@musictube369: 'ልጅነት'😇🌝 ✍️ከተለመደው የድርሰቶቻችን አጻጻፍ ዘውግ ወጣ ብለው የራሳቸውን ልዩ የስነ-ጽሑፍ ዘይቤ እና የአትኩሮት ፈርጅ ለማስተዋወቅ የደከሙ ጥቂት ደራሲያን አሉ። ከእነዚያ ጥቂቶችም አንዱ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት የብዕር ገበሬ ነው። ይህ ደራሲ ለየት የሚለው በርካታ ሰዎች (በተለይም ከተሜዎች) ብዙም ትኩረት የማይሰጡትን የብሄረሰብ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ተንተርሶ ግማሽ ደርዘን ያህል መጻሕፍትን ለተደራሲያን በማበርከቱ ነው።👌 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ዛሬ ስለ ጎሳዬ ወይንም ስለዚህ አልበም እና ስለ የከተማው መናኝ ተወዳጁ ኤልያስ መልካ ላወራቹ አልመጣሁም ይልቁንም ከሙዚቃው ዓለም ወጣ እንልና አንድ ታላቅ ደራሲ እንድናወሳ ወደድኩኝ አዎ ከዚህ ሙዚቃ ጋር ምን አገናኛቸው? ካላችሁኝ የዚህ እኔን ጨምሮ በርካታ የሙዚቃ ወዳጆች ከምንግዜም ምርጥ አልበሞች ተርታ ከላይኞቹ መደብ የሚመቀመጠው 'ኢቫንጋዲ' አልበም የመጠሪያ ስም ላገኘው ሙዚቃ የሀሳብ መነሻ የሆነውን መፅሀፍ የደረሰ ታላቅ ኢትዮጵያዊ የስነፅሁፍ ሰው ነውና ዛሬ እናከብረዋለን🙌🥰 ኢትኖግራፈሩ ደራሲ ----- ፍቅረ ማርቆስ ደስታ ይባላል። በ1955 በጎጃም ክፍለ ሀገር ነው የተወለደው። በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ ዲፓርትመንት በዲግሪ ተመረቀ። በተመሳሳይ ጊዜ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ሆኖ በደቡብ ኦሞ ዞን፣ ጂንካ ከተማ ተመደበ። እዚያ መኖር ሲጀምርም በዞኑ ባሉት አስራ ስድስት ብሄረሰቦች ቋንቋ፣ አለባበስ፣ አመጋገብ፣ ጌጣ ጌጥ፣ የኢኮኖሚ ስምሪት፣ ባህላዊ ዳኝነት፣ ማህበራዊ ህይወት፣ ሙዚቃ፣ ዳንኪራ፣ አፈ-ታሪክ፣ ስነ-ቃል ወዘተ ተማረከ። ፍቅረ ማርቆስ ያየውን ነገር በማድነቅ ብቻ አልታቀበም። ከመምህርነት ሙያው ጎን ለጎን ያየውንና የሰማውን ነገር በጥልቀት አጥንቶ ለመክተብ ወሰነ። በዚህም መሠረት ከብሄረሰቦቹ መካከል እርሱ ላለበት አካባቢ ቀረብ የሚለውን የሀመርን ህዝብ ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ኪነ-ጥበብ እና ትውፊት በማጥናት ያገኘውን ውጤት እንደ ግብአት ተጠቅሞ ኢትኖግራፊያዊ የፈጠራ ጽሑፎችን መጻፍ ጀመረ። በ1987 የመጀመሪያ ድርሰቱ የሆነውን "ከቡስካ በስተጀርባ"ን ለህትመት አበቃ። ---- ፍቅረ ማርቆስ መጽሐፉን ለህትመት ሲያበቃ ይዞት የተነሳው ጭብጥ ስለፍቅር እና ወንጀል መጻፍ በለመዱት ደራሲዎች እና በዚህ ዐውድ የተጻፉትን ድርሰቶች ማንበብ በለመደው ተደራሲ ዘንድ አጓጊ እና አነጋጋሪ መሆን አልቻለም ነበር። በአንትሮፖሎጂ እና ታሪክ ጥናት ዘርፍ የተሰማሩ ምሁራን ግን ስራውን በጣም ነው ያደነቁለት። አንዳንዶቹም በዘመኑ ጋዜጦች እና መጽሔቶች ላይ የተለያዩ ግምገማዎችን ጽፈውበታል። ከዓመት በኋላ ደግሞ መጽሐፉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር ባለው የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም "ፍኩይ" የተሰኘ ሽልማት ተሸልሟል። በዚህ የተነቃቃው ደራሲ ፍቅረ ማርቆስ በ1990 በብዙዎች ዘንድ የሚወደደውንና የእርሱ masterpiece ስራ ለመሆን የበቃውን "ኢቫንጋዲ"ን