@musictube369: 'ነጋ ነይልኝ'🤌😇 ✨በ1961 ዓመተ ምህረት በጎጃም ክፍለ ሀገር በምትገኘው የፍኖተ—ሰላም አውራጃ የተወለደው ፣አባቱ "በላይ—በትረሰላም" እናቱ ወይዘሮ " እንየው—መራ" ይባላሉ። እናቱ ቤት ውስጥ ሲጠሩት "የኔ ይሁን" በሚል ቁልምጫ ሲሆን፣ ወላጆቹ ከእሱ ሌላ ሁለት ወንድና፣ አንዲት ሴት ልጅ በአጠቃላይ አራት ልጆች አፍርተዋል። ✨ውድ ቤተሰቦቼ ዛሬ በ2017 ግለ ህይወት ታሪኩን በመፅሀፋ አሳትሞ ያደረሰን ኑሮውን በአሜሪካ ያደረገው የባህል ሙዚቃ ሲባል ቀድሞ ወደ አይምሮአችን የሚመጣው 'በአስተሪዮ ማርያም' የጥምቀት ስጦታው የምናስታውሰው እጅግ ተወዳጁን ይሁኔ በላይ ከብዙ በጥቂቱ እናወሳዋለን እናከብረዋለን🙌🙏🥰 ...... ይሁኔ ወደሙዚቃ የተሳበው ገና ጨቅላ ሕፃን ሳለ ነበር። በውስጡ የታመቀ የሙዚቃ ፍቅሩን ማውጣት የጀመረው ገና የ9 አመት ታዳጊ ሳለ ሲሆን፣ በዚህ ዕድሜው የታዳጊ ህፃናት የኪነት ቡድን ውስጥ መሳተፍ የጀመረው ይሁኔ፣ በሙዚቃ ከታች ብድግ ያደረጉት የባህል ጨዋታዎች ነበሩ። ምንም እንኳን የተወለደው በፍኖተ—ከተማ ውስጥ ቢሆንም ከተማዋን ከከበቧት የገጠሪቱ ክፍሎች ነዋሪዎቹ ይመጡ ስለነበርና ይሁኔም አልፎ አልፎ ወደገጠር ጎራ የማለት አጋጣሚው ስለነበረው፣ በበዓላትና በሰርግ ጊዜ ይዜሙ የነበሩ ዘፈኖችና ሃገረሰብ ጭፈራዎች ይመለከት ስለነበር ትንሽዬ ልቡ በባህል ዜማዎች ምርኮኛ ትሆን ጀመር። ወቅቱ ደግሞ ኪነት ከቀበሌ ጀምሮ፣ እስከ ክፍለ ሀገር ድረስ የተስፋፋበት ስለነበር ይሁኔ ውስጡ ያለውን ክህሎት ያወጣ ዘንድ ምቹ የሆነ አየር ፈጥሮለት ነበር። በጊዜው ከህፃናት ኪነት አንስቶ በየአመቱ የወረዳና የአውራጃ ውድድሮች ይካሄድ ነበር። ይሄ ውድድር የሚካሄደው ባህር—ዳር ከተማ ውስጥ ሲሆን፣ በቀድሞው መንግስት መዋቅር በነበሩ ሰባት አውራጃዎች መካከል በሚደረጉት ውድድሮች ላይ፣ የባህል ገፅታን ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ አልባሳቶች ራሱን የቻለ የውድድር ድምቀቶች ስለነበሩ፣ ይሁኔም በደበሎና ራስ ላይ በሚጠመጥመው ስታይሉ ዓይን ውስጥ መግባት ጀመረ። የእነይሁኔ አውራጃ በየአመቱ አንደኛ ይወጣ ስለነበር፣ በወቅቱ በጎጃም ምድር ተጠናክሮ የወጣው የግሽ አባይ የኪነት ቡድን አብሯቸው እንዲሰራ ጥያቄ አቀረቡለት። በወቅቱ ግን የ10ኛ ክፍል ተማሪ የነበረው ይሁኔ ትምህርቴን ልጨርስና እመጣለው የሚል ቃል ገብቶላቸው ስለነበር በቃሉ መሰረት ትምህርቱን አጠናቆ በ1979 ግሽ—አባይ ኪነትን ተቀላቀለ። ይሁኔ ግሽ—አባይ ከገባ በኋላ በመላው ኢትዮጵያ እሱና የኪነት ቡድኑ እውቅና የተጎናፀፉበት "አንቱዬዋ" የተሰኘውን ሙዚቃዊ ድራማን ሰሩ። ተደጋግሞ ቀደም ባለው ጊዜ በህብረት ትርዒት የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ ይቀርብ በነበረው በዚህ ሙዚቃዊ ድራማ .......የየራሳቸውን የሙያ ክህሎት ይዘው የወጡና ጥሩ ደረጃ የደረሱ አርቲስቶች የተሳተፉበት ሲሆን፣ የሙዚቃዊ ድራማው አዘጋጅና አቀናባሪ "እሱባለው—ጫኔ" ዋሽንት በመጫወት ነብሱን ይማረውና " ሃብቱ ንጋቱ ወይም አንሙቴ" እንደተፈቃሪዋ አባት "ሰማኽኝ—በለው" እንደእናት "አመለወርቅ—እለፈው" ይሁኔ ያፈቀራት ሆና የተወነችው "ብዙአየው—ጎበዜ" ነበሩ። የግሸ—አባይ ኪነት ቡድን የሀገሪቱ ትልቅ የባህል ነፀብራቅ የነበረና ብዙ ስራዎች ይሰራል ተብሎ ቢጠበቅም፣ አብዛኞቹ ያልተሳካ ህይወት ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ ከፊሎቹም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ምናልባት