@musictube369: "ሰው መሆኔ"🩵🤒 ✨ዓለም ላይ ብርቱ የሚባሉ የጥበብ ሰዎች አሉ። ከነዚያ መካከል አንዷ ናት ለሙያ ስትፈጠር እንደ አስቴር አወቀ ግማሽ ክፍለ ዘመን በብቃት ትውልድን አስተሳስረህ በፍቅር የነገሰች 👸 *የተዋጣላት የዜማ ደራሲ *የግጥም ደራሲ *የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች እና በቅንብር የምትሳተፍ *ኑሮዋን በአሜሪካን ሀገር ካደረገች ጀምሮ ደግሞ የተዋጣላት ዲዛይነር በመሆን ለረጅም አመት የሀገሯን ባሀል ያስተዋወቀች (መድረክ ላይ የምታደርጋቸው ውብ የባህል ልብሶች በራሷ ዲዛይን የተደረጉ ናቸው) ባለድንቅ ተሰጥኦዋ እንደ ህፃን ልጅ የቅን ልብ ባለቤቷ አስቴር አወቀ (አስቱካ) የኔ ጨዋ!🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ዛሬ የአሸናፊነት ምሳሌዋን የሶል ንግስቷን አስቴር አወቀ በዚህ ገና መግቢያውን ስንስማው አረማመዷ የሰው ፍቅሯን ፈገግታዋ ሹሩባዋ በዓይነ ህሊናችን የሚስለው በአሜሪካን ሀገር የሰራቺው ክሊፗ እንደ ትላንትን መመልከቻ መስታወት በሚያሳየን 'ሰው መሆኔ' ሙዚቃን ጋብዤያቹ እንማርበት ዘንድ ውጣ ውረድ የተሞላበትን የብርቱዋን የህይወት ታሪክ በትንሹ አካፍላቹሃለው🙏 -------------------------------------------------------- ብቃቷን ስላረጋገጠችበት ተሰጥኦዋ ዛሬ ብዙ አልልም። ይልቅ ብዙ ስላልተነገሩት አስገራሚ እና የአይበገሬነት ታሪኳእንጅ! ✍️አስቴር የተወለደችው በቀድሞው አጠራር ጎንደር ክፍለ ሀገር ደብረታቦር አውራጃ ደራ ወረዳ ልዩ ስሟ ሀሙሲት በምትባል አነስተኛ መንደር ነው ። በቤተሰቦቿ በሥራ ዝውውር ምክንያት ለአጭር ጊዜ አሰላ ከዛም አዲስ አበባ ኖራለች። በትምህርቷ በጣም ጎበዝ ከሚባሉት ተማሪዎች ተርታ የምትመደብ ተማሪ ነበረች። በ1956 ዓም የወሰደችው የ6ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና (ሚኒስትሪ) ውጤቷንን የሚያሳያውን ፎቶ ብዙዎች በሶሻል ሚዲያው ላይ ያያችሁት ይመስለኛል። ለሙዚቃ በነበራት ከፍተኛ ፍቅርና ፍላጎት ድምፃዊ ለመሆንወደ ፖሊስ ኦርኬስትራ በመሄድ ያደረገችው የመጀመሪያ ሙከራ " ድምፃዊ መሆን አትችይም" በሚል መራር ውሳኔ ተደመደመ። እንደማስተዛዘኛ ግን በተወዛዋዠነት እድሏን እንድትሞክር ተፈቅዶላት ፖሊስ ኦርኬስትራን ለ7ወር በተወዛዋዥነት በነፃ በማገልገል ኪነጥበብን ተቀላቀለች። ከ7ወር ግልጋሎት በኋላም በነፃ ዝውውር ወደ አንጋፋው የሀገር ፍቅር ቲያትርቤት በመዘዋወር ከ1965 እስከ 1967 ዓ_ም በተወዛዋዠነት ማገልገሏን ይታወሳል። በዚህ እልህ አስጨራሽና ተስፋ አስቆራጭ ሂደት ሙያዋን የጀመረችው አይበገሬዋ ድምፃዊት የመጀመሪያ የሙዚቃ ሸክላዋን በተመለከተ አሳታሚው የታንጎ ሙዚቃ ቤት ባለቤት ነፍሳቸውን ይማርና ታላቁ አሊ አብደላ💔 ባንድ ወቅት እንዲህ በሚል ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል " አስቴርን በሸክላ ለማስቀረፅ ስመርጣት ድምጿአይሰማም ከሚል ስጋት " ይቅርብህ " ያሉኝ ሰዎች ብዙ ነበሩ ። እኔ ግን ቁ1 ስራዋን በድፍረት አሳትሜ አወጣሁት፡ ያው እንደተፈራውም ተቀባይነቱ ቀዝቃዛ ነበረ ። ሰዎችን ስጠይቃቸውም "ድምጿ ጥሩ ነው ምን እንደምትል ግን አይሰማም "ይሉኝ ነበር ። እናም አስቴርም በወቅቱ " በቃ እኔ ሙዚቃ አይሆንልኝም" ብላ ተስፋ ቆረጠች ። እኔ ግን እሷ ትልቅ ቦታ የምትደርስ ድምፃዊ እንደምትሆን እርግጠኛ ስለሆንኩኝ እልህ ውስጥ ገብቼ አስቴርንም አበረታትቼ ፣ የድርሰት ማጥኛ ቤት አዘጋጅቼ ፤ ውብሸት ፍሰሀን ጨምሬ ረጅም ጊዜ በፈጀ ጥናት በባህል መሳሪያዎች የታጀበ ስራቸውን አሳትሜ ሳወጣው ተቀባይነቱ ዳር ከዳር ከመሆኑም በላይ ያኔ ያልተደመጠው የመጀመሪያ ስራዋ ሁሉ እንደገና እንደ አዲስ ይፈለግና ይሰማ ጀመር ። ሀገሩ ሁሉ አስቴር አስቴር ይል ጀመር።"🥰 ብለው ነበር ታዲያ በዚህ መልኩ የአይበገሬነት ጉዞዋን የጀመረችው አስቴር አወቀ ግማሽ ክፍለን ዘመን በሚጠጋው የሙዚቃ ዘመኗ አንድ የሸክላ ሙዚቃን እና 25 የሙዚቃ ካሴቶችን በግሏ እንዲሁም _አንድ የሙዚቃ ካሴት ከድምፃዊ ውብሸት ፍስሀ ጋር በጋራ _ከድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ጋር" መች እንዲህ "የተሰኘ አንድ ዜማ በቅብብል _"እንኖራለን ገና "በሚል በኤች አይ ቪ ዙሪያ የተሰራ የጋራ አልበም ከአስቴር አወቀ የረጅም አመት ጥረት ና ውጤት ጀርባ ድርሻ ካላቸው መካከል አሊ አብደላ የታንጎ ሙዚቃቤት ባለቤት ተሾመ ፀጋዬ የኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ባለቤት የሚያስመሰግን ትልቅ ድርሻ አላቸው ። አስቴር እጅግ ከበርካታ የግጥም እና ዜማ ደራሲያን ለቁጥር ከሚታክቱ የሙዚቃ ባንዶች እና አቀናባሪዎች ጋር የሰራች ሲሆን አበጋዝ ክ/ዎርቅ ታዲያ እጅግ በበርካታ ሙዚቃዎቿ ጀርባ ያለ የተከበረ ታላቅ የሙዚቃ ሰው ነው ክብር ይገባዋል🙏🙏 አስቱካ ፈጣሪ እድሜን ከጤና ጋር ጨምሮ ይስጥሽ❤ ለዛሬ አበቃሁ🥰 ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡🙌 musictube #fyp #አስቴርአወቀ #ሰውመሆኔ #musictube369 #ethiopianmusic

