@musictube369: ብሌን🥹💜 🩶በሕይወቴ ዘመን በደስታ በሀዘኔ ሁሉን ያየሁብሽ ብሌኔ ነሽ የዓይኔ 🖤🖤 ሙዚቃዎች የምትወድባቸው ብዙ ኣይነት መንገድ አለ ። አንዱ ግን ስሜቶች እየቀያየሩ ከፍና ዝቅ በማድረግ ቀልብ የሚስቡ ቃላትን መርጠው የልብን የሚያደርሱ ውብ የፍቅር ሙዚቃዎች ናቸው ዛሬ የጋበዝኳቹ የተወዳጁ የፀሐዬ ዮሐንስ 'ብሌን' አንዱ ነው ከእናት እስከ ልጅ ከፍቅረኛ እስከ የትዳር አጋር ለሁሉም እንዲሆን በዶክተሩ ታላቁ መሰለ ጌታሁን የተቀመመ መድኃኒት 🤒 ውድ ቤተሰቦቼ ዛሬም የፍቅረኞችን ቀን የማከለ ሌላ ስጦታ የሚሆን ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃ ከፀሐዬ እና አበጋዝ ጥምረት ጋር በ1999 ከወጣው 'ሳቂልኝ' አልበም ላይ መርጬ ይዤላቹ መጥቻለሁ ፀሐዬ የሁለት ትውልድ ነፀብራቅ ጨዋታ አዋቂ ድንቅ ጥበበኛ ሆኖ ሳለ የልህቀቱን ጣሪያ ሊያሳየን ከአበጋዙ ፊት አውራሪነት ከነ አማኑኤል ይልማ ከነ ሞገሰ ተካ መሰለ ጌታሁን ሀብታሙ ቦጋለ ዘውዱ በቀለ አይነት ድንቅ የሙዚቃ ሰዎች ጋር ተጣምሮ ከወላይትኛ እስከ ትግርኛ ከፍቅር እስከ ባህል ከሀገር አስከ ፈጣሪ እየወሰዱ ጥበብን ወልደው በዚህ እንከን አልባ አልበም እጃችን በአፋችን አስጭነውናል🙏 የፀሐዬን ስራ አንዱን ከአንዱ ማወዳደር ለብዙ የሙዚቃ አፍቃሪያን ሲያዳግት ይታያል ፡፡ እውነት ነው ሁሉም በሚባል መልኩ የፀሐዬ ሙዚቃዎች ዘፈን እንዴት መዘፈን እንዳለበት የሚያሳዬ ምርጥ ስራዎች ናቸው ፡፡ " ጥንድ ጥንድ ሆነው ሲሄዱ ባይ ሳልዋሽ ያይኔ ሲሳይ ቀናሁ በሰዎች ላይ ዛሬም ሳላይሽ ላድር ነው ወይ እባክሽ ነይ " እርግጠኛ ነኝ ዘፈኑን ካወቃችሁት በውስጣችሁ እያዜማችሁት ነው ፡፡ " ተበድዬስ ይቅርታ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ እንኳን ልልክ አማላጂ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጂ" አስታወሳችሁት ... ? ምን አይነት ውብ ሙዚቃ ነው ፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ ፀሐዬ ያልተዘመረለት ድንቅ ሀገር ወዳድ ከያኒ ነው ! ቢባል ቢያንስበት እንጂ አይበዛበትም 🙏 ስለ ጀግንነት ፣ ስለ ፍቅር ፣ መተሳሰብ ፣ በጎነት ፣ ሁሉንም የሰራ ከ 10 በላይ አልበም ከነዚህ አልበም በጢቂቱ . 1986 የሐገርሽ ልጅ ነኝ ፣ ፌዘኛ 1978 ገነት የሙዚቃ ቤት /ሎጋ/ ሌሎችም ያሉበት …፣ ጡር ነው -1979 ፣ ፍንጭቷ -1975 ፣ ሰላም አይለበኝ ፣ ሳቂልኝ 1999 ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን (Golden Era) ከሚባለው ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በልዩ ጉልበት እና ተወዳጅነት የዘለቀ አንጋፋ የሙዚቃ ዕንቁ ነው። የ"ሳካ" ንጉሥ፡ ፀሐዬ ዮሐንስ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ "ሳካ" (Saka) የተሰኘውን የሙዚቃ ስልት (Rhythm) በማስተዋወቅ እና በስፋት በመጠቀም ይታወቃል። ዘፈኖቹ አድማጭን የማነቃነቅ እና የመደነስ ጉልበት አላቸው። ልዩ የድምፅ ቀለም: ድምፁ በተፈጥሮው ኃይለኛ እና ልዩ የሆነ የድምፅ ርግብግብ (Vibrato) ያለው ሲሆን፤ ይህም ከሌሎች ድምጻውያን ይለየዋል። የመድረክ እንቅስቃሴ: በመድረክ ላይ በሚያሳየው ጉልበታማ (Energetic) እንቅስቃሴ እና ልዩ አለባበስ ይታወቃል👌😎 እስቲ መለስ ብላቹ የሱን ሙዚቃዎች እንድትሰሙት ልጋብዛቹ እና ላብቃ🥰 ጥቂቶቹን የረሳችኋቸውን ልጠቁማቹ፡- "የበረሃ ሎሚ" (እጅግ ተወዳጅ ስራው) "ሳካ" "እምቢ አልልም" "ወይ አዲስ አበባ" "ትዝታ" (በራሱ ስልት የተጫወተው) "አይዞሽ ሀገሬ" ....