@shyred7: በስልክ ስናወራ የነገረችኝን ነገር አምኖ መቀበል ከበደኝ።እራሴው "ችግር የለውም ንገሪኝ" ብዬ አበረታትቻት ከነገረችኝ በኋላ መናገር አቃተኝ። ረዘም ላሉ ሰኮንዶች ዝም አልኳት። . . ግራ ተጋብታ "አውቃለሁ ደስ አይልም ግን በቃ ከሌላ ሰው ከምትሰማው እኔው ልንገርህ ብዬ ነው። ምንም ልደብቅህ አልፈልግም ስለኔ ሁሉንም ነገር ማወቅ አለብህ" አለችኝ። "እሱማ ልክ ነሽ ሀሳብሽ ይገባኛል በቃ ይሄን ነገር እንርሳው" ብዬ ምንም እንዳልመሰለኝ ለማስመሰል ሞከርኩ።ከዚህ በላይ ምንም ማውራት አልቻልኩም። ምላሴ ተሳሰረ። "በቃ በኋላ እደውልልሻለሁ" ብያት ስልኩን ዘጋውት። አንዳች ነገር ውስጤን ሲሰብረው ተሰምቶኛል። . . "የምወዳት ልጅ ከሌላ ሰው ጋር ተኝታ እንደነበር...የሌላ ሰው ገላ አቅፋ እንደነበር... እንዴት ነው አምኜ መቀበል የምችለው?" እራሴን እጠይቃለሁ። ከዚህ በላይ ነገሩን ከባድ የሚያደርገው ደግሞ አብራቸው የተኛቻቸው ሰዎች እኔ የማውቃቸው ሰዎች መሆናቸው ነው። ይሄን ሳስብ እልህ አይሉት ቅናት አላውቅም ግን እንባዬን አመጣው። በስለት እንደተወጋው ያህል ተሰማኝ። አመመኝ። . . "እኔ እጇን እንኳን ለመያዝ ይቅርና ለመንካት የምፈራውን ሌላው ግን...." ሀሳቤን ሳልጨርስ እንባ ቀደመኝ። "በቃ ቺት አደረገችብኝ ማለት ነው?" አልኩ። "ኧረ ይሄ ያለፈ ታሪኳ ነው" እራሴን ለማረጋጋት ሌላ ሀሳብ "ያለፈ ታሪኳስ ቢሆን እንዲ እያፈቀርኳት በእኔ ላይ??" አይምሮዬ ውስጥ የማያባራ መልስ የሌለው ጥያቄ ተፈጠረ። . . "ግን ለምን? ለምን በእኔ ላይ?" ብዬ ልጠይቃትም ፈለኩ። ግን ምን ዋጋ አለው ያለፈ ታሪኳ ነው። ባለፈ ታሪክ መወቃቀስ አይቻል። . . ችግር የለውም ንገሪኝ ብዬ እራሴን ችግር ውስጥ ከተትኩት። የእኔና የእሷ ነገር ብዙም እንደማይቆይ የተረዳሁት የዚህ ቀን ነበር። . . ሁላችንም ያለፈ ታሪካችን ያለፈ ቢመስለንም ሁሌም ይከተለናል። #fyp #fyppppppppppppppppppppppp #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #viral #viralvideo
ShyRed
Region: ET
Saturday 02 May 2026 07:14:31 GMT
Music
Download
Comments
amrela :
በጣም ከባድ ስቃይ ነው አይዞክ 🥺
2026-05-03 06:48:05
19
Tinishu Aposto :
yifexerall gin begize.raki🥰🥰
2026-05-05 15:37:57
4
Alexi :
እኔው እራሴ ነኝ 😒😣😣🥺😢
2026-05-21 12:56:57
5
𝐓𝐢𝐫𝐮 𝐁𝐚𝐫𝐛𝐞𝐫💈💈💈 :
2026-05-21 20:37:49
4
nazim :
አኔ ደሞ brakup kedergn ስንትመለስ ከሌለ ወንድ አንደ ተኝቻለሁ አላች rese እኮ ነው ንገረኝ biyet ግን አልቻልኩም ቡሀላ በጣም ከባድ ስሜት ነው አሁንም aln ግን አንደmalgbet ነገርኩት
2026-07-23 17:02:46
0
RiseUp🇨🇭 :
ይሄን ስሜት የሚያውቅ ያውቀዋል😔
2026-05-18 16:50:00
9
sun 🌞 :
hard
2026-05-03 10:20:35
3
Eyob💫 :
ይሄን ስሜት ሚረዳው የደረሰበት ብቻ ነው 🥺
2026-05-20 14:02:55
2
Rιgнт Perѕon💎⚡️ :
እኔ በጣም ነው ለ መጠየቅ ምሳቀቀው 💔
2026-05-23 12:46:41
1
yony :
ከባድ😳
2026-05-02 10:15:11
3
e_r_m_i_16 :
😌😌🥺
2026-05-31 16:32:35
1
To see more videos from user @shyred7, please go to the Tikwm
homepage.