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 05 January 2026 21:36:35 GMT
386304
17904
132
1386

Music

Download

Comments

user943818612309
Sew Mehone :
Eshi yih mn yibalal endih aynet intro keyet new yemigegnew kemr tikikilegna ye temesto music new Abegaz kelib enamesegnallewn 👏👏👏🙏👏👏👏.
2026-01-06 06:36:14
31
sebriesmael
sebri :
ንግስቲቷ🥰🥰🥰🔥🔥👌👌👌
2026-01-05 21:41:22
64
amanuelk4
Amanuel ketema :
be docter tezaz pharmacy mesht yalbet, masterpiece, the deep lyrics, the melody ,the bridges plus astukas voice
2026-01-07 18:04:39
4
tewodros183
Tewodros183tedy :
እናመሰግናለን 🥰🥰🥰🥰🥰🙏!!!
2026-01-06 14:59:18
16
ginayon1
እናይ❤ :
the melody so powerful the lysrics so..❤🥺
2026-01-08 05:11:45
2
user6419303919443
tse507 :
thanks 🙏🙏🙏🙏🙏 yenegstuan bebzat please 🙏🙏🙏🙏🙏 please 🙏🙏🙏🙏🙏
2026-01-08 11:57:46
1
tarefani637
tare Fani :
ፍትፍት የሆነ ሙዚቃ
2026-02-21 18:35:53
1
selina69952
Selina :
my favour music 🥺
2026-01-07 20:09:11
5
tgds059
Winta👸 :
አስቱካዬ 😍🙏❤
2026-01-05 22:03:39
7
user329246589
Selam :
የኔ ውብ🥰🥰🥰🥰🥰
2026-01-09 19:40:11
1
tokyo0733
@mita zam🧚‍♀️ :
❤❤️🥰❤leyazew mengedn❤❤❤❤
2026-01-09 16:00:05
4
ekramhassen1
reham :
Astuye my medicine ❤❤❤❤
2026-01-06 01:18:06
5
user7451873222386
@Habtoom :
አወይ ሰው መሆኔ🥰🥰🥰🥰
2026-01-06 14:09:32
2
jovanijo22
jovanijo22 :
endim lka nbsn miyaschnk zfn alen🥰
2026-01-06 04:42:26
3
user7909042650228
Nafkot :
ንግስቲቷ👏👏👏👏
2026-01-06 03:20:45
3
yimamousman0
yimam ousman :
love music best
2026-01-06 21:08:06
2
zolazelzalaw
ዘላለም :
የኔ 👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸👸
2026-01-27 07:19:03
1
mesti468
mesti :
Astuyee🥰🥰🥰
2026-01-07 20:04:46
1
addisgursha
Addis Gursha :
the only song i listen to
2026-01-06 07:19:51
7
daniel7kiwi
Daniel7kiwi :
ብሰማው የማይሰለቸኝ ዘፈን😊
2026-01-06 10:22:13
7
baesg18
baesg2 :
best music 🎵🎵🎵 ever thanks to our legends
2026-01-08 20:32:20
1
abrila76
Abrila AK :
አወይ ሠው መሆኔ
2026-01-07 16:04:42
1
antshztaye
Antshzgunner :
OMG!!!She did wrote this song. In deed she is z queen
2026-01-07 19:08:06
1
bydbonda2bydfashion
Beya Beya :
Queen Astukaaaaaaa
2026-01-06 05:06:59
2
whoknows1105
it's me😎 :
Queen 👑
2026-01-06 03:17:14
2
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About