በተረፈ እኔም ብዙ የሱን ሙዚቃዎች እዚህ ስለሰራኋቸው ፈታበሉ🥰 ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡🙌 musictube #fyp #ፀሀዬ_ዮሀንስ #ብሌኔ #musictube369 #ethiopianmusic
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Region: ET
Friday 13 February 2026 20:49:27 GMT
Music
Download
Comments
radu🥰tadlele💞 :
le enate 💞
2026-02-14 05:36:43
77
Atnasiya 🍫🍫 :
caption ♥️♥️♥️♥️
2026-02-14 18:47:05
20
⚡️SURAFEL❄️ :
be ezi seat yhe zefen ke enat wchi manm yemikerb yelem 💯
2026-02-14 19:14:48
7
henok molla official :
ሞገስ ተካ ይችላል ነው የምልህ 👏
2026-02-14 01:53:12
20
𝕓𝕖𝕞𝕟𝕚💜 :
እናት አለሜ
2026-02-14 07:47:29
6
Anna ♾️ :
2026-03-25 06:58:54
1
😇😁 :
mom❤️
2026-03-28 18:14:32
5
@BMYE18 :
aleww🥰
2026-04-01 16:22:33
1
helen 1999 :
for ma gramama
2026-02-14 21:47:30
2
betelehem furniture :
ex neber yegabezeg yezaren ayaregewena
2026-02-15 13:31:27
1
Yarsema1 :
For my mom ❤️🥰
2026-02-14 19:46:34
4
dawitp :
ብሌኔ ብሌኔ
2026-02-14 19:42:59
1
Che :
my fav 🥰
2026-02-13 21:32:18
7
BETI🍁 :
"enate ''❤❤❤❤
2026-02-14 20:26:50
1
ብሌን🫐 :
weye🥰
2026-02-15 08:39:32
1
@Abaye :
wow wow 🥰🥰🥰🥰🥹🤔🤔🤔✌️✌️👏👏👏👏❤️❤️❤️❤️
2026-02-15 05:46:36
2
mercyee🦋 :
@sarina🥺
2026-02-14 13:48:24
0
blen ♌ :
waye😊
2026-02-15 19:57:47
1
Nazu (ባትያ)CR7🍫 :
ከእናት በቀር ምቀርበው የለም
2026-02-14 17:57:25
8
R :
እህ ተወኝ እንደውም ናፍቆኛል እንኳን ዘፈኑን ሰምቸ የኔ ውድ አባት🥺🥺🥰
2026-02-14 11:29:28
8
king :
lenate egabzatalew🤩🤩🤩
2026-04-14 11:30:10
0
feven ye selale lij 🦋🦋😘 :
mom my😘😘😘❤️❤️❤️
2026-04-16 10:08:19
0
🇪🇹Seyya :
Yane man 🥰🥰🥰
2026-05-12 16:29:52
0
ማሜ ሀበሻ🇪🇹🇪🇹 :
አያየችው ነው
2026-02-16 00:01:47
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm
homepage.