@pethome_shopvn: Hạt S2 Pet V3 thành phần 35% gà và 18% bò giúp bé ăn ngon #hatchomeo #meow #fyp #thucanchomeo #pethomeshopthucung #xuhuong #s2pet #s2petv3

PetHome-Shop Thú Cưng
PetHome-Shop Thú Cưng
Open In TikTok:
Region: VN
Wednesday 01 April 2026 12:00:00 GMT
1201
0
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @pethome_shopvn, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

አካል ለአካል🤌🤒 ✍️(
አካል ለአካል🤌🤒 ✍️("...ሙዚቃ ከነ ሙሉ ከብሯ በኤልያስ በኩል ነው ምታልፈው") ሮፍናን ደሞ እንዲህ ይላል ("...ኤልያስ መልካ ሙዚቃ አቀናባሪ ብቻ አይደለም ፈላስፋም ጭምር እንጂ) 🥰 ትላላለች ዘሪቱ ከበደ ስለከተማው መናኝ ኤልያስ መልካ💔 ነፍሱን ይማረውና ኤልያስ መልካ -አንድ ሆኖ ብዙ ነበረ ሊድ ጊታሪስት, ቤዚስት, ፒያኒስት, ድራመር, ሳክስፎኒስት, ኮንዳክተር, ገጣሚ, የዜማ ደራሲ, አቀናባሪ, ፕሮዲውሰር ይሄን ሁሉ መሆን ለአንድ ሰው በጣም ከባድ ነው።🙏🙌 ✨ ውድ ቤተሰቦቼ በአዲስ አመት መባቻ 1996 ጷግሜ ላይ የወጣውን እንደ ጎርፍ ከተማዋን በድንቅ ድምጿ አነጋግራ አዲስ መሆኗን ባስረሳቺው በተወዳጇ ዘሪቱ ከበደ በአይነቱም በይዙትም ወጣ ብሎ በድንቁ ኤልያስ መልካ ግሩም ልህቀት ተከሽኖ በቮይስ ሙዚቃ ቤት በኩል ለኛ ለአድማጮች የደረሰውን በስሟ "ዘሪቱ" ተብሎ በስሟ የተሰየመውን ጥንቅቅ ያለ አልበም መቼስ ከብዙዎቻችን የሙዚቃ ወዳጆች ልብ ውስጥ ሁሌም በፍቅር የሚኖር የሚናፍቅ ጥንቅቅ ተደርጎ የተሰራ አልበም ነው🥰🙏 ታዲያ ከዚህ የሚጣል ዘፈን ከሌለው ውብ አልበም ላይ አንድ ድንቅ ጥምረት የማይደገም የሚመስል ጥምረት የአብነት እና የዘሪቱ ኮከቦች በሚያረግፍ ድምፅ እየተቀባበሉ የፍቅርን መላዕክት ያነቁበት ሙዚቃ የሄ ዛሬ የጋበዝኳቹ 'አካል ለአካል'💛 ዘሪቱ ለሙዚቀኝነቷ መነሻ አባቷ የሚያደምጧቸው የእነ elef derald ፣ Nat King Cole ፣ ካሳ ተሰማ ፣ መሀሙድ አህመድ የሸክላዎች ሙዚቃዎች ነበሩ ። በነገራችን ላይ የዘሪቱ አባት የአርክቴክት ባለሙያ የነበሩ ቢሆንም ከበደ "ማርንጌ" የሚል ቅፅል ስም ያስቸረ የዳንስ ችሎታም ነበራቸው😁 ዘሪቱ ከልጅነት የጀመረው የሙዚቃ ፍቅሯ በአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ባሉ የት/ቤት ክበባት ከዳበረ በኋላ በ1996 አ.