@musictube369: እሹሩሩ 🤙🤤 ✍️ በዛወርቅ አስፋው፣ አለማየሁ ሂርጶ፣ ትግስት በቀለ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ፣ ኤልሳቤት ተሾመ፣ ሙሉጌታ አባተ፣ ከድር ጭቅሳ፣ መስፍን ታምሬ፣ ዓለምአየሁ ደመቀ፣ታመነ መኮንን... ውብ ጥምረት ነፍሱን ይማረውን በወቅቱ እጅግ ዝናን አግኝቶ ከነበረው ቴዲ ራጋ 🙏 የሙዚቃ በለውለታ የማራቶን ሙዚቃ ቤት ባለቤት አቶ ታምሬ ልጅ የጥሩ ጆሮ ባለቤት ፕሮዲውሰር መስፍን ታምሬ ጋር በከድር ጭቅሳ እና ሙሉጌታ አባተ በአዲስ እይታ በመጣ ድንቅ የሙዚቃ ቅንብር ብቃት የተከሸነ ውብ የፈጠራ አልበም "Take Five Collection" 👌🥰 1.በዛወርቅ አስፋው "ና ደሞ ና" 2."ቡና" በዛወርቅ አስፋው 3.ጎሳዬ ተስፋዬ "ጽጌሬዳ" 4.አለማየሁ ሄርፖ "ጥርሶችሽ" 5.ጎሳዬ ተስፋዬ "አሞኛል" 6.ትዕግስት "እሹሩሩ" 7.ጎሳዬ ተስፋዬ "አራዳ" 8.አለማየሁ ሄርፖ "በመልክሽ" 9.ጎሳዬ ተስፋዬ "ሲዋልል" 10.ኤልሳቤጥ ተሾመ "ልጁን ያያቹ" 11.አለማየሁ ሄርፖ "አለው ይሆን እንዴ" 12.ጎሳዬ ተስፋዬ "የጎጃም ማር ነሽ" የዚህ እና የሌሎች ዘመን ተሻጋሪ አልበሞች ቀማሪ ያልተወራለት ያልተከበረው በስራው ልክ ያልተዘመረለት በርካታ አርቲስቶችን ፈር ቀዳጅ ሆኖ ከህዝብ ያስተዋወቀ እጅግ ትልቁ የሙዚቃ ቀማሪ (አቀናባሪ) የዛሬው ተመስጋኝ ባለታሪካችን ከጥቂት አመታት በፊት በአሳዛኝ ሁኔታ ሳናስበው ያጣነው ሙልጌታ አባተ(ዳባ ሮባ) 1957-2009🙌🙏 ✨ውድ ቤተሰቦቼ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከአንድ ምዕራፍ "ብቸኛ ባንድ" ሆኖ ወደ ሌላ ምዕራፍ ያሸጋገረ፤ከ "400" በላይ አልበሞችና በጥቅሉ ከ "5000" በላይ ዜማዎችን ያቀናበረ እንዲሁም ከበርካታ ዘፈኖች ጀርባ ሆኖ ግጥምና ዜማዎችን የሠራ የዚህች ሀገር ታላቁ የሙዚቃ ባለውለታ ባህሉን ጠንቅቆ የተረዳው ሙልጌታ አባተ በ1957 ዓ.ም በወሎ ኮምቦልቻ ነበር የተወለደው። ይህ ታላቅ የሙዚቃ ባለሙያ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ድርሻ ነበረው፡፡ ከታላላቆቹ ድምጻውያን ጋሽ ማህሙድ አህመድ እና ታምራት ሞላ ጀምሮ እስከ ዘመነኞቹ ማዲንጎ አፈወርቅ እና ፍቅርአዲስ ነቅአጥበብ የበርካታ ድምጻውያንን ቀን በሥራዎቹ ማውጣት ችሏል፡፡ ለ25 ዓመታት በዘለቀ የሙዚቃ ቅንብር፣ የዜማ እና የግጥም ደራሲነት ሙያው ከ5000 በላይ ሙዚቃዎች ሠርቷል፡፡ ከዕውቁ የሮሀ ባንድ በመቀጠል ለረጅም ዓመታት በሙዚቃ አቀናባሪነት ያገለገለ ‹ብቸኛ ባንድ› እስከመባል ደርሶም ነበር ሙልጌታ አባተ ልቡ ለባህል ዘፈኖች የምታደላ ቢሆንም ለዘመናዊ ሙዚቃዎች እና ለበርካታ የብሔር ብሔረሰብ ዘፈኖች የዋለው ውለታም እንዲሁ በቀላሉ የሚነገር አይደለም፡፡ ከኦሮምኛ ድምጻውያን ዳዊቴ መኮንን (አን ዱፌን ጅራ)፣ ጌታቸው ኃይለማርያም . . . ከጉራጊኛ ጋሽ አርጋው በዳሶ . . . ከወላይትኛ ኮይሻ ሴታ . . . እና ሌሎች ስመ ጥር የብሔር ብሔረሰብ ዘፋኞች በእጁ ጥበብ አጊጠዋል፡፡ ድምጻዊ አበበ ተካ (‹‹ወፊቱ›› - አበበ ተካ / ሙዚቃ አቀናባሪ - ሙልጌታ አባተ / ዜማ ደራሲ - አበበ ብርሃኔ / ግጥም ደራሲ - ሙልጌታ )፣ ማናልሞሽ ዲቦ፣ ሠርጉዓለም ተገኝ፣ ኃይልዬ ታደሰ፣ ፀጋዬ እሸቱ፣ ታደሠ ዓለሙ፣ ገነት ማስረሻ፣ ሐመልማል አባተ፣ ማዲንጎ አፈወርቅ፣ ሰማኸኝ በለው፣ . . . ምኑ ቅጡ . . . ብቻ . . . በዜማና ግጥሞቹ እንዲሁም በሙዚቃ ቅንብሩ ረጅም እጁን ለበርካታ ድምጻውያን ጀባ ሲል ኖሯል - ‹‹ያለ አንዲት እረፍት››፡፡ በቅጽል ስሙ ‹ዳባ ሮባ› ተብሎ የሚጠራው ሙልጌታ አባተ የውለታውን መክበድ ያህል ስሙ በአደባባይ ከፍ ብሎ ለመጠራት አልታደለም፡፡ ስለዚህ ባለ ቲፎዞ አልነበረም፡፡ እናም ከ5000 በላይ የሙዚቃ ሥራዎች ያሉት ትልቅ ባለሙያ ጥቂት ወዳጆቹና የሙዚቃ ሠዎች በተገኙበት ህዳር 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በሠሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርሲቲያን የተቀበረው የእድሜውን 25 ዓመታት ገደማ አብዛኛውን ጊዜ ስቱዲዮው እያሳለፈ ለስድስት ልጆቹ እና ለባለቤቱ እንኳን ተገቢውን ጊዜ ሳይሠጥ የኖረው ሙሉጌታ ‹መቼ ነው ግን የምታርፈው› ተብሎ ሲጠየቅ ‹ስሞት ነው የማርፈው› ብሎ ይመልስ ነበር፡፡ይህ ታላቅ የሙዚቃ ባለሙያ ከሦስት ወራት የሕመም እንግልት በኋላ በ52 ዓመቱ አረፏል፡፡ ሙልጌታ አባተ ትዳር መስርቶ ስድስት ልጆችን ያፈራ ነበር። በሠራቸው አይረሴ ዜማዎች ትውልድ ሲዘክረው ይኖራል እኔም ለዛሬ የዚህን ታላቅ ባለሙያ ስራዎች እና ታሪክ እጅግ በጣም በጥቂቱ ከውቅያኖስ በጭልፋ እንዲሉ አውስተነዋል ነፍስ ይማር🙏🙏 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 musictube 🇪🇹 #fyp #Ethiopianmusic #musictube369 #ትዕግስትበቀለ #እሹሩሩ

