@musictube369: የድንገት እንግዳ🤌☺️ ✍️ግርማ ሞገስ ያለው መቻልን የታደለ ትልቅ ማንነት ያለው ተወዳጅ ሙዚቀኛ ነው የዓይንሽ ዛጎላማ ነው የደሞ ጀመረኝ የኋላ እንዳይቆጭሽ .... አይነት 12 አልበሞችን ያደረሰን በትውልድ ቅብብል ከዝናው ማማ ላይ ያልወረደ አንጋፋው ሙዚቀኛ ኤፍሬም ታምሩ (ኤፊያችን)🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ የተወለደው ባህርዳር ከተማ ሲሆን አብዛኛው የህይወት ትዝታው የከተመው ግን ከአባትና እናቱ አገር ደጀን ነው፡፡ የፖስታ ቤት ስራ አስኪያጅ የነበሩት አባቱ የሥራ ዝውውር ምክንያት ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ክፍል ያለውን ጊዜውን ባህር ዳር፤ደብረማርቆስ፤ዲላ፤ወሎ ጠቅላይ ግዛት፤ አዲስ አበባ በመዘዋወር ተምሯል፡፡ በአባቱ የጤና እክል ምክንያት ቤተሰቡ ወደ ደጀን ተመልሶ ትምህርቱን እዛው ቢቀጥልም በስካውት ; የትያትርና የሙዚቃ ክለቦችም በመሳተፍ የነፍሱ ጥሪ የሆነውን የሙዚቃ ችሎታውን የተረዳበት ወቅትም ነበር፡: በወቅቱ የተለያዩ ከተሞችን በመዘዋወር የሙዚቃ ስራቸውን ከሚያቀርቡ ባንዶች ጋር ከቤተሰቡ በመደበቅ የክረምትን ሁለት ወራትን አብሮ ያሳልፍ ነበር ፡፡ የቤተክርስቲያን ሰዎች የነበሩት ወላጆቹ በተለይም አባቱ ይህንን በመቃወም በእግር ብረት እስከማሰር ቢደርሱም ሙዚቃ በቤቷ ልታነግሰው ወዳለችና በቀጣይ ክረምቶችን በተመሳሳይ የሙዚቃ ስራ ያሳልፍ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት በጎጃም 7ቱም አውራጃዎች መካከል በዘመናዊና ባህላዊ ሙዚቃ ውድድር ሲደረግ በዘመናዊ ሙዚቃ አንደኛ በመውጣቱ በደብረማርቆስ ሃይስኩል ውስጥ የነበረው የብሉናይል ኦርኬስትራ ይህንን በማየት ቀጥሮት ከባንዱ ገቢ 18 ፐርሰንት እየተከፈለው ከደጀን ደብረማርቆስ እየተመላለሰ የጥላሁን ገሰሰን ሙዚቃ ያቀርብ ነበር፡፡ ዝነኛው ኤፍሬም ታምሩ የሚለው ስያሜም ከዛን ወቅት ጀምሮ ያገኘው ይመስላል፡፡ በህይወቱ ትልቅ ቦታ እንዳለው የሚመሰክርለት ድምፃዊ አያሌው መስፍን ጋር ለመስራት ባገኘው አጋጣሚ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ዛምቤዚክ የተባለ የምሽት ክለብ ስራ ጀመረ፡፡ በታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቃ ድምፃዊ አሊ ቢራ ፈታኝነት በቀን 3 ብር ደሞዝ የተጀመረው የሥራ ህይወቱ ቬነስ ክለብ፤ ሆቴል ዲ-አፍሪክ ፤ ራስ ሆቴል ፤ ጊዮን ሆቴል ፤ሂልተን ሆቴል፤ በመጫወት ቀጥሏል:: “ገና ልጅ ነኝ ጋሜ“ የመጀመሪያ አልበሙ ሲሆን ከታዋቂዎቹ የግጥምና ዜማ ደራሲዎች ይልማ ገ/አብ እና ዶ/ር አበበ መለሰ ጋር የሰራው “ነይልኝ“ ከህዝብ ጋር የተዋወቀበት የምንግዜም ልዩ ስራው ነው፡፡ ለአድናቂዎቹ ባበረከታቸው 12 አልበሞች ፍቅር፤ትዝታ፤ሀገር፤ናፍቆት፤መለያየት:ይቅርታ በማራኪ ጥበብ በድምፁ ተዘክረዋል፡፡ አድናቂዎቹ የድምጻዊው ስራዎች የፍቅር ህይወታቸው አጋፋሪ፤ የትዝታ መሰላል; የሃዘን ማስረሻ እንደሆኑላቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች ይመሰክራሉ፡፡ የቅርብ ጓደኞቹና የስራ ባልደረቦቹ ስለግል ባህሪው ሲያወሱ "ተጫዋች; ቀልደኛ እና ተግባቢ" ነው ይላሉ:: የእረፍት ጊዜውን አትሌቲክስ፤ እግር ኳስ በመመልከት፤ ሙዚቃ በማድመጥና መፅሃፍትን በማንበብ እንደሚያሳልፍ ከአመታት በፊት በሰይፉ ፋንታሁን የመዝናኛ ዝግጅት ላይ ቀርቦ ገልጷል፡፡ ኤፍሬም ታምሩ አዲስ አልበም ጀባ እንደምትለን ተስፋ አደርጋለሁ። ጥበበኞች ዜማና ግጥሚቸውን ከሽነው ደስ በሚለው አዚያምህ ሙዚቃን ከነክብሯ እንናፍቃታለን። እኔም ለዛሬ ከታላቁ ሮሃ ባንድ ጋር እና እጅግ ከምናከብረው አበጋዙ ጋር በመሆን በውብ ሁኔታ ከሰራው እንደገና አልበም እጅግ ተወዳጁን 'የድንገት እንግዳ'ን እንደተለመደው ለትውስታ ጀባ አልኳቹ☺️ ስለ አበረከትክልን ፍቅርን አንድነትን ህይወትን ከሚያሳዩን የማይጠገቡ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች እናመሰግናለን ሁሌም እንሰማቸዋለን እናያቸዋለን። ከዘፋኝ ኩሩ ኤፍሬም ታምሩ🥰🙏 ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 musictube #fyp #ኤፍሬምታምሩ #የድንገትእንግዳ #musictube369 #ethiopianmusic

