@musictube369: መርከብ ⚓😇 ✍️ቴዲ በአንድ ስንኝ ውስጥ ብዙ ሚስጥሮችን የመሸሸግ ልምድ አለው። በተለይ ደግሞ መርከብ ላይ የተጠቀማቸው ቃላቶችና የዜማው ቅኝት መልእክቱን ከባድ አድርገውታል። ተፈልፍለው ነው የሚገኙት👌 መርከብ ውስጥ የተሳፈረችው ሲመለዲዴ/Si malee dide! 🇪🇹 ክቡር ዶክተር የግጥም እና ዜማ ደራሲ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ይሄ ዛሬ የጋበዝኳቹ የቴዲ አፍሮ “መርከብ” በተለያዩ ሰዎች ዘንድ የተለያየ ትርጉም መሰጠቱ የቴዲ አፍሮ የግጥም አጻጻፍ ስልት ውጤት ነው። ቴዲ ብዙውን ጊዜ ግጥሞቹን በምሳሌያዊ ንግግሮች (Metaphors) ስለሚሞላ፣ አድማጩ እንደራሱ ስሜትና አረዳድ እንዲተረጉመው እድል ይሰጣል። 📌ታዲያ ለሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ነው ያሉም አልጠፉም... ይህ መላምት በብዛት የሚነሳው በዘፈኑ ውስጥ የኦሮሚኛ ቋንቋ በጉልህ ጥቅም ላይ በመዋሉ ነው። ቴዲ በዘፈኑ ውስጥ የኦሮሚኛ ቋንቋን ሲመሌ ዲዴ/Simalee dide መጠቀሙ ለሟቹ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ያለውን አክብሮት ለመግለጽና ለማስታወስ መርከብ ውስጥ ጣል የተደረገች በሁለቱ ህዝቦች መካከል የፍቅር ድልድይ ለመገንባት የታለመ ነው ተብሎ መውሰድ ይቻላል። ምንም እንኳን ቴዲ በይፋ "ለሃጫሉ ነው" ባይልም፣ አድማጮች ግን የሁለቱን አርቲስቶች ታዋቂነትና የነበራቸውን ተጽዕኖ በማነጻጸር ዘፈኑን ከመታሰቢያነት ጋር ያያይዙታል። 📌የሌሎች እይታ ደግሞ የቴዲ አፍሮ የኋላ ታሪክና ቀደምት ስራዎቹ እንደ ያስተሰርያልና ናአት ዘፈኖቹን በፖለቲካ መነጽር እንድንመለከት ያደርጉናል። መርከብ የምትለው ኢትዮጵያንነው በውቅያኖስ (በአለም አቀፍ ጫናና ወይም በውስጥ ችግር) ላይ የምትናወጥን ሀገር እና ያንን ማዕበል አልፎ ወደ ሰላም ለመድረስ የሚደረግ ጥረትን እንደሚያመለክት ይተረጉሙታል። 📌እንደ ፍቅር ዘፈን ለብዙ አድማጮች “መርከብ” ንፁህ የፍቅር ዘፈን ነው። ሲመሌ ዲዴ/Si malee dide (ከአንቺ በቀር እምቢ አለኝ) የሚለው የኦሮሚኛ ሀረግ እና ሌሎች የፍቅር ቃላቶች ዘፈኑ ለተፈቀሪ የተዘፈነ ጥልቅ የፍቅር መግለጫ አስመስለውታል። ፍቅርን እንደ ውቅያኖስ፣ ተፈቃሪን ደግሞ በውቅያኖስ ላይ እንደምትጓዝ መርከብ በመመሰል የፍቅርን ጉዞና ጥንካሬ ይገልጻል። 💡በዘፈኑ ውስጥ የተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችንና ባህሎችን ማካተቱ፣ ቴዲ ሁልጊዜ የሚሰብከውን የ"ኢትዮጵያዊነት" እና የ"አንድነት" ፖለቲካዊ ፍልስፍና እንደሚያንጸባርቅ ይተጋል። ዘፈኑን ሲመረመር "ሰው ማለት መርከብ፣ አለም ውቅያኖሱ" የሚለው ስንኝ የዘፈኑን ፍልስፍና ይይዘዋል። ሰው በህይወቱ የሚያጋጥሙትን ማዕበሎች (ፍቅር፣ ፖለቲካ፣ ሞት) አልፎ የሚጓዝበትን የህይወት ጉዞ የሚገልጽ ይመስላል። ✍️ለመሆኑ እናንተስ ከነዚህ ሦስት ትርጉሞች የትኛው በበለጠ ይስማማቹሃል? ወይስ ሌላ የታያቹ የተለየ ትርጉም አለ? እኔ ግን በ6ኛ ሙዚቃችን እስክመለስ ጓጉቻለሁ😁 እድሜ ለንጉሱ በ18 ሙዚቃዎች ዓለሜን እየቀጨው ነው🤗 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 musictube 🇪🇹 #fyp #Ethiopianmusic #musictube369 #መርከብ #ቴዲአፍሮ💚💛❤
