@kidankal.tadele30: በአባታችን አቡነዮሴፍ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም። ይሄ ታላቅ ገዳም የሚገኘው በላስታ ቅዱስ ላሊበላ አቡነ ዮሴፍ ጥብቅ ሲሆን ከቅዱስ ላሊበላ በስተሰሜን ምስራቅ በግምት ከ64km በላይ የሚወስድ ሲሆን ገዳሙ የሚገኝበትም ስፍራ አቡነ ዮሴፍ በኢትዮጲያ በከፍታ ሦስተኛ ተራራ እንደሆነ ይነገራል ከውም -‹አቡነ ዮሴፍ› የሚለውን ስም ያወጣላቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ - የንጉስ ዳዊት ልጅ ሆነው ሳለ ዓለምን ንቀው መነኑ፡፡ - ሲወለዱ 117 ሙታን ተነስተዋል፡፡ - ጽርሐ አርያም ድረስ ሄደው የሥላሴን መንበር አጥነው ተመልሰዋል፡፡ - ከድንግል ማርያም ወንበር እና መስቀል ተቀብለዋል፡፡ - ታምረ ማርያምን ከግብጽ አስመጥተዋል፡፡ - አንቀጸ ብርሃንን ራስደጀን ሄደው አምጥተዋል፡፡ - ዝንጀሮን እና ሰውን አሰታርቀዋል፡፡ አሁንም የሚታይ ነው። አቡነ ዮሴፍ አባታቸው አጼ ዳዊት ፡ እናታቸው ጽዮን ሞገሳ ፡ወንድማቸው አጼ ዘርዓያዕቆብ ዘተስሜ ቆስጠንጢኖስ ነው፡፡ ብርሀነ አለም አቡነ ዮሴፍ በ 1383 ዓ.ም ህዳር 19 ቀን ተወለዱ ፡፡የተወለዱ እለት 117 ሙታን ተነሱ ፡ አቡነ ዮሴፍ መጀመሪያ ስማቸው መርቆሪዮስ ነበር ፡መርቆሪዮስ የዚህን አለም ጥበብ ና የቤተክርስቲያኑን ሞያ ጥበብ በአባታቸው ቤት እያሉ ተማሩ ፡፡ከተወለዱ ጀምረው የሚያደርጉት ታምር ያስደንቅ ነበር፡፡ድቁና ሾሟቸው፡፡ እግዚአብሔር የነብሳቸውን ድህነት በወደደ ግዜ ብርሀናዊ መለአኩን ቅዱስ ሚካኤልን ላከላቸው እና መርቆርዮስ ሆይ ይህን ሀላፊውን አለም ትወደዋለህን ?አፀያፊ አይደለም? አላቸው ፡፡ከዚያ ግዜ ጀምረው እሱ እራሱ የወደደውን መንገድ ይመራቸው ዘንድ እግዚአብሔርን እየለመኑ ጾምና ጾሎት እያበዙ ይሄዱ ጀመሩ፡፡ ከተወለዱበት ሀገር የሚኖር አባ ዘካሪያስ የሚባል ነበር እርሱም ዘመዳቸው ነበር ፡፡ #habeshatiktok #creatorsearchinsight #EthiopianOrthodox #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር #ኦርቶዶክስ⛪ተዋህዶ⛪ለዘለዓለም🙏ትኑር🙏
Kidankal (ኪዳነቃል)
Region: ET
Sunday 22 March 2026 09:58:58 GMT
Music
Download
Comments
Abraham :
ሰይናይ❤️❤️❤️🥰🥰
2026-05-18 14:14:53
1
Weldesenbet yimer :
ይበል ነው ፀጋ ማለት እንድህ ነው
2026-03-24 04:00:19
1
የአርሴምዬ ልጅ :
🙏🙏🙏
2026-03-23 10:27:40
1
Abraham64 :
🥰🥰🥰
2026-03-24 02:00:59
1
To see more videos from user @kidankal.tadele30, please go to the Tikwm
homepage.