@admaelpray7: *የ "7" ቁጥር ነገር እጅግ በጣም እያስደነቀኝ ነው።በጥቅሉ አለም የተፈጠረችው በቁጥር ነው።እግዚአብሔር ሰማይና ምድር ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ።ሰባተኛዋን ቀን ባረካት፤ቀደሳትም፤ሊፈጥረው ከጀመረው ሥራ ሁሉ በእርስዋ ዐርፎአልና። *እስካሁን በዓለም ላይ ከ900 አመት በላይ የኖሩ ሰዎች 7 ብቻ ናቸው። 1.አዳም 930 አመት 2.ሴት 912 አመት 3.ሄኖስ 905 አመት 4.ቃይናን 910 አመት 5.ያሬድ 962 አመት 6.ማቱሳላ 969 አመት 7.ኖኅ 950 አመት *አዳም የተፈጠረው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ተብሎ ይታመናል።የአፈር ዝርያዎች በራሱ 7 ናቸው።ከሰባቱ አዳም የተፈጠረው "ስውሩ አፈር" በተባለው ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ይገኛል።አፈሩ ከተገኘ ፍቱን መድሀኒት ነው ይባላል። *እግዚአብሔር አዳምን ፈጠረ፥አዳም ሴትን ወለደ።የኖረበት ዘመን 930 ዓመት ሆነ፤ሞተም። *ሴትም ሄኖስን ወለደ።የኖረበት ዘመን 912 ዓመት ሆነ፤ሞተም። *ሄኖስም ቃይናንን ወለደ።የኖረበት ዘመን ሁሉ 905 ዓመት ሆነ፤ሞተም። *ቃይናንም መላልኤልን ወለደ።የኖረበት ዘመን 910 ዓመት ሆነ፤ሞተም።ልጁ መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኋላ 895 ዓመት ሆነ፤ሞተም።መላልኤል 900 ዓመት አልሞላውም። *ያሬድም ሄኖክን ወለደ።የኖረበት ዘመን ሁሉ 962 ዓመት ሆነ፤ሞተም።ሄኖክ በምድር ላይ የኖረበት ዘመን 365 ዓመት ሲሆን ከዛ በኋላ በበጎ ሥራው እግዚአብሔርን ሰውሮታል። ሄኖክ በራሱ ከአዳም ጀምሮ 7ኛ ትውልድ ነው።በገነትም ሰባቱን ሰማያት አይቷል። 1. ጽርሐ አርያም 2. መንበረ መንግስት 3. ሰማይ-ውዱድ 4. ኢየሩሳሌም-ሰማያዊት 5. ኢዮር 6. ራማ 7. ኤረር የሚባሉትን። *ሄኖክ ከመሰወሩ በፊት ማቱሳላን ወለደ።ማቱሳላም ላሜሕን ወለደ።የኖረበት ዘመን 960 ዓመት ሆነ፤ሞተም። *ላሜሕም ኖኅ'ን ወለደ።ላሜሕ የኖረበት ዘመን 747 ዓመት ሆነ፤ሞተም። *ኖኅም 3 ልጆችን ወለደ፤እነርሱም ሴም፥ካምና ያፌት ናቸው።በኖኅ ዘመን በሰዎች ክፋት ምድር በማየ አይኅ ተደመሰሰች።ከ40 ቀን በኋላ ምድር ደረቀች።ኖኅ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረበ፤እግዚአብሔርም ለኖኅ ቃልኪዳን ሰጠው።ኖኅም ከጥፋት ውኃ በኋላ 350 ዓመት ኖረ።በጠቅላላ የኖረበት ዘመን 950 ዓመት ሆነ፤ሞተም። *እናም እስካሁን በምድራችን የ7ቱን ሰዎች ያህል ከ900 ዓመት በላይ የኖረ የለም፤ወደፊትም አይኖርም ከስዎራን በቀረ። አግልግሎት ለመደገፍ በጸሎት ለሚታሰብ 1000128077107

ቤዕንተ ቅዱሳን የአበው የጸሎት  ማህበር 7
ቤዕንተ ቅዱሳን የአበው የጸሎት ማህበር 7
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 23 April 2026 04:48:56 GMT
33401
770
6
257

Music

Download

Comments

mekonengeta
Mekonen Meki :
የዘመን ይምጣልን
2026-04-23 05:42:18
0
astu.1926
astu 19 :
ማውረድፈልጌ አልወርርድአለኝእድወርድአርጉት
2026-06-01 17:15:26
0
user676753761
Fantaye Tigabu :
🥰🥰🥰
2026-05-20 08:50:27
1
sma.belewu
ቤተ አማራ :
♥️♥️✝️✝️
2026-05-29 14:35:06
1
terefe.kifle4
Terefe Kifle :
😳😳😳
2026-06-02 18:50:11
0
To see more videos from user @admaelpray7, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About