ከዚያ የኪነት ቡድን ሾልከው የወጡና ተሳክቶላቸዋል የሚባሉት ሰማኽኝና ይሁኔ ናቸው። ..........1980ዎቹ መግቢያ አካባቢ የፍኖተ—ሰላም ተወላጁና ጎጃሜው የባህል ሙዚቃ ፈርጥ የሆነው ይሁኔ—በላይ እንደማንኛውም ሰው የተሻለ ህይወትና ኑሮ ፍለጋ ወደዩናይትድ ስቴትስ በስደት አቀና። በእርግጥ የመጀመሪያ አካሄዱ ለስራ የነበረ ቢሆንም፣ የሃይማኖት አባቶችን ሳይቀር አስራ የምታስቀረው አሜሪካ የይሁኔንም ቀልብ ማርካ ውጣ አስቀረችው። ቢሆንም ግን ከዚያ በኋላ በሰራቸው አልበሞቹ በሙሉ የሀገሩን ባህል፣ ናፍቆት፣ ትዝታ፣ ትውፊታዊ ሃሳቦችን በማንሳት አያሌ ዜማዎችን አንጎራጉሯል። ክፍተት ሲያገኝም ሀገር ቤት ብቅ እያለና ገጠር ድረስ እየገባ የሙዚቃ ቪዲዮችን በመስራት ለትላንት ማንነቱ ያለውን ክብርና ታማኝነት ለመግለፅ ሲሞክር ይታያል። በባህል ዘፈኖቹ ያደገበት አካባቢ አሻራ ይኖር ዘንድ የሚፈልገው ይሁኔ፣ በመጀመሪያ ካሴቱ ስላደገበት አንድ ዋርካ ያቀነቀናት ዘፈኑ ትዝ ይለኛል። ይሄ ዋርካ ፍኖተ—ሰላም ውስጥ ይሁኔ ከጓደኞቹ ጋር ያደገበት የልጅነት ትውስታው ሲሆን፣ ፀጋዬ ደቦጭ ምርጥ አርጎ በግጥም ከትቦ እና ዋርካው ስለይሁኔ ፀባይና ባህሪይ እንዲያወራ አድርጎ ፅፎለታል። በእርግጥ ይሁኔ ጨዋ፣ ቅን፣ ቁጥብ፣ ለሰው ጥሩ ማሰብ መለያው የሆነ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው። ኑሮ ያልተሳካቸው የቀድሞ ጓደኞቹን ጭምር አሜሪካ ሆኖ በመደጎምና ችግራቸውን በመካፈል ለረጅም አመታት ሲረዳቸው የኖረና ትላንት አሻግሮ የሚመለከት ምስጉን ሰው ነው። ............" አሁን ምን ያደርጋል አሜሪካ ቢሉ አሁን ምን ያደርጋል ጅዳ ጅዳ ቢሉ መርካቶም ጅዳ ነው ጠንክረው ከሰሩ የሚለውን ስደትን ያጣጣለበት አልበሙን ባወጣ ሰሞን ወጥቶ የቀረው ይሁኔ፣ በእርግጥ አወጣጡ የተሻለ እንጀራ ፍለጋ ብቻ ሳይሆን፣ ለመቅረቱ ዋንኛው ምክንያት ያልታሰበ የህይወት አቅጣጫ ስላጋጠመው ነበር። ይሄ ከመንገድ የጠበቀው ህይወቱ ደግሞ የሰው ልጅ ሁሉ ዕጣ ፈንታ የሆነው ቤተሰብ የመመስረትና ልጆች የማፍራት መሰረታዊ ጉዳይ ሲሆን፣ ፈጣሪ የውሃ አጣጩን እና የግራ ጎን አጥንቱን አበጅቶ ይጠብቀው የነበረው በአንድ የቀን አጋጣሚ ነበር። ቦታው በካሊፎርኒያዋ ሎስ አንጀለስ ከተማ ሲሆን፣ እንደተለመደው በዚህች ከተማ አመታዊው የኢትዮጵያዊያን ደማቅ የስፖርት ፌስቲቫል ይደረግ ስለነበር፣ ተያይዞ በሚቀርበው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ይሁኔ ስራዎቹን እያቀረበ ነበር። የሙዚቃው አዘጋጅ የሆነውን ፕሮሞተር እህቱ በዝግጅቱ እያገዘችው ሳለ፣ ከስራው በላይ ቀልቧ ሙሉ በሙሉ ያረፈው በይሁኔ ላይ ነበር። ከአዘፋፈኑ፣ ከባህላዊ የአቀራረብ መስዕቡ በላይ ይህቺ ሴት የይሁኔ ወንዳወንድነትና፣ ጠይም ኢትዮጵያዊ ገፅታው እንዲሁም ሰው አክባሪ ትህትናው ሁለንተናዋን መስጦ በአጭር ጊዜ በአይን ፍቅር አንበርክኳታል። .......አስቴር አወቀ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ ምኒሊክ ወስናቸውን ጨምሮ አያሌ ዘፋኞችን በማሰራት ለሀገሯ ሙዚቃ የራሷን ሚና ተጫውታለች። እኔም ለዛሬ በሁላችንም ህሊና ውስጥ ተቀርፆ የቀረውን ነፍሱን ይማረውና በታላቁ ሙሉጌታ አባተ የተከሸነውን በተከበሩት አበበ ብርሃኔ እና ይልማ ገ/አብ ግጥም እና ዜማው የተዋሃደውን 'ኧረ ነጋ ነያ'ን ጋብዤያቹ አበቃሁ🙏 ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡🙌 musictube #fyp #ይሁኔበላይ #ነጋነያ #musictube369 #ethiopianmusic

