@musictube369: ሰንደል ገላዬ🤌🙂‍↕️ ✍️አንዳንድ ጊዜ 'ዘመን ውለታ ቢስ ይሆን?' እላለሁ። ላደመቁት፣ ለሆኑለት ሁሉ ቁብም የለው? አነዚያን አጋፋሪዎቹን ለምን ይረሳል?..ውበቶቹን! በየዘመናቸው የገነኑ ልክ እንደ ሽቶ መዓዛ ቆይተው የተረሱ አድምቅውን የረሳናቸው እንዳልነበሩ በሌላ የተካናቸው ያዋሩን፣ ያጫወቱንና ያዜሙልን። የጊዜያቸው ምስጉኖች ነበሩን። በተለይ ዜመኞቹ! የወረት ነፋስ ሳያጠፋብን፣ በራስ ግዴለሽነት በድርሳናት ስንፍና ከትዝታ ሳይጨለፉ የጠፈፉ። ወዴት ሄዱ?.. አሉ?..አለፉ?..የትና ማን ዘከራቸው? የሚገርማችሁ በሞት የተለዩትን'ንኳን ለይተው የሚያውቁ ጥቂቶች ናቸው። ያዩዋቸው፣ የጠየቋቸው አብዝቶ ጥቂቶች ናቸው🥺ላንሳቸው እስቲ🙏 ✨ውድ ቤተሰቦቼ እስቲ ዛሬ ከጋበዝኳቹ ከወረታው ውበት ልጀምር አሳድገሺኛል በማር በወተት ኢትዮጵያዬ እማማ ምድራዊ ገነት🥰 በሚለው እጅግ የብዙዎችን ትዝታ በሆነው አንጀት አርስ ሙዚቃው "ሾፌርእወዳለሁ ስትዪኝ ሰምቼ ሞቼልሽ ነበረ ብስኪሌት ነድቼ " በሚለው ግጥሙ የማይረሳው ወረታው ውበት ነው። ወረታው ተስረቅራቂ ድምጽ የነበረው፡ ለየት ባለ የግጥም አገላለጹ የሚታወቅ ነበር። " ከደን የወጣች አርጩሜ 'ምትመስል ጀግና እንደ ተስቦ የምታሰለስል " የምትለው ግጥም ያለችባት ዘፈን በጣም ደስ ትለኛለች። ወረታው ብዙም የካሴት እና የሲዲ ሥራዎች የሉትም!አንድ ከከተማና ከፀሃይ ከብፅአት ጋር ሌላ ከገነት ማስረሻ ጋር ሁለት ሙሉ ሥራዎች ለብቻው ሰርቷል ሌላ ካለ እታረማለሁ። ወረታውን እንዳለ ጌንቦ"ዘፍኖ ራሱ ዝም ሲል ወይንም ከንፈሩን ሲገጥም ድምፁ አየር ላይ እየተርገበገበ ለረዥም ሰአት ይቆያል" ይለዋል ፌድአዌዩ እንደ ብር ማንኪያ ይቆያል ለማለት ቤዝ ባሪቶን ገቢር ቢሰጠው በደንብ የሚጫወተው ይመስለኛል ጆሽዋ ቶማስ ቶማስ ስቲዋርት ....የሚያስከነዳ ድምፅ👌🥰 ▪▪▪ ሌላው በኋላ ከመጡ ዜመኞች የሆነው ደግሞ ተስፋዬ ወርቅነህ ነው። ተስፋዬ ወርቅነህ ( ከሚላ ነይ ከረሜላ ) በሚል ዘፈኑ በ1992 አካባቢ ብቅ ያለ የተለየ ድምጽ የነበረው ድምጻዊ ነበር። " አበጀሁ ወደድኩሽ እኔስ እንኳን እንኳን ፍቅርሽ አይደለምወይ የጣለብኝ ድንኳን " በወጣትነቱ በሞት ተለየ። ሞቱ ብዙዎቹን የሙያ ጓዶቹን ያጎደለ ከባድ ሃዘንም ላይ የጣለ ነበር። አበበ ተሰማ ነይ ብራ፣ዳማ ቡሎ፣ልወዝወዘው በግሬ የድምፁ ጉልበት! ሌላው የሚገርመኝ ነገር ከአበበ አማርኛ ሲዘፍን ኦሮሞና ኦሮምኛ የደረሱበት ደርሶ የሚያውቅአይመስልም፤ኦሮምኛ ሲዘፍን ደግሞ ጆሮውን ቢቆርጡትም አማርኛ የሚሰማ አይመስልም ሁለቱንም በየተወላጁ ቅላፄ እንዴት እኩል እንደሚያስኬዳቸው ለማድመጥ ከፈለክ ቢሌቦም ቢሌን ከ ያም ሎጋ ጋር እያዛነቅኽ ማድመጥ ነው! ጎሃፅዮን ተወልዶ የማደግ በረከት! ቻላቸው አሸናፊ 4ቱንም ቅኝቶች መዲናና ዘለሰኛን ጨምሮ በማሲንቆም ሆነ በዘመናዊ ባንድ ታጅቦ ሰርቷል።ድምፁ ነጎድጓድ ነው!በቃ ልዩ!የኢሠፓ ምስረታ ዝግጅት ላይ ያቀረበው ሥራውን ይዘን እንኳን ለበርካታ አመታት ሥራዎችን ማበርከቱን ብንገምትም ከብርቱካን ዱባለ ጋር የሠሩትን የባህል መዘክር ግን ማስተርፒሱ ይመስለኛል በሷ ቅልጣን በሱ ማስገምገም 🥰 ሌላው በኋላ ከመጡ ዜመኞች የሆነው ደግሞ ተስፋዬ ወርቅነህ ነው። ተስፋዬ ወርቅነህ ( ከሚላ ነይ ከረሜላ ) በሚል ዘፈኑ በ1992 አካባቢ ብቅ ያለ የተለየ ድምጽ የነበረው ድምጻዊ ነበር። " አበጀሁ ወደድኩሽ እኔስ እንኳን እንኳን ፍቅርሽ አይደለምወይ የጣለብኝ ድንኳን " በወጣትነቱ በሞት ተለየ። ሞቱ ብዙዎቹን የሙያ ጓዶቹን ያጎደለ ከባድ ሃዘንም ላይ የጣለ ነበር። በተጨማሪም፦ ወንድሙ አማረ ሙሉቀን አለነ ስዩም ዘውዴ ስፈልግ አያሌው ሰርጎለም ተገኝ ጌታቸው ስሑል ( አውቶቡሰይ ) አበበ አበሹ ( ታርታሌ ቢሻን ሃሮ ) የምታውቁትን የምታስታውሱትን አጋሩኝ በህይወት የሌሉትን ነፍስ ይማር🙏 ያሉትንም እድሜ እና ጤና ይስጥልኝ ክበሩልኝ እያልኩኝ ለዛሬ አበቃሁ ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡🙌 @musictube 🇪🇹 #fyp #ወረታውውበት #musictube369 #ሰንደልገላዬ #ethiopianmusic

