@israel.du: ***የሥላሴ አንድነት*** • በሥልጣን • በመለኮት • ዓለምን በመፍጠር • በአነዋወር(በአኗኗር) • በአገዛዝ • በሕልውና • በማሰብና በመናገር ፍፁም አንድ ናቸው፡፡ የሥላሴ ማለትም የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ የአንድነት መጠሪያቸው ‹‹እግዚአብሔር›› ይባላል፡‹‹እግዚአብሔር›› የሚለው ቃል የተገኘው፡ ‹‹‹እግዚእ››› ‹‹‹አብ››› ‹‹‹ሔር››› ከሚለው ሦስት የግዕዝ ቃላት ነው፡፡ ‹‹‹እግዚእ››› ማለት (ኢየሱስ ክርስቶስ) ‹‹‹አብ››› ማለት (እግዚአብሔር አብ) ‹‹‹ሔር››› ማለት ደግሞ ጠባቂ፣ ቸር፣ ሩህሩህ (መንፈስ ቅዱስ) ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት፡ • አብ እግዚአብሔር ነው • ወልድም እግዚአብሔር ነው • መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር ነው ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ብሎ ተናግሮ ይህን ቃል ለአብ ብቻ ነው ማለት በጣም ትልቅ ስህተት ነው ምክንያቱም ቃሉ የሦስቱም ፍጹም አካላት የአንድነት መጠርያ ነውና! የብዙዎችም የውድቀት መነሻም የእግዚአብሔርን ሥምና ትርጓሜን ያለማስተዋል ነው፡፡ ለምሳሌ ዓለምን ሲፈጠር አብ ብቻውን አልፈጠረም ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንጂ ማስረጃ፡- “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ” ዘፍ 1÷1 በዚህ አስተምህሮ ሥላሴ በአንድነት ዓለማትን እንደፈጠሩ በግልፅ ታውቋል፡፡ ***የሥላሴ ሦስትነት*** • በስም • በአካልና • በግብር (በሥራ) ***ሥላሴ በሥም ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ (ማቴ 28÷19)፡፡ ***ሥላሴ በአካል ሦስት ናቸው*** • ለአብ የራሱ መልክ ,ገፅ እና አካል አለው፡፡ • ለወልድም የራሱ መልክ ,ገፅ እና አካል አለው፡፡ • ለመንፈስ ቅዱስም የራሱ መልክ ,ገፅ እና አካል አለው፡፡ አብ እና መንፈስ ቅዱስ ረቂቅ አካላት ሲኖሯቸው የሚዳሰስስ እና የሚጨበጥ ግዙፍ አካል ያለው ግን ወልድ ብቻ ነው፡፡ ይህም በተዋህዶ ከድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ ነው፡፡ በአካል አብ ወልድን እና መንፈስ ቅዱስን መሆን አይችልም! ወልድም አብና መንፈስ ቅዱስን መሆን አይችልም! መንፈስ ቅዱስም አብና ወልድን መሆን አይችልም! ሦስቱ አካላት በአካል ቅልቅል የለባቸውም! ነገር ግን ሦስት አካል እንላለን እንጂ ሦስት አምላክ(መለኮት) አንልም! አንድም ሦስት ስም እንላለን እንጂ ሦስት እግዚአብሔር አንልም! *አብ*፡- አካላዊ *ልብ* ነው (የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ *ልባቸው* ነው) *ወልድ*፡- አካላዊ *ቃል* ነው(የአብ እና የመንፈስ ቅዱስ *ቃላቸው* ነው) *መንፈስ ቅዱስ*፡– አካላዊ *እስትንፋስ* ነው(የአብ እና የወልድ *ሕይወታቸው* ነው)፡ *ሥላሴ (በአብ) ልብነት ያስባሉ (በወልድ) ቃልነት ይናገራሉ (በመንፈስ ቅዱስ) ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ፡፡ *ሥላሴ በግብር (በሥራ) ሦስት ናቸው* + አብ፡- አባት(ወላዲ አስራጺ) ነው፡፡ (ወልድን ይወልዳል መንፈስ ቅዱስን ያሰርጻል) + ወልድ፡- ልጅ(ተወላዲ) ነው፡፡ (ከአብ ይወለዳል) + መንፈስ ቅዱስ፡- ሰራጼ ሕይወት ነው፡፡ (ከአብ ይሰርጻል) ***ነገር ግን*** -አብ አባት ቢባል ወልድን እና መንፈስ ቅዱስን በአኗኗርም ሆነ በሥልጣን ፍፁም አይበልጣቸውም! -ወልድም ልጅ ቢባል ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ በአኗኗርም ሆነ በሥልጣን ፍፁም