@gebrekidan07: ማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም! የማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም ኢትዮጵያዊ ትውፊቱን ያልለቀቀ እና ጥብቅ ሥርዓትን የተከተለ ሕይዎት የሚኖርበት ሃይማኖታዊ ቦታም ነው፡፡ ገዳሙ ከጎንደር ከተማ 132 ኪሎ ሜትር፣ ከመተማ ወረዳ ገንዳ ውኃ ከተማ 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ከደረቅ ዓባይ ቀበሌ በስተደቡብ የ3 ሰዓት የእግር ጉዞ ካደረጉ በኋላም ይገኛል፡፡ የማኅበረ ስላሴ አንድነት ገዳም በአራተኛው መቶ ከፍለ ዘመን በመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጳጳስ አቡነ ሰላማ ዘመን እንደተመሠረተ ይነገራል። የአሁኑን ስያሜ ከማግኘቱ በፊት “ምቋመ ሥላሴ”ይባል ነበር፡፡ የሺዎች ማኅበር እየተባለም ይጠራል፡፡ ማኅበረ ሥላሴ የሚለው ስያሜ በአጼ ፋሲለደስ እንደተሰየመም ነው የሚነገረው። ማኅበረ ስላሴ አንድነት ገዳም ከአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ከነበሩ ነገሥታት ጋር የተሳሰረ ታሪክ እንዳለውም ይነገራል። ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ፣ ከአጼ አምደ ጽዮን፣ ከአጼ ልብነ ድንግል፣ ከአጼ ሱስንዮስ እና ከአጼ ፋሲለደስ ጋርም የተያያዘ ሰፊ ታሪክ አለው፡፡ ከሱዳን ድንበር አካባቢ በመገኘቱ ምክንያት በተለያየ ጊዜ ጥቃት ሲደርስበትም ቆይቷል፡፡ ከዮዲት እስከ ሁለተኛው የጣሊያን ወረራ በተደረጉ ጦርነቶች የገዳሙ በርካታ ቅርሶች ወድመዋል፡፡ ገዳሙ የተለያዩ የእፅዋት ዝርያዎችንም ይዟል። የዲዛ፣ የእጣን ዛፍ፣ ሽመል፣ ዞቢ እና ቋራ የመሳሰሉት እፅዋት ዝርያዎች መገኛም ነው። እንደ ዝንጀሮ፣ ነብር፣ አጋዘን፣ ሜዳቋ የመሳሰሉ የዱር እንስሳት፣ እፅዋት፣ እዕዋፋት እና ተሳቢዎች ይኖሩበታል፡፡ ገንዳ ውኃ እና ሽንፋ በተባሉ ታላላቅ ወንዞች የተከበበም ነው። ገዳሙ የአካባቢውን ሥነ ምኅዳር ከመጠበቅ አኳያ ባለው ፋይዳ ተመሥርቶ በጥብቅ ሥፍራነት እንዲከለል ተደርጓል፡፡

ልጅ እሸት
ልጅ እሸት
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 13 March 2026 12:00:35 GMT
3152
230
5
13

Music

Download

Comments

aman05934
aman :
🙏🙏🙏🙏
2026-03-13 12:06:43
1
abreham121296
ABEREHAM1212 :
🥰🥰🥰
2026-03-13 12:07:20
1
massssssu1
ማስቴ😂❤ጎጃሜዋ❤😂 :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-03-13 12:19:58
0
ayu85232
Kebron Ayenew @@@$$$ :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-03-13 16:36:58
0
samueldagnew257
ቀራንዮ ሚድያ :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰 በርታ
2026-04-06 12:27:20
0
To see more videos from user @gebrekidan07, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About