@musictube369: ምነው ሸዋ 🤌🤤 ✍️ይገርማቹሃል ሁሉም ነገር አበቃና አብዱ ኪያርና ቴዲዮ ዘፍናችኃል ተብለው ሲኦል ውስጥ ሰይጣን እይቀቀላቸው ነው አሉ በመሃል አብዱ ኪያር ሶስት ቀን ሙሉ ረፍት ተሰጠው… ቴዲዮ ቀወጠው፤ እኔም ዘፋኝ እሱም ዘፋኝ እንዴት ተደርጎ ብሎ አንዱን ሰይጣን ጠየቀው: … ሰይጣኑም "ባክህ እኛም ተበሳጭተናል 'ትልቅ ፈጣሪ ነው ትልቅ ለዘላለም የሰው ትልቅ የለም' የሚለው ዘፈኑ እንደመዝሙር ተይዞለት ነው አሉ🤭😂 (ደሞ ከቴዲ ዮ ጋር አታጣሉኝ ቀልዱን ነው የነገርኳቹ😁) ✨ውድ ቤተሰቦቺ ኤቢዲ ድንቅ ድምፃዊ ብቻ አይደለም እንደ ታላላቆቹ እንደ ነዎይ እና አስቴር ጨዋታ አዋቂ እና የተጨበጨበለት ድንቅ የግጥም እና ዜማ ደራሲም ጭምር ነው ታዲያ የአንዳንድ ሙዚቃዋቹ የግጥም ጥልቀት እንደ መዝሙር ጥልቅና የረቀቀ ነው ልክ ዛሬ እንደጋበዝኳቹ 'ምነው ሸዋ'🙌 ይህ በተወዳጁ አርቲስት "አብዱ ኪያር" የሙዚቃ ግጥም ፥ በዘመናችን ከሚስተዋሉት የአምላክን ታላቅ ክብር የዘነጉ ፣ ቅዱሳን መፅሐፍቶች ሁሉ የሚያስተላልፉትን አስተምህሮት መሠረታዊ ነጥብ የሳቱ ፣ የእኔነት ስሜትን በማርካት ላይ ያነጣጠሩ ፣ በራስ ወዳድነታችንና በሥጋዊ ከንቱ ፍላጎታችን ዛቢያ የሚሽከረከሩ መዝሙር ከማይመስሉ መዝሙር ተብዬዎች ጋር ሳነፃፅረው - ይህንን የአብዱ ኪያር የሙዚቃ ግጥም "ዘፈን" ሳይሆን "መዝሙር" ብዬ ልጥራው እችላለሁ👌 . ቢቀር ይቅር ~ ቢቀር ይቅር እንጂ ምቾቴ መክበር አልፈልግም ~ እኔስ በብልጠቴ ብኖር ይሻለኛል ~ ከነቅንነቴ በስፍር በቁጥር ~ ላልተወሰነ ዕድሜ ላልተወሰነ ዕድሜ አልፈልግም መኖር ~ ባቋራጭ ቀድሜ ባቋራጭ ቀድሜ የዛሬን ለመኖር ~ ማስመሰል አልችልም ተዉኝ እኔ አልችልም ለማይረባ ፀሎት ~ እኔ "አሜን" አልልም እኔ "አሜን" አልልም የሆዴን ነገር ብረሳ ~ የዋህነቴን ባበዛ ሞኝ ነህ አሉኝ ፈዛዛ እውነትን ይዞ የኖረ ፍቅርን ይዞ ያደረ ልቡን ለእውነት የሰዋ ሞኝ ይባላል ወይ ሸዋ? ፍቅር ከውስጥ እንጂ ~ ከነፍስ መች ተገኝቶ ያውቃል ~ ውጪው ቢታሰስ ልብ ይቀርብ የለም ወይ ~ ከሰው ሰራሽ ኪስ 💡በጠቅላላው በዚህ በ2001 ባልተነገረት ድንቅ አቀናባሪ ዳዊት ጥላሁን ተቀምሮ ሙሉ በሙሉ በአብዱኪያር ግጥም እና ዜማዎች ተዋቅሮ በተበጀው 11 ሙዚቃዎችን የያዘው እንከን አልባ አልበም ላይ እውነት ለመናገር የሚጣልም ዘፈን የለውም ለኔ በግሌ እዚህ አልበም ላይ የተካተቱት ሙዚቃዎች ከሱ አልበሞች ሁሉ በግጥሞቹ ብስለት እጅግ ይለይብኛል👌 ለምሳሌ ሰባት ፣ ቻይና ቻይና ፣ ነፍሴ ነሽ ትግስቴ ፣ ማፈሬ ፣ እንደድሮአችን አይነት ሙዚቃዎችን ከምነው ሸዋ በተጨማሪ መመልከት እንችላለን 💡ማህበረሰባዊ ጉዳዮችን በሚፈትሹና ጽንሰሃሳባዊ ብስለትንና ፋይዳን ያዘሉ ጉዳዮችን በድፍረት ከሚያነሱ ጥቂት ድምፃውያን አንዱ የሆነው ድምፃዊ ና የዜማና ግጥም ደራሲ አብዱ ኪያር በ90 ዎቹ የሙዚቃውን አለም ተቀላቅለው ተቀባይነትን ካገኙ ድምፃውያን መሃል አንዱ ሲሆን በ 1995 ዓ.ም "መርካቶ ሰፈሬ" በ 1998 ዓ.ም "ፍቅር በአማርኛ" በ 2001 ዓ.ም "ምነው ሸዋ" በ2008 ዓ.ም "ጥቁር አንበሳ" በቅርቡ ደሞ "ፖ" የተሰኙ 5 የሙዚቃ አልበሞችን ወደህዝብ አድርሷል። ለጎሳዬ ተስፋዬና ፍቃዱ ግርማ ዜማና ግጥም ከመድረሱም ባሻገር ከካሳሁን እሸቱ፤አዲስ ሙላት፤ሜላት ቀለመወርቅና አፍሪካዊው ፍራንኪ ዲ ጋር በጥምረት ማቀንቀኑም ይታወሳል።የአንጋፋውን ተወዳጅ ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩን "በፍቅርሽ መያዜን" የተሰኘ ቆየት ያለ ነባር ዜማ በድጋሚ ከመጫወትም ባለፈ "ማለባበስ ይቅርና" "መላ መላ" በተሰኙ ኤች አይ ቪን የተመለከቱ ህብረዝማሬዎች ላይ መሳተፉ አይዘነጋም። "እርድና ከኤርትራውያን እናትና አባቷ ሰባተኛ ውስጥ ተወልዳ በህዝብ ተቀባይነትን ካገኘች እነሆ 49 አመት ሆኗታል። ፍቅር ሐይማኖት እንደማይገድበው ኦርቶዶክስ ሚስቱ ምስክር ነች። ወንድ ልጅ ገግሞ ሰርቶ ገንዘብ ማግኘት እንዳለበት አምስት አመት ከስድስት ወር የፈጋባት የሳውዲዋ ጅዳ ትመስክር። ሰው ገንዘብና ዝናን ሲያገኝ የነበረበትን መርሳት እንደሌለበት በጉስቁልና ጊዜ የደረሰላቸው የአማርኛ መምህሩን ሒዱና ጠይቋቸው።ሰለ ግጥምና ዜማ ችሎታው አራቱን አልበሞቹን ለጆሮዎቻቹ ጋብዛችሁ መልሱን አድምጧቸው። ስለ ጨዋታ አዋቂነቱ ከስሩ የማይጠፉት ታዋቂ ሙዚቀኞችን ጠይቋቸው። አብዱ ኪያር ማለት ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ቆሎ ውስጥ እንዳለ ለውዝ ማለት ነው። ቆሎው ሌሎች ሙዚቀኞች ናቸው። ቆሎውን ያለ ለውዙ መቆርጠም ትችላለህ። ለውዙን ስትጨምርበት ግን ቆሎው ጣፍጦህ እንድትቆረጥም ያደርግሃል ። ሁሉም ሰው እንዳጋጣሚ ከቆሎው ውስጥ ቀድሞ የሚቆረጥመው ለውዙን መሆኑ ደግሞ ይገርማል። ኢንተርቪ ካንተ ውጪ ለአሳር ነው! አስር አራዳ አውቃለው ዘጠኙ አብዱ ኪያር ነው የተባለለት እድሜ እና ጤና ጨምሮ ይስጥህ ለዛሬ አበቃሁ🙌🥰 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 musictube 🇪🇹 #fyp #Ethiopianmusic #musictube369 #አብዱኪያር #ምነውሸዋ

