@musictube369: "ሁለመናሽ ሙሉ"🩵🤌 ✨ባለፉት 40ዓመታት የኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ታላቅ ቦታን ይዟል። በእሱ ዘመን ከነበሩት ድምፃውያን መካከል መልካሙ ተበጀ ፣ሙሉቀን መለሰ፣ እና ጥላሁን ገሰሰ እንደነሱ ዘፈንን በመስማት ነበር ወደ ሙዚቃው አለም የተቀላቀለው። ከያሬዳዊ ዜማ ዝማሬ ጎን ለጎን ለላቲን፣ በተለይ ደግሞ ለጃዝ የሙዚቃ ስልት ልዩ ፍቅር እንዳለው እና ከማዳመጥ በዘለለም የሙዚቃ ስልቶቹን በስራዎቹ ውስጥ አብዝቶ እንደሚጠቀም ይናገራል። "ሆድ በሚበሉ" የፍቅር ዜማዎቹ ይታወቃል። በ1970ዎቹ ዋዜማና በ1980ዎቹ መባቻ ላይ "ዝነኛው" የሚል ቅፅል ስያሜው የሚታወቀው እጅግ ተናፋቂው ተወዳጁ ቴዎድሮስ ታደሰ🙌 ------------------------------------------- ✨ውድ ቤተሰቦቼ የቴዎድሮስ ታደሰ"ዝምታ" አልበም በቆየ ቁጥር እንደ ወይን ይበልጥ የሚጥም ብዙዎች እንደሚሉት ዝምታን ለማድነቅ ቃላት ስለሚያንሰኝ ዝም እላለሁ🤫 ለዛሬ ታዲያ በወርቅ የተለበጡ 10 ሙዚቃዎችን ከያዘው ከዚህ ዘመን ተሻጋሪ አልበሞች ተርታ ከፊት ከሚቀመጠው ስራ ላይ ነፍስ የሚሰለበውን የታላቋ የዓለምፀሐይ ወዳጆ የግጥም ስራ በራሱ የዜማ ልህቀት ተራቆ በአበጋዙ የተከሸነውን ውብ የፍቅር ዘፈን 'ሁለመናሽ ሙሉ'ን ጋብዤያቹ ሁሌ እንደማደርገው ሙዚቃውን አስታከኬ ስለተወዳጁ ቴዲ ታደስ በጥቂቱም ቢሆን ትንሽ ላወጋችሁ ወደድኩ።🙏🥰 ---=== በአዲስ አበባ ተወልዶ ያደገው ቴዎድሮስ ታደሰ ፣ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ትውልዶችን ያገናኘ በተለያየ የእድሜ ደረጃ ያሉ እና የተለያየ አይነት ጣዕመ ዜማ (Music taste) ላላቸው ሰዎችም ተደራሽ ስለሆነ በብዙዎች ይወደዳል። ---=== ሙዚቃን የጀመረው በቤተክርስቲያን እያለ ሲሆን የቴዲ የሙዚቃ ህይወቱን ያስጀመረለት ትልቅ አጋጣሚ በሰርግ ፕሮግራም ላይ እንዲዘፍን ተጋብዞ የሙሉቀን መለሰን "ዋሳ መገና"ን የዘፈነ ጊዜ ነበረ። ---=== ሙዚቃን ከጀመረ በኋላ በብዛት የቀደምት ድምፃውያንን ስራዎች (በተለይ የሙሉቀን መለሰን) ከህዝብ ጋር ተገናኘ። ከህዝብ ያገኘው አስተያየት ገንቢም ጠቃሚም የሆነለት ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ የመጀመሪያ አልበሙ "ሉባንጃዬ" በቀላሉ ነበር ገበያውን የተቆጣጠረው። በማስከተልም "እየቆረቆረኝ" እና "ሳዱላዬ" አልበምን በተከታታይ በመልቀቅ ለሙዚቃ ወዳዱ ህዝብ ስራውን በላይ በላይ ተደራሽ አድርጓል። ---=== አንጀት በሚበላው ድምፁ ያዜመው "እምዬ ኢትዮጵያ" የተሰኘ ዜማውን ትልቅ ትንሽ በየትኛውም የእድሜ ደረጃ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን ልክ እንደ ብሔራዊ መዝሙር ያዜሙታል። ---=== ቴዎድሮስ ታደሰ ደስ በሚለው ድምፁ ብዙ ሀገሮችን እየዞረ አድናቂዎቹን አዝናንቷል። "ሰምቶ ዝም አለ" የሚለውን 5ኛ አልበሙን አጠናቅቆ አሜሪካ ዳንግላ Virginia ከገባ በኋላ ለአድናቂዎቹ አድርሷል። አሜሪካ እያለ ብዙ ቦታዎች ላይ የሙዚቃ ዝግጅቱን ቢያቀርብም በብዙ ኢንተርቪዎች ላይ የስደት ኑሮ እንዳልተመቸው ይናገር ነበር። ---=== "ዝምታ" የተሰኘው ይሄ አልበሙ ከበፊቶቹ አልበሞች በተለየ ሁኔታ Jazz ነክ ስለነበሩ ቲኒሽ ቅሬታን አስተናግደው ነበር። ቢሆንም አዲስ ነገር ለሙዚቃ ቤተሰቡ አድርሷል። ከብዙ የህይወት ውጣ ውረዶች የተነሳ ስራው ላይ ትኩረት ማድረግ ያልቻለው ቴዎድሮስ ታደሰ፣ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ለሱ ከባዱ ውሳኔ ነበር። የሚገርመው ግን ለ 17 ዓመታት ያህል አይተውት የማያውቁት አድናቂዎቹ አየር ማረፊያ ድረስ ተገኝተው ተቀብለው አስደምመውታል። ---=== ቴዲ ታደሰ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክፍሎች የሙዚቃ ዝግጅቱን ካቀረበ በኃላ ወደሚኖርባት አሜሪካ በመመለስ በ2009 እራሱን የቻለ ስቱዲዮ አቋቁሟል። የ "Yo Yo Records" ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆነው ቴዲ ታደሰ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ የሙዚቃ ስልቶች ማስተዋወቅን አላማው አድርጓል። አንዳንድ ሙዚቃዎቹን ከመዝሙር ለይቼ አላያቸውም ከስጋ አልፈው ከመንፈስ የሚዛመዱ ይመስል ልዩ ተመስጦ ውስጥ ከተው ልብ ይሰልባሉ የቴዲ ሙዚቃዎች እንዲህ ናቸው❤ ፈጣሪ ባለህበት ጠብቆ እድሜ እና ጤና ይስጥህ እንወድሃለን 🥰🙏🙏 --------------------------------- ለዛሬ አበቃሁ🙌 ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡🙌 musictube #fyp #ቴዎድሮስታደሰ #ሁለመናሽሙሉ #musictube369 #ethiopianmusic

