን በዚህ አላበቃም ሁለተኛ አልበሙን ይዞ እያስገረመን በነገራችን ላይ ከአልበሙ ዉጪ ከ ዘፈናቸው /መላ መላ/ ከነ ፀደንያ ገብረ ማርቆስ ፣ ዘሪቱ ከበደ ፣ ሚኒልክ ወስናቸው ፣ የመሳሰሉት ጋር እንዲሁም ከ አይሌ ሩት ጋር /በየመሀሉን / አብረው ሰርተዋል ፣ የፍቅር አኩኩሉን እያለ በሁለተኛ አልበሙ አስደመመን  በቅንብር ዳግማዊ አሊ ፣ ካሙዙ ካሳ በግጥም ቃሲም ሙሀዓዲን እራሱ እዮብ መኮንን የተሳተፈበት እሮጣለሁ አልበም በዘመን ውስጥ የሚሻገር የማይሸፋፈን ግልፅ የሆነ እውነታው በግጥሞቹ ይፀባረቃሉ እሮጣለሁ፣ የጋበዝኳቸው፣ ወሀጂራ ወል አለይ ፣ ወደ እናቴ ቤት እንደ ምሳሌ እንያቸው  … ይለፍ የተሰኘ ሙዚቃው ሰዎች ክፉ ነገር ሲፈፅሙ ይለፍ የሚያናድድ ነገር የሚያበሳጭ ሲመጣ ይለፍ እያለ እያረጋጋህ የሚናገር ነው ፍቅር ተው ለልቤ ስንቅ ሁንለት የተስፋ መንገዱ ይስመር ይቅናለት ይለፍ ሰምቶ እንዳልሰማ አይቶ እንዳላየ ክፉ እና ደጉን አውቆ እየለየ ድንገቴ ፍቅር ሳታውቅ ግን የማይመስል ነገር የሚሆንበት የጋበዝኳቸው … ከጥሪው መዝገብ ስምሽ ሳይሰፍር በሌሎች ግብዣ አመጣሽ ፍቅር አክባሪ ያጣው ደጋሽ የልፍኜ ያልታለምሽውን አንችን አገኘ የኔ ያልከው ሰው ቀርቶ የማያውቅህ ሰው ከ ምታውቀው በላይ ሆኖ ሲንከባከብህ በሌሎች ግብዣ እሱ ይገግሳል ማለት ነው … እዮብ እኝህን ውድ ስጦታ ሰቶን ወደ ማይቀረው ሞት በድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በነሀሴ13/2005 አመተ ምህረት በኬንያ ናይሮቢ ህክምና ሲደረግለት ቆይቶ ህይወቱ አልፏል🥺 ከኬንያ ወደ አዲስ አበባ አስክሬኑ ሲመጣ 14 /2005 ግብአተ መሬቱ ተፈፅሟል ፡፡ ግን ዘመን የማይሽራቸው ሙዚቃ ስለ ሰጠን ሞተ ብሎ ለማሰብ ይከብዳል ሁለተኛ አልበሙ ላይ እንዳቀነቀነው…😥 ለሙት ሙት ሆኜለት መች እቀመጣለሁ… የመኖርም ፈተና ምንም ቢያንገዳግድ አታካችም ቢሆን መውጣት እና መውረድ ነፍሴን ልታደጋት ሕይወቴን ዘክሬ ሞቴም ትንሳኤ ነው በሕያው መኖሬ … "እኔስ ላልቀር ማለፌ ነበረን አትርፌ ለመሞት አልኖርም ለመኖር ነው ሞቴ"... ነፍስህ በሰላም ትረፍ🤍💐 @Musictube ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 #fyp #እዮብመኮንን #ወኪልነሽ #musictube369 #ethiopianmusic

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱️🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱️🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 04 December 2025 21:49:10 GMT
170717
15598
80
1413

Music

Download

Comments

abelmewded6
Gomez :
Underrated music 🙆 eyob is a king
2025-12-04 21:57:46
107
tewodros183
Tewodros183tedy :
ይሄ አልበም 2000አይደል የወጣው ሀብትሽ?
2025-12-05 14:20:23
31
binu.wolde
Binu Wolde :
ኤልያስ መልካ 🙌🙌
2025-12-05 04:50:16
32
call_me_addis
𝗖𝗔𝗟𝗟 𝗠𝗘 🔱𝗔𝗗𝗗𝗜𝗦 🔥 :
የሞተ የማይመስለኝ ሰው 😔
2025-12-13 17:09:40
14
7kbingo2
maf Andi :
ክብር ለሬጌው ንጉስ 🙏🙏
2025-12-05 19:03:15
9
some_1_idk3
Call_me_ጮርናቄ :
እዮብ መኮንን ያለም ነው ዘዉዴ አይመስለኝም
2025-12-05 10:37:25
4
chichi.fana
chichi fana :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰iconic musician
2025-12-04 22:31:10
5
imenn01
aymen_hd💊🧊🐥 :
2000
2026-01-09 18:09:16
2
mulle22addis
Mulle Addis :
eyoba 🥰
2025-12-05 00:11:36
7
user6272467797332
abdii :
king of king
2025-12-05 19:15:53
2
natid.marly
Nati D. Marly :
The one & only yoba......Rest in power 🙏🙏
2025-12-06 18:12:48
1
natanestifanos
Natan Estifanos ኤልያስ መልካ :
Elu
2025-12-14 20:45:33
1
selemonsisayi
selemon :
ኤላዬ
2025-12-05 17:19:35
3
sur.rkid4
sur. r :
ከአሁን በኋላ ሌላ ...👍
2025-12-06 17:53:53
0
henok.581787878571
Henok :
እዮባዬ 🥺🔥
2025-12-19 20:24:30
1
yabu1067
yab :
yesi🎧 eyoba
2025-12-04 22:06:26
2
azriel_meme
Azriel🗿 :
Eyoba 🖤👑
2025-12-23 13:43:42
1
amiko8081
Amanuel Tsehaye :
eyoba the king
2025-12-05 20:28:11
1
user4283617336750
ONE LOVE ❤ :
eyobaye🥰🥰🥰
2025-12-20 16:57:56
0
bekikuk5
@Bekikuk(TBH)™️🚨 :
አንደኛ ነህ ለኔ እዮባ🙏
2025-12-14 04:06:11
0
tt754595
መሲ🌸 :
ወኪል ነሽ❤️
2026-02-13 19:19:23
0
67ofunny
one 🕜 day :
eyobe 🙏 ♥️
2025-12-21 12:29:48
0
sumeya_94
Sumayyah👻🌸 :
ወኪል ነሽ 🎶❤
2025-12-06 07:51:37
1
iisaac_v8
ይስሐቅ❄️ :
ከኔ በላይ ነው ገባኝ
2026-01-30 19:22:22
0
samra_1216
Samrawit✨ :
@🥀𝓶𝓮𝓵𝓾𝓾🥋🌹 🥰
2026-01-11 00:00:25
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About