@haylemaryam29: #እስቴ_መካነ_ኢየሱስ እስቴ መካነኢየሱስ ከአዲስ አበባ በ672 ኪ/ሜ ከባህርዳር በ112 ኪ/ሜ ከጎንደር በ226 ኪ/ሜ ርቀት የምትገኝ ጥንታዊና ታሪካዊ ከተማ ነች። በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በንግስተ ሳህላ እንደተመሰረተች የሚነገርላት እስቴ መካነ ኢየሱስ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ፀጋዎች እንደ ገነት ተክል የተበረከተላት የንግስት ሳህላ የብር ሙዳይ፥ የወርቅ ወቄት ናት። እስቴ የሚለው ስም "እስቲ እንያት" ከሚለው ከንግስቷ ቃል የወጣ ሲሆን መካነ ኢየሱስ የሚለው ደግሞ ከታላቁ ገዳም ካልዕ እስክንድርያ ደብረ ሀይማኖት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ጋር ተያይዞ የመጣ የግዕዝ ስርዎ ቃል ነው። መካነ ቦታ ሲሆን የኢየሱስ ቦታ ማለት ነው። እስቴ መካነ ኢየሱስ በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ ካሉት ወረዳዎች መካከል በቆዳ ስፋቱ አንደኛ ሲሆን ወረዳው ከሁለት እስኪከፈል ድረስ 12 ወረዳዎችንና 3 የአማራ ክልል ዞኖችን የሚያዋስን ትልቅ የቆዳ ስፋት ያለው ወረዳ ነው። እስቴ መካነ ኢየሱስ በክልሉ ብሎም በሃገራችን ካሉ በርካታ የተፈጥሮ እና የሰው ሰራሽ ሃብት መገኛ የሆነ ድንቅ ቦታ ነው። ለምሳሌም የአንበሳ ቅርጽ ያለው የእስቴ ዴንሳ ተራራ እጅግ ግሩም ውበት ከተጎናጸፈ ደን ጋር ዛንጨፈናን ጨምሮ... ካልዕት እስክንድርያ ደብረሃይማኖት መካነ ኢየሱስ፥ ዋሻ ማርያም፥ ባለ 14 ጉልላቱ ባለ 14 ቅኔው ታላቁ ገዳም ቆማ ፋሲለደስ፥ ብር አደጌ፥ ገንተኛ ሚካኤል፥ ሳጋ ወለቴ ገዳም፥ ገዳመ ኢየሱስ፥ ጎኖ ገብርኤል፥ ሸንቆሌ አማኑኤል፥ ዳት ጊዮርጊስ፥ አጎና ማርያም፥ ጅብ አስራ ማርያም፥ ኮስተት ዮሐንስ፥ ዳጉት ኢየሱስ፥ አበርጉት ሚካኤል(አብ አርጉት)፥ የበቁ አባቶችና የሚራመድ ዛፍ የሚገኝበት ዝጎራ መድኃኔዓለም ገዳም፥ በገብስ ምርትና በቱሪስት መስህብ የሚታወቀው ጉና ተራራ፥ ታሪካዊ የሆነው ነገርግን ትውልዱ ታሪኩን እንዳያውቅ የተዳፈነው... አባቶቻችን ከ1928 እስከ 1935 በነበረው የኢጣልያ ወረራ ወቅት ጣሊያንን አይቀጡ ቅጣት የቀጡበት ቁት አቡነ አረጋዊ(የአምባ ተራራ) በተመሳሳይ ጢንጫ ማርያም፥ ማታርጌ ጊዮርጊስ ወዘተ በስም ጠርቸ የማልጨርሳቸው ድንቅ ጸጋ የተቸረው ሃብታም ህዝብ ነው። የእስቴ ህዝብ። ወረዳው ከዞን ከተማ በ52 ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን ለክልሉም ሆነ ለሃገራችን መተንፈሻ ሳንባ ነው ቢባል ያለምንም ማጋነን እውነታውን የሚገልጽ ገዥ ሃሳብ ነው። የእስቴ መካነ ኢየሱስ ህዝብ በታታሪነቱ፥ በስራ ወዳድነቱ፥ በወንድነቱና በሀገር ፍቅሩ በድፍን ኢትዮጵያ የሚታወቅ ድንቅ ህዝብ ነው። የሃይማኖት አባቶች፥ መምህራኖችና ሰባኪያን የፈለቁበት፥ ተጽዕኖ ፈጣሪና ባለሃብት ግለሰቦች የወጡበት ትልቅ ህዝብ ነው። ከራስ በጌምድር ጉና ተራራ መካነ ኢየሱስ ረቻ ገብርኤል አንስቶ እስከ አባይ በረሀ ቆማ፥ የሾ፥ ሸንበቆች፥ ደምባ፥ ይዶግ እንዲሁም ድፍን ቄጣ፥ ጥናፋና ምክሬ በሚያመርተው ነጭ ጤፍ የኢትዮጵያን ህዝብ ይመግባል። የእስቴ ህዝብ ከነጭ ጤፍ ውጭም የተለያዩ እህሎችን ያመርታል። ኑግ፥ ተልባ፥ ገብስ፥ በቆሎ፥ ዳጉሳና ድንች በተለይም ደግሞ ከቆማ እስከ አባይ በረሀ ባሉ ቦታዎች ውስጥ እንደ ጥጥ፥ ቦለቄና ሰሊጥ በስፋት የሚመረትበት ድንቅ የወርቅ ምርት ባለቤት ነው። መልካም ዕለተ ሰንበት!🙏 *በፌስቡክ - https://www.facebook.com/hayle.maryam.31 *በቴሌግራም - https://t.me/haylieZ እሁድ - የካቲት 8/2018 ዓ.ም #creatorsearchinsights #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #2026 #viral