ም ለአድማጭ በደረሰው የላፎንቴኖች " ጓደኛ " አልበም ላይ በምን ሰይሜሽ፣ላላ፣ትዝ ይለኛል በተሰኙት ሙዚቃዎች በኳየር እና ፊውቸሪንግ በመሳተፍ ብቅ አለች በዛው አመት ለ HIV በተቀነቀነው "መላመላ" በተሰኘው የህብረት ዜማ ላይ ከደረቷ በመታወጣው በሀይለ የተሞላ ተስረቅራቂ የድምፅ ችሎታዋ ጋር በሰፊው ከህዝብ ጋር ተዋውቃለች። የህይወት Experience፣በተለያዩ ግዜያት ውስጧን የነኩ ፊልም እና ሙዚቃዎች ሙዚቃን ለመስራት የሚያነሳሷት ዘሪቱ ከበደ ውስጧን በነኩ እንደነዚህ ባሉ ጉዳዮች ላይ መሰረት ያደረገውን እና በውስጡ 12 ሙዚቃዎችን ያካተተውን "ዘሪቱ" የተሰኘውን አልበሟን በወርሀ ጳጉሜ 1996 አ.ም ለአድማጭ አደረሰች ። ዘሪቱ ከበደ እስከ አሁን ድረስ የመጀመሪያም የመጨረሻም በሆነው በዚህ አልበሟ በዋናነት ተስፋን፣ይቅርታን፣ፍቅርን፣ወቀሳን፣ሙግትና ጥያቄን ያዘሉ ፍቅር ወለድ ሀሳቦችን ዳስሳበታለች "ዘሪቱ" አልበም በ90ዎቹ ከወጡ ሰፊ ተወዳጅነት እና ተቀባይነት ካገኙ ግንባር ቀደም አልበሞች አንዱ እና ዋንኛም ነው ዛሬም ድረስ ተደማጭ ተወዳጅ ሲሆን የአዳዲስ ድምፃውያን መፈተኛ የልክነት ማሳያም ነው። ይህ በበሳል ግጥሞች ሀሴት በሚያላብሱ ዜማ እና ቅንብሮች የታጀበው ተወዳጅ አልበም አብዛኛው ግጥሞች በዘሪቱ ከበደ የተደረሱ ሲሆን ኤልያስ መልካ እና አብነት አጎናፍር በግጥም ተሳትፈውበታል አብዛኛው ዜማዎችም በዘሪቱ ከበደ የተሰሩ ሲሆን ኤልያስ መልካ፣ናቲ ማን፣አብነት አጎናፍር፣ሄኖክ መሀሪን የመሳሰሉ ታላላቅ ሙዚቀኞችም በዜማ ተሳትፈውበታል። ባለፉት 25 አመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ የገነነ ስም ያለው ታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ኤልያስ መልካ ሙሉ አልበሙን ችክችካ፣ሮክ፣ስሎው ሮክ፣ፖፕ እና ካንትሪ ስልቶችን በማላበስ አዲስ ነገር ይዞ መቶ አቀናብሮታል ዘሪቱ ከበደ ከዚህ አልበሟ በኋላ ሁለተኛ አልበም ለአድማጭ ባታደርስም እንደ እነ አርቴፊሻል፣አዝማሪ ነኝ፣ውሸታም፣አይደለሁም ስም፣ አለሁ ፣እዛ አልቀረሁም፣ ደግሞ የወንድ ቆንጆ እና ወዘተ ያሉ ጠንካራ መልዕክት ያላቸው እና ፍቅርን የሚሰብኩ በርካታ ነጠላ ዜማዎችን ለህዝብ አድርሳለች ። በአሁኑ ሰአት ዘሪቱ በእሷ እምነት እና አስተሳሰብ "አዝማሪ ነኝ" ያለችለትን "አርቴፊሻል" አለም "ውሸታም" ብላ በአዲስ መንፈሳዊ ማንነት " እዛ አልቀረሁም " በማለት ከሙዚቃ ጋር ስንብቷን ያስረገጠች ይመስላል ዘሪቱ ከበደን ዛሬ ሙዚቃችን ላይ አለማየታችን እጅግ ቢያስቆጭም እራሷ እንዳለችው " እሱ አይሳሳት ሁሉም በምክንያት " እያልን የዛሬን የሙዚቃ እና ሙዚሸኞችን ዳሰሳችንን እንቋጫለን 🙌። ዘሪቱዬ🥰 ረጅም እድሜና ጤና ፈጣሪ ጨምሮ ይስጥሽ እንወድሻለን ክበሪልን🙏 ቤዛ ለከተማው መናኝ ታላቁ ሰው ኤልያስ መልካ ለሥራዎችህ እጅ እንነሳለን! "ዘመን ልርሳህ ቢል እንኳን ሊረሳ የማይችል ታላቁ ሰው ኤልያስ መልካ" ጊዜ ለማይሽራቸው ሥራዎችህ እጅ እንነሳለን! ነፍስህ በሰላም ትረፍ... 🙏 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🙌🙏 @musictube 🇪🇹 #fyp #ዘሪቱ_ከበደ #አካልለአካል #musictube369 #ethiopianmusic

About