@askal935: #አቡነ አረጋዊ ወር በገባ በ14 ከዘጠኙ ቅዱሳ አንዱ የሆኑት አቡነ አረጋዊ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል ነው። አቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞ ሲደርሱ ወደ ሰማይ ቀጥ ያለች ተራራ ሰው በምንም መንገድ ሊደርስባት ወይም ሊወጣባት የማይቻለውን ቦታ እሳቸው ተመኙዋት። #ከዚያም "አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ" እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝሙር ፺፣፺፩:፲፩ - ፲፮ ላይ “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና ፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስደሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል፡፡ ወዲያው ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው አመስግነዋል። በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም፡፡ በሰንበተ ክርስታያን ከቅዳሴ በኋላ ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላች ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላ ግን ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውላቸዋል። የጻድቁ አባታችን በረከትና ምልጃ አይለየን!🙏

ባለ ማህተቧ ✝️🩷⛪
ባለ ማህተቧ ✝️🩷⛪
Open In TikTok:
Region: SA
Tuesday 23 December 2025 04:10:59 GMT
5143
166
3
37

Music

Download

Comments

lwamlwam05
ኪዳና ምህረት (16) እናቴ ሓደራኪ :
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ❤️❤️❤️
2026-08-20 09:19:55
0
askal935
ባለ ማህተቧ ✝️🩷⛪ :
ረድኤት በረከታቸው ይድረሰን🙏🙏🙏
2025-12-23 04:26:14
0
zeyneb.zeyneb878
ለሁሉም ጊዜ አለው :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2025-12-23 11:02:48
0
To see more videos from user @askal935, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About