@musictube369: 'በፍቅርሽ መያዜን' 🤌🥵 ✍️ግጥምና ዜማ ደራሲ፣ ድምፃዊ የሙዚቃ አቀናባሪ አንጋፋው ሁለገቡ የጥበቡ ሰው ተስፋዬ ለሜሳ💔 ✨ውድ ቤተሰቦቼ የዛሬው ባለታሪካችን ተስፋዬ ለሜሳ የምድር ጦር ሙዚቃ ክፍልን ገና በላጋ ዕድሜው ተቀላቅሎ በድምፃዊነት ሙያ ጀመረ፤ ተስፋዬ በጣም የሚያምርና ቀጭን ድምፅ ነበረው ምድር ጦር እያለ ስለ ሙዚቃ፣ ስለ እንቁጣጣሽ፣ ስለ ሀገር የራሱን ድርሰቶች ተጫውቷል... ~ውቢት ኢትዮጵያ በማለት ስለ ኢትዮጵያ በአድናቆት አዚሟል ~ ስለ ሙዚቃ * ፍጥረት የሚወድሽ ሙዚቃ በዚህ ዓለም ላይ ሙዚቃ ውብ እንደ ጨረቃ ድንቅ እንደ ፀሐይ ምነው ባላየሁሽ በቀረብኝ ኖሮ ነፍሴ ሳትወጣ አትቀርም ዘንድሮ...በማለት ለሙዚቃ አዚሟል ~ስለ እንቁጣጣሽ *እንቁጣጣሽ እንኳን ደህና መጣሽ በአበቦቹ በወፎች ታጅበሽ....በማለት አዚሟል... ጋሽ ተስፋዬ ለሜሳ ምድር አዲስ አበባ ብዙም ሳይቆይ ድምፃዊነቱን ባልታወቀ ሁኔታ አቁሞ ወደ ሐረር ተዘዋውሮ በምሥራቅ ዕዝ አሰልጣኝነት ሲሰራ ቆይቷል። ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ተምልሶ ውስጡ የነበረውን የሙዚቃ ፍቅር ለበርካታና ታዋቂ ድምፃውያን ድርሰቶቹን መስጠት ጀመረ፤ ከነዚህም ውስጥ በጥቂቱ.. ለጋሽ ጥላሁን *ያቺ ቆንጆ ጥርሰ በረዶ ናት *አካል አይንሽን ጣል አርጊብኝ *ፈልጌ አስፈልጌ *እቱ ገላ እቱ ገላ ገላ *የምወድሽ ፍቅሬ የአላንቺ ማን አለኝ *አስታውስሻለሁ *ሕብረት *ያስብኩት ተሳካ *የህይወቴን ተስፋ ፍቅሬን አጣዋት *ምኞት እኮ ሕልም ነው *ፍቅር ቤቷን ሰርታ *ከአንቺ ጋር ካልሆነ *ብዙ ጊዜ አለፈ *ካሰኘሽ *አጉል ነው ለጋሽ መሐሙድ *ጉብል የሀገሬ ልጅ ውብ አይናማ *የድሬ ልጅ ነች የከዚራ *ንሽቴ *ማሬ ገላ *ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም ለጋሽ ሙሉቀን *እኔና አንቺ ሆነን በተለይ ያረግነው *እንደምነሽልኝ እንደምነሽዋ አልማዜዋ ለአስቴር *አማላጅ ሳይቀረኝ መላዕክተኛ ላኩኝ *ሙናዬ ሙናዬ ለኤፍሬም * ዛሬ የጋበዝኳቹ 'በፍቅርሽ መያዜን በአንቺ መቸገሬን ' *አንቺ ልጅ ነይልኝ በሞቴ መውደድ አካላቴ ለነፃነት *ይላል ዶጁ ይላል ዶጆ ፏፏ ይላል ዶጁ *አይናማዬ መውደድ ከተማዬ አይናማ ሰው ልቤን አትመልሰው.... *ለኤልያስ ተባባል የመጀመሪያ ሥራዎቹ የሆኑትን እቱ ምን ጠፍቶ ሀገራችን ፍቅርሽ ይዞኛል ምን ይሻለኛል። አንጋፋው የግጥምና ዜማ ደራሲ በተለያዩ ወቅት ከሰራቸው ከዜማና ግጥም ባሽገርም የሙዚቃ አቀናባሪም ነበረ የተለያዩ ነባር የባህል ስራዎችንም ወደ ዘመናይነት በመቀየር ሰርቷል ከነዚህም ውስጥ የሙሉቀን እንደምነሽልኝ እንደምነሽዬ አልማዝዬ፣የነጻነት አይናማይ መውደድ ከተማዬ የድሮ የተለያዩ ሰዎች የሰሩትን ስራ እሱ አስተካክሎ ጊዜ አይሽሬ አድርጎ ሰርቷቸዋል ተስፋዬ ለሜሳ እንደ ዘመኑ የጥበብ ሰዎች በወታደራዊው መንግስት ብዙ እንግልት ፣እስር ደርሶበታል በተለይ ደሞ በጥላሁን ገሠሠ ፈልጌ አስፈል በሚለው ስራ ዘፈኑ በሃገራትን ቀደምት ሚውዚክ ቪዲዮ ከተሰራላቸው ስራዎች መሐል አንዱ ነው ዘመን አይሽሬም ነው ታዲያ ዘፈኑ የተሰራበት ዘመን ድሞ የደርግ ስርሀት ሁሉን ነገር ከአብዮቱ አንጻር በሚያይበትና በሚመዝንበት ጊዜ ነው ዘፈኑ መጀመሪያ ሲሰራ ልዝናና ስወጣ ብቅ ብል በማታ የለቺም ካሳንቺስ እሷ መች ተገኝታ ነበር የሚለው ታዲያ ይህ ሀሳብ በወቅቱ በነበሩ እወደድ ባይ ካድሬዎች ተቃውሞ ገጠመው እንዴት በሶሻሊስት ዘመን ርእዮት አለም ምንድነው ለአንዲት ሴት ይህን ያህል ቦታሰጥቶ ያለስራ መንገላወድና መንከራተት በሚል ተጽኖ የግጥሙ ሀሳብ ከስራ ስወጣና ከስራ በኋላ የሚሉ ሃሳቦች ገብተውበት እንዲህ ተዜመ .... አየናት መርካቶ ሲሉኝ ትላንትና ከስራ በኋላ አጣኋት ሄድኩና ትገኛለች ብዬ ፒያሳ ደረስኩኝ አይኔ እንደናፈቃት ሳላያት አደርኩኝ እየተመላለስኩ ላገኛት ሞከርኩኝ ሰንጋተራ ባጣት ፍል ውኃ ቀጠልኩኝ ከስራ ስወጣ ብቅ ብል በማታ የለችም ካሳንቺስ እሷ መች ተገኝታ... እንዲል ተደርጎ ተሰራ...። ጋሽ ተስፋዬ አንተ ብታልፍም ሥራዎችህን እያዳመጥን ስናስታውስህ እንኖራለን። ነፍስ ይማር ብለናል💔 ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🙌🙏 @musictube 🇪🇹 #fyp #ethiopianmusic #musictube369 #አብዱኪያር #በፍቅርሽመያዜን
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Region: ET
Tuesday 27 January 2026 20:48:15 GMT
Music
Download
Comments
bubuye :
2026-01-28 06:15:43
30
🇦🇱𝑑𝑗.𝑎𝑏𝑒𝑛𝑖🇦🇱 :
2026-01-28 17:53:08
3
#ÖŹÀ@08 :
2026-01-28 08:17:15
10
𝗬𝗼𝗻𝗮𝘀 𝗦𝗵𝗶𝗺𝗲𝗹𝗶𝘀 :
2026-01-28 10:48:39
7
[𖣂Ň€bæ𖣂 geykume𖣂} :
2026-01-28 07:42:33
4
Mi$Baህ ከ ☪️♏✅ :
2026-01-28 14:29:38
3
0_six :
2026-01-28 08:42:45
1
𝐌. 𝐒.𝐝𝐮𝐧𝐞𝐠𝐰𝐚🇱🇾🇱🇾 :
abd kantibachin👑👑
2026-03-01 21:51:36
1
MÅRK 🧔 :
2026-01-31 09:07:27
1
مبارك 🇪🇹 :
✌
2026-01-28 12:15:54
1
îŝ𝖒æ𝖑𝖑💱💲 :
first
2026-01-27 20:52:43
6
Danny dan :
✌️🔥
2026-02-06 20:21:54
1
THE GOD FATHER, :
2026-01-28 07:48:38
1
🇪🇹Lij fuade ❤🔥✅ :
ooo😁
2026-02-09 13:57:14
0
#ÖŹÀ@08 :
2026-01-28 08:17:09
2
bubuye :
2026-01-28 06:15:14
6
bubuye :
2026-01-28 06:15:27
4
bubuye :
2026-01-28 06:15:19
2
simon :
2026-01-27 21:58:43
12
አዳማ ናዝሬት ዳጊ ፍሪጅ ቤት :
abd king
2026-01-30 19:27:03
0
✳ተውህቦ✳ :
wag 1
2026-02-14 00:07:04
0
Nebiyu 21 :
2026-02-11 15:50:37
0
Mikiyas :
ያበደ👍👍👍👍👍👍👍👍
2026-02-11 16:17:58
0
Shimeket 5 :
ከ ኤፍሬም ይልቅ ይህን Rmx ነበረ በደምብ የያዝኩት ኦርጅናሉ ግን የኤፍሬም ታምሩ ነው😅
2026-01-28 16:39:13
4
Julian Tefera :
ኤፍሬም ታምሩ
2026-01-29 15:44:42
1
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm
homepage.