@hameretewahedomedia: ታሪክ የሚጻፈው በጽኑ እምነትና በትጋት ነው። መስከረም 9 ቀን 2014 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የባቱ ዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ፤ አባታዊ መሪነት የተቀመጠው ያ መሠረት፣ ዛሬ በባቱ (ዝዋይ) ከተማ እምብርት ላይ በተጨባጭ እየታየ ይገኛል። ይህ የG+7መንታ ዘመናዊ የትምህርት ተቋምና የሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ ግንባታ ልዩ የሚያደርገው ያለ ምንም የባንክ ብድርና የውጭ ዕርዳታ፣ በልዑል እግዚአብሔር ረዳትነትና በቅዱስ ገብርኤል ተረዳኢነት ብቻ እዚህ ደረጃ መድረሱ ነው። ገዳሙ ካለው ውስን አቅም በመነሳት ይህን የመሰለ ግዙፍ ፕሮጀክት ማከናወን መቻሉ የገዳሙን በረከትና የብፁዕነታቸውን ጽኑ ራዕይ ይመሰክራል። ገዳሙ ገዳማውያኑን ከመጠበቅና ወላጅ አልባ ሕጻናትን በፍቅር አቅፎ ከማሳደግ ባለፈ፣ በቃለ እግዚአብሔር የታነጹና ዘመናዊ የአመራር ጥበብን የተላበሱ አገልጋዮችን በማፍራት የቤተክርስቲያንን ልዕልና ያረጋግጣል። ይህ ተቋም ሲጠናቀቅ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በማቀላጠፍ ለነዋሪው ትልቅ ኩራትና የዕውቀት ማዕከል ይሆናል። በአሁኑ የግንባታ ሂደትም ሆነ ነገ ሥራ ሲጀምር ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር የባቱ ከተማን የንግድና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በእጅጉ ያነቃቃል። ወጣቱን ትውልድ በሥነ-ምግባርና በዕውቀት በማነጽ ለሀገርና ለወገን የሚጠቅም ዜጋ በማፍራት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና ይጫወታል። ይህ በባቱ መሐል ከተማ ላይ የሚታየው ድንቅ የግንባታ እንቅስቃሴ፤ መንፈሳዊ ተልዕኮ ከዘመናዊ የልማት ስኬት ጋር እንዴት ተዋህዶ እንደሚጓዝ ሕያው ማሳያ ነው። ዘርቶ የማያልቅበት፣ ቅደም ተከተል ፈጣሪ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን፤ በወላዲተ አምላክ አማላጅነት፣ በቅዱስ ገብርኤል ተረዳኢነትና በአረጋዊው በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ትጋትና መሪነት የሚከናወነው ይህ የታሪክ አሻራ ለፍጻሜ እንዲበቃ የሁላችንም ርብርብና ጸሎት አይለየው። በዲ/ን አየለ #ባቱ #ዝዋይ #ሐመረብርሃን #አቡነጎርጎርዮስ
ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ
Region: ET
Wednesday 04 March 2026 12:04:54 GMT
Music
Download
Comments
🥷⚔️ Kuziy 🇧🇪 :
🥰🥰🥰
2026-03-04 13:44:14
1
@Hizikel ዘደብረ ሰላም 19 :
🥰🥰🥰
2026-03-04 12:43:37
1
Dn AsfawBirraa :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-03-04 12:29:17
1
ተሬ ከሳቴ ብርሀን :
🥰🥰🥰🥰
2026-03-17 09:25:42
0
afetaw manga :
🥰🥰🥰
2026-03-04 17:48:44
0
አባቴ ፲፫ 🥰🥰🥰 :
🙏🥰🥰
2026-03-12 07:51:22
0
seble619 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🙏🙏
2026-03-06 13:01:08
0
Dn Er Dejene :
❤️❤️❤️
2026-03-06 15:28:57
0
KESIS LEYKUN ZEWDU :
🥰🥰🥰
2026-03-10 15:28:13
0
zewe ye maryam leje :
🥰🥰🥰🥰
2026-03-05 11:20:23
0
fike0933 :
🥰🥰🥰
2026-04-01 09:14:14
0
Fido dido 1995G.C :
👌🌸🌸🌸🌸🌸
2026-03-04 15:06:32
0
ዘጸአት :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-03-04 14:45:18
0
fike0933 :
🙏🙏🙏
2026-04-01 09:14:16
0
To see more videos from user @hameretewahedomedia, please go to the Tikwm
homepage.