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 31 December 2025 21:40:02 GMT
32028
1366
20
107

Music

Download

Comments

user943818612309
Sew Mehone :
In Ethiopia traditional music history yerasun yehone ashara yanore best musician new Yihune Enamesegnallen. 🙏🙏🙏.
2026-01-01 17:35:13
6
miki.king61
Miki King🤴🇪🇹🤫 :
ልጅነቴን የሚያስታውስኝ ሙዚቃ 🥰🥰
2026-01-25 10:11:13
1
user8005758188123
Nani :
ደስ ሲል የ90s 👌👌
2026-01-01 18:23:43
4
kingezanna
Ezedin 📿 🌱 🧘🏽‍♂️ :
☀️
2026-02-03 14:31:28
1
tewodros.gebre2
ayu gebre swot man :
🙏🙏🙏🙏🙏yehoni belaye
2026-01-07 10:02:55
1
iwalkthisearthallbymyse7
typing...? :
pls aster aweke azezo 🎶
2026-01-22 19:21:12
0
fits4abu
@fitsum :
@ሊያ 🤪🥰😘
2026-01-01 06:27:31
2
tizitanegash
Luna🌙✨ :
🥰🥰🥰
2026-01-04 14:27:25
1
elsabet.argaw5
Elsabet Argaw :
🥰
2026-01-05 12:41:59
1
binu.wolde
Binu Wolde :
🥰🥰
2026-01-01 06:22:20
1
whoknows1105
it's me😎 :
🥰🥰🥰
2026-01-01 05:40:24
1
ermiyas_t
Ermiyas_t :
🥰🥰🥰
2026-01-01 05:03:42
1
kidist7392
QuiteStrom 🌷 :
🔥🔥🔥
2025-12-31 21:49:47
1
anirhami.abir
AFRHM. 🤙💫💞💯💖 h :
🥰🥰🥰
2026-01-25 03:00:25
0
1qenyisakal2
Yesuf woloyew🥷🇨🇦🇨🇦 :
👍👍👍
2026-02-05 16:01:23
0
rewada66
Rewdi :
😂😂😂
2026-01-30 06:39:23
0
user686603404434
R♥️♦️🧸 :
Neya neya ere neya neya
2026-02-14 18:50:50
0
10babi27
B@bi ካዛ :
Yazzzz
2026-01-01 04:42:17
8
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About