ለአንባቢያን አበረከተ። በተከታዮቹ ዓመታትም " የዘርሲዎች ፍቅር"፣ "አቻሜ" እና "የንስር ዐይን" የተሰኙትን መጻሕፍት አሳተመ። በ1995 ገደማ አምስቱንም መጻሕፍት በአንድ ላይ አጠቃልሎ ወደ እንግሊዝኛ ተርጉሞ ሲያበቃ መጽሐፉን "Land of the Yellew Bull" በሚል ርእስ ለህትመት አበቃ። ------- ደራሲ ፍቅረ ማርቆስ ደስታ በመጽሐፎቹ የሀመርን ህዝብ በማስተዋወቅ ብቻ አልቆመም። በብሄረሰቡ ደንብ መሠረት የሀመሮች አካል ሆኖ ከእነርሱ ጋር ኖሯል። ሀመሮች ደራሲው በብዕሩ የዋለላቸውን ውለታ በደንብ በመገንዘባቸው እንደ አንጋፋ ልጃቸው ይመለከቱታል። ይሁን እንጂ በ2004 "እሄዳለሁ" ብሎ ሳያስታውቃቸው ወደ አሜሪካ በመሻገሩ በጣም ተናደውበት ነበር። ፍቅረ ማርቆስ በአሜሪካ ለአስር ዓመት ያህል ከቆየ በኋላ አምና ወደ ሀገሩ ተመልሷል። ታዲያ ደራሲው ወደ ሀመሮች ዘንድ ሲደርስ በዝምታ አልታለፈም። "በባህላችን መሠረት ጠፍቶ የመጣ ሰው ወደ ህዝቡ የሚቀላቀለው ከተገረፈ በኋላ ነው" ሲሉት ለመገረፍ አላቅማማም። ቅጣቱን ከተቀበለ በኋላም ከሚወዳቸው የሀመር ብሄረሰብ አባላት ጋር ተቀላቅሏል። ------- ሀመር የሚባለው ኩሻዊ ቋንቋ ተናጋሪ ብሄረሰብ በኢትዮጵያ ምድር ለረጅም ጊዜ ነው የኖረው። በቀድሞ ዘመናት ስለዚህ ህዝብ ባህል፣ ታሪክ እና ትውፊት የነበረን እውቀት በጣም ውስን ነው። የሀመር ማንነት ወለል ብሎ የታየን ደራሲ ፍቅረ ማርቆስ ደስታ ባደረገው የብዕር ተጋድሎ ነው። ደራሲው ብዙ የለፋበት ብሄረሰቡን የማስተዋወቅ ስራ ውጤት ማምጣቱንም በራሱ ዐይን ለማየት ችሏል። ለምሳሌ በድሮ ዘመን የ"ኢቫንጋዲ"ን ምንነት የሚያውቅ ሰው እጅግ በጣም ጥቂት ነው። ባለፉት ሀያ ዓመታት ግን "ኢቫንጋዲ" በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅ ጽንሰ ሐሳብ ለመሆን ከመብቃቱ ባሻገር ለብዙ የፈጠራ ስራዎች መነሻ ሲሆን አይተናል። በዚህ ረገድ ጎሳዬ ተስፋዬ የተጫወተው "ኢቫንጋዲ" የተሰኘው ተወዳጅ ዘፈን እንደ አብነት ሆኖ ሊነሳ ይችላል። ----------- ኢትዮጵያ ውብ ናት! በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት የውበቷ ፈርጦች መካከል አንዱ ብሄርና ብሄረሰቦቻችን፣ ቋንቋዎቻችን፣ የብሄሮቻችን ቱባ ባህል፣ ትውፊት፣ ኪነ-ጥበብ እና ታሪክ ነው። በዚህ በኩል እንደ ኢትዮጵያ የታደሉት ጥቂት ሀገሮች ብቻ ናቸው። እነዚህ በፈጣሪ የተሰጡንን ውበቶች እንደ ትልቅ ጸጋ ቆጥረን በደንብ ከያዝናቸውና ከተጠቀምንባቸው የፍቅር ማጎልበቻ ከማድረግ አልፈን ከፍተኛ ገቢ ልንዝቅባቸው እንችላለን። ይህንን ለመረዳት ካሻን አሁንም የደራሲ ፍቅረ ማርቆስ ደስታን ስራዎች እንደ ምሳሌ ማንሳት ይበቃል። ፍቅረ ማርቆስ የደረሳቸው ስራዎች በኪናዊ ውበታቸው ከማማር አልፈው ብዙ ቱሪስቶች የሀመርን አካባቢ እንዲጎበኙ በማነሳሳት ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። እኛም ካወቅንበት የብሄረሰቦቻችንን ባህል፣ ቋንቋ፣ ትውፊት እና ታሪክ የወንድማማችነት ማጠናከሪያ፣ የእርስ በራስ መማማሪያ እና የውብ ኢትዮጵያዊነት ማጎልበቻ ከማድረግ አልፈን ትልቅ የሀገር ገቢ ማመንጫ አውታሮች ልናደርጋቸው እንችላለን።🙏 ----- ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡🙌 @musictube 🇪🇹 #fyp #ጎሳዬ_ተስፋዬ #ልጅነት #musictube369 #ethiopianmusic