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Region: ET
Friday 24 April 2026 19:48:48 GMT
Music
Download
Comments
DAGIM 🧾 :
እኔ ለ ሀጫሉ በሚለው Agree 👌🇪🇹
2026-04-24 20:08:49
22
የራማው ልዑል ዋስ ጠበቃዬ :
አቦ ያንተ ስራ እራሱ ያምራል ✌️
2026-04-24 20:41:17
13
Ermiyas_t :
bro techelalek 🫡🎶🔥👌😘
2026-04-25 05:14:25
5
®Benyamer Kide®✌ :
The first comment giver☺️
2026-04-24 19:52:36
4
Buze_tsi_ab :
ignam abireni alemachinin iyekechen newu🙏🙏🙏
2026-04-26 12:56:01
1
ᴛᴇᴅᴅʏ☄️ :
king (GOAT)🐐
2026-04-25 19:20:22
2
ህሩይ የማነብርሀን💊💊💪 :
2026-04-25 03:57:07
5
hayelom araya :
Abate Zafane
2026-05-25 20:01:59
0
yirga genbawe :
2026-04-24 20:50:47
2
mikiyas Abinet :
bravo ሌላም ስራልን🙏🙏🙏
2026-04-25 06:57:49
1
aschalewtadele977 :
ሰወደው ኮ❤
2026-04-25 06:36:18
2
Sontera :
"ሲመሌዲዴ" የሚለው ቃል የተፃፈው በ 1 ቃል ብቻ መሆኑ ቴዲ የኦሮምኛውን ውርስ ትርጉም ሳይሆን የግእዙን ትርጉም መጠቀም የፈለገ ይመስለኛል:: so he's not singing about Hachalu rather he's telling us about his current frustration and his future plan 😔😔😔
2026-04-28 18:17:14
2
የጨለማው ዘመን :
ዘፈኑ ለኛ ለአማሮች ነው የተዘፈነው
2026-04-25 18:24:48
1
deja vu :
ተጨማሪ ሙዚቃ ቅንብር እና ኪቦርድ በረከት ተስፋግዚ ነው
2026-04-25 13:59:04
2
ቤቢ :
💪
2026-04-24 20:50:05
3
wenda :
❤️❤️❤️❤️❤️❤️🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-04-24 20:01:35
1
Nati :
🥰🥰🥰
2026-04-25 20:18:23
1
Ôl_Ąn✨ :
🤝🤝🤝
2026-04-25 16:08:48
1
ms olds :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-04-24 20:27:08
2
mihretu507 :
⚓🚢⚓🚢⚓🚢⚓🚢
2026-04-25 07:53:05
1
aschalewtadele977 :
❤❤❤
2026-04-25 06:36:07
1
abinezer :
🥰🥰🥰
2026-04-25 08:51:46
1
ሩት :
❤️❤️❤️
2026-04-25 07:39:09
1
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm
homepage.
© 2021-2026 TikWM. All rights reserved.