የፌስቡክ ፔጅ (My New Facebook Page) https://www.facebook.com/AfendiEthno2018 => የቴሌግራም ቻነል (My Telegram Channel) https://t.me/afandishaHarar ---- Galatoomaa! እናመሰግናለን። Thank you! የቕንለይ! - @afendi1978"/>
የፌስቡክ ፔጅ (My New Facebook Page) https://www.facebook.com/AfendiEthno2018 => የቴሌግራም ቻነል (My Telegram Channel) https://t.me/afandishaHarar ---- Galatoomaa! እናመሰግናለን። Thank you! የቕንለይ! - @afendi1978 - Tikwm"/>
የፌስቡክ ፔጅ (My New Facebook Page) https://www.facebook.com/AfendiEthno2018 => የቴሌግራም ቻነል (My Telegram Channel) https://t.me/afandishaHarar ---- Galatoomaa! እናመሰግናለን። Thank you! የቕንለይ! - @afendi1978"/>
@afendi1978: አፈንዲ ሙተቂ ------ በአንድ ወቅት በዚሁ ግድግዳ ላይ በለጠፍኩት ጽሑፍ "እኔ የኬኔዲ መንገሻ እና የከዲር ሰዒድ ትውልድ አባል ነኝ" ብዬ ነበር። እንዲያ ያልኩት ለሀንጀባ ሳይሆን ከልቤ ነው። ታዲያ አንዳንዶች አባባሌን በምሳሌ እንዳስረዳ ጠይቀውኛል። እኔም ለምላሹ ሳስብበት ነበር። ኬኒዲ መንገሻ እና ከዲር ሰዒድ ከልባቸው አርቲስቶች ነበሩ። ሁለታቸውም በልበ ቀናነታቸው ተመስክሮላቸዋል። በተለይ ግን እነዚህ ሁለት መሳጭ አርቲስቶች በ1980ዎቹ ውስጥ በሙዚቃቸው በጣም ነበር ቀልባችንን የገዙት። ሚሊዮኖችን በጥበብ ስራቸው አስደስተዋል። አስተክዘዋል (በሀረርጌ ያልተወለዳችሁ አማርኛ አድማጮች ከዲር ሰዒድን ብዙ አታውቁትም ይሆናል። በሀረርጌ የተወለደ ሰው ግን ያለ ብሄር እና ቋንቋ ልዩነት ዘፈኖቹን ይሰማ ነበር። ከዲር በሌሎች የኦሮሚያ ዞኖችም በጣም ይታወቃል)። ------ በዛሬዋ ምሽት የኔ ትውልድ ቀንዲል የሆኑት ኬኔዲ መንገሻ እና ከዲር ሰዒድ በተመሳሳይ ርእስ ላይ የዘፈኗቸውን ሁለት ዘፈኖች ከግጥሞቻቸው ውበት፣ ከዜማ ፍሰታቸው፣ ከመልእክታቸው ግዝፈት እና ከሙዚቃ ቅንብራቸው ርቀት አንጻር እየፈተሽኩ ላስቃኛችሁ እቅድ ነበረኝ። ነገር ግን ያልተጠበቀ እንግዳ ቤቴ ድረስ መጣና በዘመዳሞች መካከል የተፈጠረውን ግጭት እንዴት እንደምንፈታው እየተወያየን ነው። ስለዚህ ነገሩን በቀጠሮ ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ተገድጃለሁ። በነገራችን ላይ ኬኔዲን እና ከዲርን የሚያመሳስላቸው ሌላ ትልቅ አብነት እንዳለ ልብ ብላችኋል? ሁለቱ አርቲስቶች ካወጧቸው ካሴቶች መካከል ብዙዎቹን ያሳተሙት በአንድ ሙዚቃ ቤት ነው። እርሱም የድሬ ዳው "ነጋሪት ሙዚቃ ቤት" ነው። ይህም ብዙዎች ልብ ያላሉት ነገር ግን አርቲስቶቹን በጥበብ ያጣመረ ክስተት ነበረ። ----- አፈንዲ ሙተቂ ጥር 3/2018 ተማም! ሰላም! ---- የሶሻል ሚዲያ አድራሻዎቼ የሚከተሉት ናቸው። => የፌስቡክ ፔጅ (My New Facebook Page) https://www.facebook.com/AfendiEthno2018 => የቴሌግራም ቻነል (My Telegram Channel) https://t.me/afandishaHarar ---- Galatoomaa! እናመሰግናለን። Thank you! የቕንለይ!
Afendi Muteki
Region: ET
Monday 12 January 2026 18:48:59 GMT
Music
Download
Comments
ISA :
🥰🥰🥰
2026-01-12 20:32:37
0
Mekdse Melese :
❤️❤️❤️❤️
2026-05-18 21:35:53
0
To see more videos from user @afendi1978, please go to the Tikwm
homepage.