@ri_.yna:

'♡Reina🤍👑
'♡Reina🤍👑
Open In TikTok:
Region: TR
Thursday 11 December 2025 22:46:50 GMT
30444
684
1
228

Music

Download

Comments

nachida.guergour
Nachida Guergour :
🥺🥺🥺
2026-07-30 00:59:54
0
To see more videos from user @ri_.yna, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ዐይነስውሩ ባለማሾ ክረምት አይደል ተረት ብናወራ ምን ይለናል?  ከእኛ ቢያልፍ ለልጆቻችን ይተርፋቸዋል! ተረት ተረት ከዕለታት አንድ ቀን በአንዲት ትንሽ ከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ ዐይነስውር ነበረ። ይህ ዐይነስውር ሰው ማዬት የማይችል ቢሆንም ሁሌም ግን ሲመሽ በሚሄደበት ቦታ ሁሉ ማሾ አብርቶ ይሄድ ነበር። አንድ ቀን ምሽት ላይ ራቱን ከቤት ውጭ በልቶ ማሾውን አብርቶ ወደቤቱ ሲጎዝ፤ በመንገዱ ላይ ከገጠሙት በእሱ አቅጣጫ ከሚሄዱ ወጣት መንገደኞች ጋር ተቀላቅሎ መንገዱን ይቀጥላል።  ወጣቶቹ በአጠገባቸው የነበረው ተጓዥ ሰው ዐይነስውር ሆኖ ሳለ ማሾ ተሸክሞ በመሄዱ እየተንሾካሾኩ ሲያላግጡበትና የመሰላቸውን ሃሳብ እየሰነዘሩ ሲጓዙ ከመካከላቸው አንዱ ዐይነስውሩን ጠጋ ብሎ በድፍረት፤
ዐይነስውሩ ባለማሾ ክረምት አይደል ተረት ብናወራ ምን ይለናል? ከእኛ ቢያልፍ ለልጆቻችን ይተርፋቸዋል! ተረት ተረት ከዕለታት አንድ ቀን በአንዲት ትንሽ ከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ ዐይነስውር ነበረ። ይህ ዐይነስውር ሰው ማዬት የማይችል ቢሆንም ሁሌም ግን ሲመሽ በሚሄደበት ቦታ ሁሉ ማሾ አብርቶ ይሄድ ነበር። አንድ ቀን ምሽት ላይ ራቱን ከቤት ውጭ በልቶ ማሾውን አብርቶ ወደቤቱ ሲጎዝ፤ በመንገዱ ላይ ከገጠሙት በእሱ አቅጣጫ ከሚሄዱ ወጣት መንገደኞች ጋር ተቀላቅሎ መንገዱን ይቀጥላል። ወጣቶቹ በአጠገባቸው የነበረው ተጓዥ ሰው ዐይነስውር ሆኖ ሳለ ማሾ ተሸክሞ በመሄዱ እየተንሾካሾኩ ሲያላግጡበትና የመሰላቸውን ሃሳብ እየሰነዘሩ ሲጓዙ ከመካከላቸው አንዱ ዐይነስውሩን ጠጋ ብሎ በድፍረት፤ "ስማ የእኔ ወንድም…አንተ ምንም ነገር ማየት የማትችል ዐይነስውር ነህ፤ ነገር ግን ማሾ አብርተህ ትሄዳለህ? ላታይበት ምን አሸከመህ? ምንስ ይጠቅምሃል?" አለው። ዐይነስውሩም ድምፁን ወደሰማበት አቅጣጫ ዞር ብሎ፤ "ልክ ነህ ወዳጄ….እርግጥ ነው እኔ ዐይኔ ምንም ነገር ማዬት የማያስችለኝ ዐይነስውር ነኝ…..ነገር ግን ይህንን ማሾ የያዝኩት ለእኔ ለዐይነስውሩ ሳይሆን ገፍታችሁ ጉዳት እንዳታደርሱብኝ ለእናንተ ለዐይናማወቹ መንገድ ለማሳየት ነው" በማለት መለሰለት። ይህንን የሰሙት ተጓዦች በዐይነስውሩ ምላሽ እጅግ ተደንቀው ስለሰጡት ያልተገባ ሃሳብ ይቅርታ ጠየቁት ይባላል። ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ! የተረቱ አብነት  ምንጊዜም በሌሎች ላይ ቸኩሎ ከመፍረድ መቆጠብ ሁዋላ ከሚመጣ ፀፀት የሚታደገን መሆኑን ይነግረናል። ስለዚህ ሁሌም ትሁት ሆነን ነገሮችን በተለዬ አቅጣጫ ለማዬት ትዕግስት ይኑረን።

About