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 04 March 2026 19:46:36 GMT
120426
6174
45
380

Music

Download

Comments

rasyab64
𝖎𝖛𝖆𝖗 :
ኦረ ገደለኝ ኤፍሬም
2026-03-04 20:20:07
13
mistir191
ሚስጥር🦅⚡️ :
ግርማ ሞገስ ያለዉ ሙዚቀኛ🥰🥰🥰👌👌👌
2026-03-04 20:56:51
8
tg.hal
Tg Hal :
የሙዚቃ ንጉስ!!! 🥰
2026-03-05 16:39:10
9
dbgr48
Ye z :
2026-04-04 07:33:41
2
jordanarodolfo
jordanna :
the one and only ephrem!!
2026-03-31 05:51:00
0
yankhjutdzcgjko
ድያቆን ዓሊ 🍑✟☪ :
zim belo yezfen❤
2026-03-05 16:12:30
2
se46659
Me 21 :
Effiyee 🥰🥰🥰
2026-03-20 19:35:21
0
mahletassaye181
wube :
ይሄ ሰውዬ ሊያሳብደን ነው ❤❤❤
2026-04-12 19:36:59
0
adiss.re1
Jerry :
wawe wfye w
2026-03-12 07:02:00
0
workinehbayugold
workinehworkineh0 :
yes
2026-03-08 14:26:29
0
mesi92827
meseret bayisa :
111111111111
2026-03-07 00:19:14
0
fasiltes0
ፋas :
remix ahhhhhh
2026-03-05 20:26:33
1
ephrem4625
Ephrem :
wow ephre
2026-03-05 11:25:03
1
e134784
winner👑 :
1ኛ ዘፈን🥰
2026-03-05 07:11:45
2
trusew.habtamu
Trusew Habtamu :
the legend 🙉
2026-04-24 06:28:10
0
tansay.shanbal
tanse oro king :
❤️❤️❤️
2026-04-24 16:30:38
1
minteetashomee
Amen Yemariyam🫅🦋 :
😍😍😍
2026-03-05 12:03:32
1
butkntafssjun.lop
bu :
💪💪💪
2026-03-05 13:50:20
1
tigistzetg48
Tigistzetg :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-03-05 10:47:06
1
amdu.....69
ʟɪᴊ ʜᴀᴍᴅᴀ...🌴 :
😇😇😇
2026-03-05 11:50:34
1
biruk1627_biruk
biruk1627 :
🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖💖🥰💖🥰💖💖🥰💖🥰
2026-03-05 11:19:38
1
user7509278596537
user7509278596537 :
🔝🎧
2026-03-05 17:02:46
1
emanda385
Amanda :
❤️❤️❤️
2026-03-05 11:37:55
1
pdave_grace
DAVE- Grace🌴 :
😭
2026-03-05 09:40:39
1
bruk4932
Bruk### :
🥰🥰🥰
2026-03-05 07:21:21
1
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About