@yirga.seyoum: የካቲት 14 ቅዱሱ አባታችን አቡነ አረጋዊ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን እንኳን ለፃድቁ አቡነ አረጋዊ ወርሐዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን አሜን ቅዱስ አቡነ አረጋዊ አረጋዊ ማለት ያረጀ የሸመገለ አዋቂ ትልቅ ሰው ማለት ነው:: አባታችን ይህ ስም የተሰጣቸው ገና ልጅ እያሉ ነበር ለምን ይሆን? አባታችን አቡነ አረጋዊ ከተሰሐቱ ቅዱሳን ከሮምና ኤሽያ ከመጡት ከ9 ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉስ ነበር እናታቸው ንገሰት እደና ትባላለች:: በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው:: ፃድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅና ንግስት አድና ይባላሉ:: የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው:: የቅዱሱ አባታችን ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው:- 1 ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው:: 2 በበርሃ ገብረ አምላክ ተብለዋል:: 3 በኢትዮዽያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ:: _ አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መፃሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ:: _ በዚያም በገዳመ ዳውናስ ግብፅ የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል:: _ ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል:: _ የት? ልሒድ ብለው ሲያስቡም መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው :: _ ተመልሰውም ለስምንቱ ባልንጀሮቻቸው ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ፀንታ የምትኖር ብለው ከስምንቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ:: _ በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል:: _ በቤተ ቀጢን አክሱም ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል:: _ ለሥራ በተለያዩ ጊዜም አቡነ አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል:: _ በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት:: _ የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ (60) ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል:: _ እንደ ወጡም>ሐሌ ሉያ ለአብ "ሐሌ ሉያ ለወልድ "ሐሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል:: በዚህም ቦታዋ ደብረ ሃሌ ሉያ ተብላለች:: ፃድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው ስድስት ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል:: _ ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም የኢትዮዽያ መነኮሳት አባት ይባላሉ:: _ አቡነ አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋ:: ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ:: _ በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች:: _ ፃድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በገዳሙ በስተምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል:: ጌታም አስራ አምስት ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአባታችን ቅዱስ አቡነ አረጋዊ ረድኤት በረከታቸዉ ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን አሜን አሜን።

Yirga Seyoum
Yirga Seyoum
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 21 February 2026 04:48:18 GMT
1283
138
6
7

Music

Download

Comments

featana
featana :
😏😏😏
2026-02-21 04:49:37
1
getu.bezabehe
Getu Bezabehe :
😁😁😁
2026-02-21 06:37:58
1
amanuel.getachew05
amanuel getachew :
🥰🥰🥰
2026-02-21 19:04:44
0
user4032842826103
user4032842826103 :
😂😂😂
2026-02-25 08:16:37
0
reje.sh26
122127 :
🙏🙏🙏
2026-02-21 11:06:47
0
user49411407739321
ኪያ ለገሰ :
🤲🤲🤲🤲🤲🙏🙏🙏
2026-02-21 07:05:44
1
To see more videos from user @yirga.seyoum, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About