@biruk.marshet: ዓርብ፦ ቤተክርስቲያን ይባላል። "…ትንቢት የተነገረለት፣ ሱባኤ የተቆጠረለት የጌታችን ከልደቱ እስከ ሞቱ ያደረገው የማዳን ጉዞ በመስቀል ላይ የተፈጸመበት፣ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪታይ ተገርፎ፣ የእሾኽ አክሊል ደፍቶ፣ እጅና እግሩን በችንካር፣ ጎኑን በጦር ተወግቶ ደሙ እንደ ጎርፍ አፈስሶ የመዳናችን ዐዋጅ የታወጀበት ዕለት ነው። "…ጌታ በመስቀል ላይ ሳለ የከበረ ደሙን ዑራኤል መልአክ በወርቅ ፅዋ ቀድቶ በዓለሙ ሁሉ ረጭቶታል። የጌታ ደም በነጠበበት ቦታ ሁሉ እግዚአብሔር ባወቀ ቤተክርስቲያንን ሠርቷቷል። ከጌታ ሞትና ትንሣኤም በኋላ ቢሆን ዛሬ ድረስ አዲስ ቤተክርስቲያን የሚታነጸው ደመ ክርስቶስ ከነጠበበት ስፍራ ነው። ቤተክርስቲያን የወልደ እግዚአብሔርን ፍጹም ሰው መሆንና ፍጹም አምላክ መሆን አምነን፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ተወልደን በስመ ሥላሴ ተጠምቀን ሐብተ ወልድና ስመ ክርስትና አግኝተን፣ በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉድ ተብለን ተጠርተን የምንኖርባት የአምላካችን ቤት ናት። "…ቤተ ክርስቲያን ድንገት የተመሠረተች አይደለችም። ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና ታስባ፣ በዓለመ መላእክት ተወጥና በአማን ጐልታ፣ ግዘፍም ነሥታ የተመሠረተችው ግን በዕለተ አርብ በደመ ክርስቶስ ተቀድሳ፣ በትንሣኤው ከብራ፣ ንጽሕትና ጽሪት ባደረጋት ጊዜ ነው። ክርስቶስ ሞቶ ባይነሣ ኖሮ ግን ቤተክርስቲያን ሕልውና አይኖራትም ነበር። "…ከአዳም መውደቅ በኋላ ለ5,500 ዓመታት በሲዖል ተግዘው የነበሩ ነፍሳት ከዓመተ ፍዳ ዓመተ ኩነኔ የጌታ ደም ፈሶላቸው የትንሣኤው ብርሃን ደርሷቸው ከዲያብሎስ አገዛዝ ነጻ የወጡበትና ገነት የገቡበት ቀንም ስለሆነ ዕለቱ እንዲህም ተዘክሮ ይዋላል። ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሰላም።

ብሩክ ማርሸት-BIRUK MARSHET
ብሩክ ማርሸት-BIRUK MARSHET
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 17 April 2026 07:57:42 GMT
2845
511
10
84

Music

Download

Comments

user4792085081408
ጋሻው :
አሜን አሜን አሜን
2026-06-20 11:44:40
0
legastsegaye
ሰው መሆን ይቀድማል💟🙏💟 :
Amen 🙏 🙏 🙏
2026-04-18 03:56:58
1
user2320209063884
emebet :
አሜን🙏🙏🙏
2026-07-07 08:15:16
0
mebrat.meki
Mebrat meki :
አሜን አሜን አሜን 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-01 10:08:47
0
million.getahun
ሚሊዮን☦️ :
አሜን
2026-05-16 20:09:59
0
user2061122783495
ማርያም እናቴ :
አሜን አሜን አሜን 🙏🙏🙏
2026-04-17 12:26:25
0
user11502420992353
abushe ficha :
🥰🥰🥰
2026-05-15 17:48:24
0
heronketema0996931568
እግዚአብሔር ሆይ መንገደን አሳየኝ :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-07 08:52:33
0
user9943621981154
muluneh :
🥰🥰🥰
2026-04-17 19:33:48
0
adu6860
adu love :
❤️❤️❤️
2026-05-18 15:43:39
0
To see more videos from user @biruk.marshet, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About