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱️🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱️🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 05 April 2026 15:18:34 GMT
32010
1557
24
67

Music

Download

Comments

heldannas
ሕልዳና :
My favorite page on this app
2026-04-06 00:40:11
2
jaket.55
J :
መስፍን ታምሬ ምን አይነት ፕሮዲዩሰር ነው He so amazing
2026-04-05 16:47:06
5
gmsmkca
gmsmkca :
ሙሉጌታ አባተ 🙏🙏🙏
2026-04-06 11:33:57
3
yoni_4k
Yoni 4k :
TG used to blur her face on the album cover!
2026-04-06 08:52:41
1
silavip1
Šilå Đ Ćlåssīc :
tigye
2026-04-09 08:17:25
0
abaselom.assefa
Abey Assefa :
Teddy raga ahunm ale
2026-04-05 17:48:15
1
emanda385
Amanda :
🥰🥰🥰
2026-04-06 11:17:31
1
natanestifanos
Natan Estifanos ኤልያስ መልካ :
🙏
2026-04-06 15:39:03
1
taju6034
$ .M. Ŷ ÊŶMÛĶ ĴŘ 🤑🥰🥰 :
😏
2026-04-08 21:41:38
0
taju6034
$ .M. Ŷ ÊŶMÛĶ ĴŘ 🤑🥰🥰 :
😂
2026-04-08 21:41:38
0
taju6034
$ .M. Ŷ ÊŶMÛĶ ĴŘ 🤑🥰🥰 :
😏
2026-04-08 21:41:38
0
user9498043765910
user9498043765910 :
🔥🔥🔥
2026-04-07 19:46:26
0
taju6034
$ .M. Ŷ ÊŶMÛĶ ĴŘ 🤑🥰🥰 :
😂
2026-04-08 21:41:38
0
taju6034
$ .M. Ŷ ÊŶMÛĶ ĴŘ 🤑🥰🥰 :
🥰
2026-04-08 21:41:38
0
teki762
ተክለab :
💪💪
2026-04-05 17:31:12
1
samenebahewi
same🚔 :
🥰🥰🥰
2026-04-05 15:27:03
1
wenda2258
wenda :
ዋው ምርጥ ሙዚቃ💚💚💚💚🙏🙏🙏🙏🙏
2026-04-05 19:22:25
1
tewodros183
Tewodros183tedy :
🥰🥰🥰
2026-04-05 18:59:45
1
biruk1627_biruk
biruk1627 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-04-05 17:00:04
1
ms937312
ms olds :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-04-07 06:41:42
0
andlandaychew
Andland :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-04-07 12:43:26
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About