haylemaryam
haylemaryam
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 15 February 2026 07:34:10 GMT
30859
1958
169
167

Music

Download

Comments

eyerus.nega2
Jeri 2123 :
my estie🥰🥰🥰🥰
2026-02-17 19:44:08
1
selam.selam487
🎼ኑረሽልኝ እይኝ🤲𝐌𝐎𝐌🌍🕊️የ¹⁶ˡⁱʲ :
ፈጣሪ ሰላሙን ይመልስልን🙏♥️
2026-03-28 09:23:21
2
user83533478138446
የስላሴ ልጅ :
ሀገሬሀገሬ
2026-02-17 19:23:12
2
reduye1
reduye1 :
አገሬ አገሬ....🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-02-17 03:36:27
2
user2036269351215
tsige :
ሀገሬ
2026-03-14 12:11:58
1
user660370380208
[email protected] :
ውቢቷ ሀገራችን
2026-02-17 14:52:54
2
abeba.goniderewa
አበባ ብቸኘዋ 💓💓 ❤️❤️ :
ሀገሬ ሰላምሽ ይብዛ🥰🥰🥰🥰🥰🥰👍👍👍👍
2026-02-17 18:21:54
2
user8434123594574
እህት የላሊጋዋ የማርያም ልጅ :
የጀግና ዘር አገሬ🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-02-24 20:10:50
1
menorbnathodnew16.19
መኖር በእናት ሆድ ነው 16.🇪🇹19🇪🇹 :
አይ ሃገሬ
2026-03-11 07:22:30
1
.4469316
Koczka Sára :
ሀገሬ
2026-02-19 03:56:03
2
user3222173148523
ገብረ መስቀል የእስቴው :
ውቢቱ ሀገሬ 💓💓💓💓💓💓💓
2026-02-18 05:37:46
1
selam_alemnew
ፍቅርን ከክርስቶስ ትትናከማሪያም✝️✝️✝️✝️ :
💪💪💪💪💪💪እስቴ
2026-02-21 18:03:26
1
robi_1621
Rø Bi 🦅 :
hagere🥰
2026-02-18 19:14:23
1
mekibaba615
Nataneam😍 :
Jegnaye💪
2026-02-21 05:53:50
1
1selam41
selam 27🙏🙏 :
my home🥰🥰🥰
2026-02-17 06:17:20
1
elsa.ya04
elsa &ya :
ሀገሬ ሰላምሽ ይብዛ
2026-02-20 14:37:47
1
matewal012
ማስተዋል :
ሀገሬ
2026-02-22 21:15:51
1
hosaena24
HOSAENA 🦅 :
እስቴ💪🏽💪🏽💪🏽💪🏽
2026-02-19 06:51:55
2
yezi422
ፅናት የድንግል ልጅ :
ሃይልየ😘😘
2026-02-27 18:37:55
1
kinde.bikes
Kinde Bikes :
i love more my country
2026-02-20 07:17:00
1
netsi8841
netsi :
እምየ ሀገሬ 🥰🥰🥰
2026-02-20 19:42:21
1
user8052577437086k
user8052577437086kindinew. :
እሰቴ.መልካም.ሀገር
2026-02-17 15:40:54
2
girma.gitora
mekdes gondre :
ዋው፣አገሬናፈቀኝ
2026-02-25 04:43:03
1
kalkidankindalem
kalye :
የትዉልድ ሀገሪ
2026-02-22 12:34:48
1
user21tadela
tadela :
ሀገሬ ሰላምህ ይብዛ
2026-02-24 04:33:56
1
To see more videos from user @haylemaryam29, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About