አያንስም! -መንፈስ ቅዱስም ከአብና ከወልድ ጋር በሥልጣንም በአኗኗርም ፍፁም እኩል ነው! ***እንዲሁም*** -አብ ወልድን ስለወለደ እና መንፈስ ቅዱስን ስላሰረጸ ቅድምና የለውም! -ወልድም ከአብ ተወለደ ስንል ፍፁም አብን መስሎና አብን አክሎ ተገኘ ማለት ነው! -መንፈስ ቅዱስም ከአብ ሰረጸ(ወጣ) ስንል ፍጹም አብን መስሎና አብን አክሎ ተገኘ ማለት ነው! ‹‹‹የሥላሴ ሦስትነት የሚታወቅባቸው መንገዶች››› 1ኛ. በመላእክት ምስጋና “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር” ኢሳ 6÷1-3 ሦስት ጊዜ ቅዱስ ማለቱ የእግዚአብሔርን የአካል ሶስትነት ለመግለጽ ነው፡፡ አንዱ ቅዱስ ለአብ አንዱ ቅዱስ ለወልድ አንዱ ቅዱስ ደግሞ ለመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ በተጨማሪም ይህንኑ ቃል በራዕይ ዮሐንስ 4÷8-9 ላይ ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የነበረውና ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም” 2ኛ. በአብርሐም ታሪክ “እግዚአብሔር ለአብርሃም በመምሬ አድባር ስር ተገለጠለት” ዘፍ 18÷1:: ተገለጠለት ሲል አንድነቱን ለመግለጽ ነው፡፡ በመቀጠል ደግሞ “እነሆ ሦስት ሰዎችን በፊቱ ቆመው አየ” ዘፍ 18÷2 ይላል ይህም አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስን ነው፡፡አያይዞም ለተመለከታቸው ሦስት አካላት እንዲህ አለ “አቤቱ በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምንሀለሁ ጥቂት ውሃም ይምጣላችሁ” ዘፍ 18÷3-4:: እነዚህን (በፊትህ፣ አትለፈኝ፣ እለምንሀለሁ) የሚሉት ቃላት አንድነትን የሚገልጹ ናቸው ነገር ግን “ጥቂት ውሃ ይምጣላችሁ” የሚለው መደምደሚያ ቃል አብርሃም ለተመከታቸው ሦስት አካላት ማለትም ለአብ ለወልድ እና ለመንፈስ ቅዱስ ነው፡ 3ኛ. በተለያዩ ቦታዎች በተጻፉ የቃላት ድግግሞሾች “እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህም እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ ይራራልህም እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ ሰላምንም ይስጥህ” ዘሁልቅ 6÷24-26 ሦስት ጊዜ የእግዚአብሔርን ስም መጥራቱ የእግዚአብሔርን የአካል ሦስትነት ለመግለጽ ነው፡፡ አንዱ እግዚአብሔር ለአብ ሁለተኛው ለወልድ ሦስተኛው ደግሞ ለመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ በተጨማሪም በመዝሙር 117÷16-17 ላይ ያለውም ቃል ይህንኑ የሚያጠናክርልን ነው፡፡ “የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገች የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች” 4ኛ. በቅዱስ ጳውሎስ ምስክርነት “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ህብረት ከሁላችን ጋር ይሁን” 2ኛ ቆሮ 13÷14 5ኛ. በነቢዩ ኢሳይያስ ቃል “የጌታንም ድምጽ ማንን እልካለሁ ት.ኢሳ6÷8 ማንስ ይሄድልናል ሲል ሰማሁት”፡፡ ማንን እልካለሁ ሲል አንድነቱን ማንስ ይሄድልናል ሲል ሦስትነቱን ለመግለጽ ነው፡፡ 6ኛ. በዮሐንስ ራዕይ ምስክርነት “አየሁም እነሆ በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም የመንፈስ ቅዱስም ስም በግንባራቸው የተጻፈባቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ሰዎች ነበሩ” ራዕይ 14÷1-2:: 7ኛ. በክርስቶስ ንግግር “አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል” ኢሳ 48÷16:: • ጌታ እግዚአብሔር ሲል (አብን) • መንፈሱ ሲል (መንፈስ ቅዱስን) • ልከውኛል ሲል (ወልድ ተላኪ) ሆኖ ከሰማይ መውረዱን ያረጋግጣል፡፡ *እንዲሁም ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ ማገባደጃ ላይ “ሂዱና አህዛብን ሁሉ • በአብ • በወልድ እና • በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው” በማለት የጌታችንን ማሠሪያ ቃል ከትቦታል ማቴ 28÷19 :: ‹‹‹‹ የሥላሴ የሕብረት (የአንድነት) ሥራ ›››› 1) በፍጥረት ሥራ ውስጥ *አብ* ብርሃን ይሁን አለ ዘፍ1÷3 *ወልድ* ዓለም በእግዚአብሔር ቃል ተፈጠረ ዕብ 11÷3 *መንፈስ ቅዱስ* የእግዚአብሔር መንፈስ በውሃው ላይ ሰፍፎ ነበር ዘፍ 1÷2 2) በሥጋዌ *አብ* አነድያ ልጁን ሰጠ ዮሐ 3÷16 *ወልድ* ተወለደ ሉቃ 2÷11 *መንፈስ ቅዱስ* ድንግል ማርያም ለመፅነስ እንድትችል ፈቅዶ መጣ 2÷11 3) በመዋጀት *አብ* የቀራንዮን መስዋዕት ተቀበለ ዕብ9÷14 *ወልድ* እራሱን ቤዛ አደረገ ዕብ9÷14 *መንፈስ ቅዱስ* በዘለዓለም መንፈስ እራሱን ገለጠ ዕብ9÷14፡፡
እስራኤል
Region: ET
Tuesday 28 April 2026 19:27:04 GMT
Music
Download
Comments
Dan :
ቃለ ሕይወት ያሰማልን🙏
2026-05-01 15:17:06
3
geta hoy temesgen :
temesgen slasye amen
temesgen slasye amen
temesgen slasye amen
2026-05-01 20:30:46
3
True man :
በርታ/ቺ🥰🥰🥰🥰
2026-05-28 11:45:14
1
Getachew Eshetu :
2026-06-16 05:42:31
1
Eyosiyas Hailu :
ቃለሀሕወት ያሰማልን
2026-06-01 06:43:09
1
አጋቻ ይቦሪሤ ባረፐረ ሁዳዪሂር :
ምስጢረ ስላሴ የተማረ የትም ይደርሳል።ቃለ ህይወት ያሰማልን።
2026-06-08 15:02:16
1
ጓል ጊዮርጊስ 23 :
በርቱልኅ በምን እናግዛቹህ ❤️🌹❤️🌹
2026-04-29 12:54:38
2
Kifle Abraha :
amen amen amen
2026-05-03 12:46:41
2
Telahun Ber :
አሜና🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-25 01:22:05
0
Gebremedhin Geshey :
ስላሴ ዓለም
2026-05-01 09:31:13
1
tedy :
amen
2026-06-01 05:50:06
1
19 :
አሜን 🙏🙏🙏
2026-05-01 14:55:28
1
alexo@21 :
እግዚአብሔር ይስጥልኝ
2026-04-30 20:48:50
1
user4254571917959 :
Aeman
2026-05-03 14:20:19
0
user4254571917959 :
NJm aeman
2026-05-03 14:19:52
0
Misgie :
ቃለ ህይወት ያሰማልን
2026-05-01 10:07:01
2
ፍቅር 𝐋𝐚𝐛 :
መለኮት ምንድነው?
ባህሪይ ምንድነው?
አካል ምንድነው?
2026-04-30 18:11:33
0
a/s :
tebarkulne fexri yesexelne be unti yabzachu qale hiyote yasemalene tsegawune yabzalene be edeme be xena yetebeqelne🤲🙏
2026-05-01 16:44:30
0
@<ዲ/ን^`እሱባለዉ>^` :
😍😍😍
2026-05-17 08:55:35
1
yohannis :
🙏🙏🙏
2026-05-11 20:15:58
1
Binyam soliyana :
🥰🥰🥰
2026-05-04 16:33:30
1
#21አይዞህ ትለኛለች :
🙏🙏🙏
2026-05-01 18:47:31
1
yilekal :
🙏🙏🙏
2026-05-01 18:08:30
1
𝙶𝚂@23 :
🙏🙏🙏
2026-05-02 03:59:19
1
space :
🥰🥰🥰
2026-04-30 19:27:59
1
To see more videos from user @israel.du, please go to the Tikwm
homepage.