@user2472469328662: + ከአፍ የሚወጣ እሳት + እባክዎ ጽሑፉን ለወዳጅዎ ያዳርሱ። "አፌ ይለፈልፋል እንጂ ውስጤ እኮ ንጹሕ ነው" አለች አባ ፊት ቀርባ - በክፉ ንግግርዋ ብዙ ሰው ያስቀየመች ሴት:: አባ መለሱላት :- ልክ ነሽ ልጄ እባብም እኮ መርዙን ከተፋ በኁዋላ ውስጡ ንጹሕ ነው! ምላስ አጥንት የለውም ነገር ግን አጥንት ይሰብራል:: እግዚአብሔር ምላስን እንደጆሮ ክፍት አላደረገም:: በከንፈርና በጥርስ ሸፍኖታል:: ትንሽ አሰብ አድርገን እንድናወራ ነው:: "ሰው ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን" የሚለው ቅዱስ ያዕቆብ ስለ አንደበት ሲናገር "ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል" እንዳለ የምላስ ኃይል እጅግ ከባድ ነው:: ከአፍ የሚወጣ እሳት ብዙ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል:: ሰው በዱላ ቢደበደብ ታክሞ ቁስሉ ያገግማል:: ክፉ ንግግር የሚያቆስለው ቁስል ግን በቀላሉ አይሽርም:: ዱላ የሚያርፈው ሥጋ ላይ ሲሆን መጥፎ ንግግር ግን ነፍስ ላይ ነው:: ክፉ ንግግሮች ሰውን ለጊዜው ብቻ ሳይሆን ለዘላለም ሊያመርሩት ይችላሉ:: (ሌላ ነገርዋን ትተነው) ሚሼል ኦባማ በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ በጣም ልብ የሚነካ ነገር ስትናገር ሰማሁ:: ስለወረደባት ስድብ ስታስታውስ "አንዳንድ ክፉ ቃላት የነፍስን ቅርፅ ይቀይራሉ" ብላ ነበር:: እውነት ነው በመራር ቃላት የነፍሳቸው ቅርፅ ከተቀየረ ስንቶች ናቸው:: የማይዘነጉት ንግግር እድሜ ልክ የሚያቆስላቸው : የአንድ ሰው ከባድ ስድብ በራስ መተማመናቸውን የነጠቃቸው : የአንድ ሰው "አትችልም" የሚል ድምፅ እጅና እግራቸውን ያሰራቸው እጅግ ብዙ ናቸው:: ሰው ለማሳቅ ተብለው የተሰነዘሩ "ትረባዎች"ና አጥንት ሰባሪ ቀልዶች ቂመኛ ያደረጉዋቸው ሰውን ሁሉ ያስጠሉአቸው ስንት ናቸው? በስድብ ብቻ የፈረሱ ቤቶች አሉ:: ስለተሰደቡ ብቻ በሕዝብ ላይ የሚፈርዱ ዘር እስከማጥፋት የተነሡ አሉ:: ተናጋሪው በጥፋታቸው ውስጥ ትልቅ ድርሻ እና ተጠያቂነት እንዳለው ግን ይዘነጋል:: እግዚአብሔርም "እንደ ዋዛ ለተናገራችሁት ቃል በፍርድ ቀን መልስ ትሠጡበታላችሁ" ብሎአልና ለሰዎች የምንሰነዝረው እያንዳንዱ ቃል ያስጠይቀናል:: በተቃራኒው ለሰዎች ጥሩ ቃል መናገርን ብዙ ዋጋ አንሠጠውም:: ለስድብ የማናቅማማ ሰዎች ለምስጋና ሲሆን ግን እንሽኮረመማለን:: ፊት ለፊት አሳምረን የምንሳደብ ሰዎች ለማመስገን ሲሆን "በፊትህ ማመስገን እንዳይሆንብኝ" እንላለን:: ሆኖም ብናወጣው ሰዎች የሚነገራቸው ጥቂት በጎ ቃል ሰብእናቸውን ይገነባል:: ፈጣሪ "ብርሃን ይሁን" ብሎ በቃሉ እንዳበራው ማድረግ ባይቻልህ እንኩዋን በጥቂት በጎ ቃላት የአንድን ሰው ቀን ማብራት ትችላለህ:: ከምንም ሥጦታ በላይ መልካም የምስጋና ቃላት በሰው ልብ የሚቀር ውድ ሥጦታ ነው:: ባል ለሚስቱ ከሚገዛው ሥጦታ በላይ "ባልዋም ያመሰግናታል" የሚለውን ቃል ቢፈጽምላት ደስታ ይሆንላታል:: ልጆች ከብዙ ሥጦታዎች በላይ ከወላጆቻቸው የሚሰሙት የፍቅር ቃል ይሠራቸዋል:: የእስክንድርያው ፊሎ ለልጅ አባትና እናቱ ከሀገሪቱ ንጉሥና ንግሥት በላይ ናቸው ይላል:: የንጉሥ ቃል የሹመት ቃል ነውና ልጆች በወላጆቻቸው የሚሰሙት "ጎሽ" የሚል ቃል ከፍ ያደርጋቸዋል:: "ልጅሽ ትምህርት የማይገባው ደደብ ስለሆነ ትምህርት ቤት አትላኪው" የሚልን ደብዳቤ "ልጅሽ በጣም ጎበዝ ስለሆነ እሱን ማስተማር ስለማንችል በቤት አስተምሪው" ብላ ያነበበች እናት ትልቅ ሳይንቲስት አፍርታለች:: ብርሃን ይሁን ! ምድር ታብቅል! ብሎ የፈጠረን አምላክ በአርኣያው ፈጥሮናልና በቃላችን የምናሳምም ሳይሆን የምንፈውስ እንሁን:: መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ "ወንድሙን የሚሰድብ ነፍሰ ገዳይ ነው" ብሎአል:: ስድብ ከመግደል እኩል ነው ሲል ነገሩን ለማግነን የተጠቀመው አገላለጽ ሳይሆን በእርግጥም መሳደብ ከመግደል ብዙም ስለማይለይ ነው:: ሀገራችን ላይ ያንዣበበው የዘር ጭፍጨፋ ብዙዎቻችንን ያሳስበናል:: እንደ ሩዋንዳ ልንሆን ነው? እንላለን:: ወዳጄ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት መነሻው እኮ የሚዲያ የጥላቻ ንግግር ነበር:: እውነት ለመናገር ዘር ነክ ስድቦችና በቀልድ መልክ የሚነገሩ የንቀት ንግግሮች ሁሉ የዘር ማጥፋት ዋዜማ ናቸው:: የጥላቻ ንግግር (hate speech) የዘር ማጥፋት እጅግ ወሳኙ መቆስቆሻ ነው:: ስለዚህ "በለው በለው" ብለህ በምትጽፈው comment ወንድሙን ከገደለው እኩል በፈጣሪ ፊት ትጠየቃለህ:: ቅዱሱ እንዲህ ይላል "እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል" ማቴ 5:22 በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ራሔል ዘ ቤተ ቅዱስ አማኑኤል ⛪
ራሔል ዘ ቤተ ቅዱስ አማኑኤል ⛪
Open In TikTok:
Region: AE
Saturday 02 May 2026 08:48:06 GMT
12993
734
80
376