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 23 January 2026 21:01:49 GMT
336629
21290
163
1655

Music

Download

Comments

jusus231732
ŀøĝø§ :
ሙዚቃው እኮ በኢንትሮ ብቻ ጨርሶታል ኤላ🥰🥰
2026-01-24 04:57:49
135
kyrix20.1
𝐊𝐘𝐑𝐈𝐗🦇 :
2026-01-24 11:01:59
92
loss_proof_trader
! :
2026-01-24 10:12:00
48
music_isbetter_thenhuman
𝙢𝙖𝙧𝙞𝙤 𝙠𝙖𝙧𝙩 :
evangadi is the difference album ግን 1994/1996?🤔
2026-02-03 20:48:08
0
fikadtiogft
Tina :
ወይኔ የልጅነቴ ዘፈን🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-01-24 17:12:34
10
user9803151623034
Alhamdulillah :
አረ ሙሉዉን
2026-01-30 17:53:00
3
abdu.king1
𝑧𝑖𝑦𝑎𝑑 𝑚 :
2026-01-24 19:50:05
13
marlgn53
Maru :
2026-01-24 14:39:26
11
ysky_angel24
yoni art🎭 :
በህይወቴ አንደኛ የምለው ዘፈን ነው🥺🥺
2026-03-02 20:34:48
6
maryamn403
❤️‍🩹🥀🇦🇹🍫 :
wow bexam dsyilali birta 👏👏👏
2026-01-23 21:09:34
5
liverpoo484
Messi 10 :
2026-01-26 04:50:25
5
itzfir5
⚡fira 🔱 :
Weyne lejenet 🥺☺️
2026-02-06 14:03:12
3
ermiyas_t
Ermiyas_t :
ela x gossaye 🥰🎶🎵👌✌️
2026-01-24 06:52:42
10
glossyyy..697
Ruth :
He sent me this 🥺
2026-01-27 13:14:05
3
hereki1
MARMOUSH 👑🔥🔥 :
🥰❤🥰
2026-01-24 11:11:42
4
hasnt553
Asuu🧕 :
2026-01-26 11:27:05
2
dani.1996t
daniel :
🥰🥰🥰🥰🥰1995
2026-01-27 08:25:42
4
sami_tofik5
S A M I :
I can’t 😭
2026-01-24 17:17:29
2
abdiabera16
A.B.D.I. :
it's not just intro but its soulfullllll intro by ella
2026-01-24 10:56:07
2
devo4300
devo :
2026-02-07 09:40:48
2
itsbeki3
❎no Name :
2026-01-25 07:22:42
1
allhyee
allhyee :
2026-02-05 10:20:53
1
zahra33103
የኔ እናቴ💗❤💌 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-01-24 08:11:13
1
aggdhdhd
aggdhdhd :
what the intro🙌
2026-03-08 08:02:58
0
abenezermengistu4
abenezer⚓️ :
የሚሳም ተራራ'እሳ?....ግን በጣም ወደድኩህ የምር🙏🙏🙏🙏 ፍቅረማርቆስ my fav ደራሲ🥰🥰🥰🥰
2026-02-19 20:24:08
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About