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 08 January 2026 18:53:32 GMT
185526
13039
90
2202

Music

Download

Comments

hilufeyy
𝑚𝑖𝑟𝑎𝑐𝑙👸🦅 :
ማንም እሱን አይተካም he is legend 👑👑🐐🐐
2026-01-08 19:46:15
154
abebeyadechu
AB በቸርነቱ :
ንዝረት ሚፈጥርብኝ ሙዚቃ 👏👏👍 🎵🎶🎵
2026-01-08 19:12:43
37
waduwrld
₩adu :
Thank you Music tube🫡 Teddy Tadesse 🐐
2026-01-12 12:46:43
7
officialhenokk
HENOK🩻 :
what can't this guy do?? 😭
2026-01-09 12:28:12
15
user943818612309
Sew Mehone :
Sweet,Slow,Cool,deep lyrics, Imaginary melody,heart break intro woof beka no words just respect for all musicians in this album especially Abegazu🙏.
2026-01-09 06:12:03
19
edomawit21
Edom🌸 :
💞
2026-01-09 11:57:18
21
selmity
selmity :
ድንቅ ሙዚቃ ነዉ🥰🥰🥰
2026-01-08 19:16:43
8
euri.mn
euri.mn :
የእምነት ማህተም ናት🥰🥰🥰🥰🥰
2026-01-10 06:42:16
2
manta_sdi______
Gracy :
ለእናቴ🥰🥰🥰
2026-01-09 19:44:58
3
martimitu
ማርቲ ዲፕል :
yene teddy
2026-01-11 16:37:36
2
kebirhas
ከ_ቢ_ር ✍️ :
ሌላ ዓለም🐐🐐🔥🔥🔥
2026-01-08 19:26:20
5
taf88_5
Taf :
teddyyy😫🥰
2026-01-09 05:19:29
7
simonepop6
baba pogba :
my fav one 😍🔥
2026-01-10 18:14:55
1
kali_asse
La promessa💎 :
ufff peace 🔥
2026-01-09 20:46:24
2
nura49924
sumeya🌸 :
ufffffff🥰
2026-01-10 19:05:36
1
samrisam12
Samri🦋♠️ :
Legend ❤❤❤❤
2026-01-13 06:51:37
1
brelala0
bre lala :
king 👌👌🙏🙏🙏 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 👌👌👌👌👌👌👌
2026-01-10 15:53:23
1
temuel12
temuel :
my fav one
2026-01-10 04:19:00
2
dureyew41
🅜🅝🅣🅔🀄️⚜️ :
Teddy 🐐
2026-01-08 19:10:28
2
barcode5551
ባርክ :
❤❤❤❤❤ ኑርልኝ
2026-01-08 19:11:29
2
tehaabdo0
Teha :
Tedy 👍
2026-01-09 18:55:04
1
tarmp6
@Trump✌️ :
Tedi is king kingo
2026-02-06 18:02:15
0
tedros.tadese55
🏍🅈🄰🅈🄰🏍🎧tedi💝 :
❤️❤️
2026-02-24 22:29:15
0
mekoda.music
mekoda music :
አለም ፀሀይ ወዳጆ ግን🥰🥰🥰 🥰🥰🥰
2026-03-06 06:13:39
0
samrawitbelege
samrawitbelege :
My🥰🥰🥰🥰
2026-01-12 13:20:47
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About