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 13 April 2026 17:10:34 GMT
158678
11886
69
620

Music

Download

Comments

abdiiiking
𝑎𝑏𝑑𝑖𝑖 :
🅰🅱🅳👑
2026-04-13 18:22:48
15
bereket.agaro
Bereket Agaro :
next
2026-06-16 17:27:02
0
mire.tesfaye
meri Love :
111
2026-05-17 16:53:57
0
user246616158
T𝙨𝙞𝙤𝙣🔥💊 :
2026-04-16 15:34:20
3
my.life.is11
my life is :
🥰🥰🥰
2026-05-30 07:51:42
0
abdelwhabmekiyou4
Abdu :
abdu😊
2026-04-25 15:26:43
0
helen_3626_aa
ሄሉ_ሮያል👑4k✨️ :
@DJKIRA_DMV @TEDDY AFRO @DJ WONDEM @AbduKiar_Official_✌️🥰🥰🙏🙏
2026-04-15 19:40:06
2
eyu9225
eyu :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-04-14 19:35:52
1
ermiyas_t
Ermiyas_t :
👍👍👍
2026-04-13 20:43:51
3
birukhailesilase1
ብሩክ ሐይለ ስላሴ ናኦድ :
😎😎😎
2026-04-13 18:35:46
2
baruiking
Barui King :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-04-13 18:33:57
2
anwar..arise.4.r.a
Anwar. arise 4 r Avar :
🥰🥰🥰
2026-04-14 13:29:55
1
yonijjj
yoni :
😂😂😂
2026-04-14 14:26:09
1
melattesga
ሜላት ተሰጋ :
🤩🤩🤩🤩👍👍👍👍👍
2026-04-14 17:08:56
1
jon952593
jon :
🥰🥰🥰
2026-04-14 16:04:28
1
abdii6759
@Abdii :
❤️❤️❤️
2026-04-14 13:12:04
1
sabee.kings
Sabee King's 👉💛💛💛💛👈 :
🥰🥰🥰🥰
2026-04-14 06:28:57
3
ms937312
ms olds :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-04-13 18:50:35
2
whoknows1105
it's me😎 :
🥰🥰
2026-04-14 06:46:13
1
ibrahimabdo226
Abdo [email protected] :
🥰🥰🥰
2026-04-14 18:39:22
1
960207588ea
ofta'ii Oromoo 💪💪🇲🇻🇲🇻 :
🥰🥰🥰
2026-04-14 07:34:45
1
usertmi1161hdz
mvxhdf :
💔💔💔💔💔💔💔💔🙏🙏🙏🙏
2026-06-18 00:02:41
1
nizaamu.daggu710824
nizo :
😂😂😂
2026-06-11 22:54:37
0
user47487805191296
salah dhinn :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-04-14 21:34:59
1
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About