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 22 February 2026 21:00:15 GMT
34863
1572
29
90

Music

Download

Comments

newaymolla1
neway molla :
Do you think enough credit is given to Mitiku Tefera and his contribution to our music?
2026-02-23 09:39:29
3
abrishlove981
Abrish 03 :
what a song🥰🥰🥰🥰 can anyone tell his name?
2026-03-10 07:35:03
2
mele_man19
መሌ ማን_የ'ናቱ ልጅ :
እዚህ ካሴት ላይ "አበባ ነው ደጇ: ሸጌ ለወዳጇ" የሚለው ሙዚቃ አለህ? ብዙ ጊዜ ፈልጌ አጣሁት!
2026-03-02 16:56:19
1
esubalewtadele21
ES :
ወረታዉ ይችላል
2026-03-05 17:59:49
0
bereketseyoum3
Bekie Arsenal :
ግጥሙ የራሱ የወረታው ውበት ነው
2026-03-02 18:43:26
1
fm4461
F / m 888 :
👌 nice story time
2026-02-23 05:57:42
0
tewodros183
Tewodros183tedy :
እናመሰግናለን 🙏
2026-02-23 04:22:41
1
melesmeles715
Melsew Andualem715 :
🥰🥰🥰
2026-03-11 07:19:54
1
mekbiblove28
mekbib drone 🇪🇹 :
🥰🥰🥰
2026-03-01 13:18:02
1
gebeyewww
yerosn :
🥰🥰🥰
2026-02-28 18:42:06
1
mekbiblove28
mekbib drone 🇪🇹 :
🙏🙏🙏
2026-03-01 13:18:06
1
user57419057720237
Mihiretu waabo :
😁
2026-02-23 22:03:51
1
emanda385
Amanda :
❤️❤️❤️
2026-02-25 12:13:32
1
shorita25
abi bingo :
🔥🙏❤️
2026-02-24 11:05:16
1
chichi.fana
chichi fana :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-02-23 20:07:22
1
1mimi353
Mimi coca :
👌👌👌🥰🥰🥰🥰🥰
2026-02-23 09:01:49
1
user7509278596537
user7509278596537 :
🥰 🎧🔥
2026-02-23 05:17:12
1
jame09094
@Temi fikir Haqeyinawu :
🥰🥰🥰
2026-02-23 07:23:00
1
zehasen
zehan :
❤️❤️👌👌
2026-02-23 12:24:56
1
abebeyadechu
AB በቸርነቱ :
👏👍💕🎶🎵🎶
2026-02-23 14:56:09
0
ms937312
ms olds :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-03-10 08:35:27
0
shewit.211221
Shewit :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-04-18 02:15:18
0
user1327629252156
💎🩸⚜️𝐘𝐚𝐲𝐨 𝐤𝐢𝐧𝐠🤴💎 :
👑👑👑
2026-05-18 20:37:37
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About