Music

Download

Comments

user2315614705468
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን :
አሜን አሜን አሜን ቃለ ሂወት ያሰማልን መምህር ለኛም እግዚአብሔር ልቦና ይስጠን እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ አሜን አሜን አሜን🥰🥰🥰
2026-05-29 07:42:35
6
sara52929
sara :
አምላኬሆይ ማረኝ ይቅር በለኝ😭😭😭😭
2026-05-03 02:07:41
5
barekta4
አሜን ዘቤተ ቅዱስ አማኑኤል :
አሜን አሜን አሜን ቃለህይወት ያሰማል አቤቱ አባት ሆይ መስጠት ትችል የለ አሰተዋይ ልቦና ስጠን🥰🥰🥰
2026-06-01 10:06:27
2
bvvvg24
Mar :
አቤቱማርን ይቅርበለን😭🥰🥰🥰
2026-05-31 22:34:38
2
emu212053
የብሩኬ እናት🤴ዘ-ቤተ አማኑኤል🙏⛪️ :
የህይዎት ቃል ያሰማልን ብቻ ይቅር ይበለን🥺🥺🥺🙏🙏🙏
2026-05-02 14:20:27
2
hiwot.asmar
Hiwot asimare :
አቤቱ ይቅር በለኝ መዳህንቴ ለወደፈቱም ልቦናን ስጠኝ🙏🙏🙏🙏
2026-05-04 13:04:33
2
.absalat.ye.maram
💞🌿ማዳኑ ሲገርመኝ💞ልጁ አደረገኝ :
💞ቃለ ሕይወት የሰማልን 🙏 እናመሰግናለን የኛ እንቁ መምህራችን 🙏👏 🍃ለኛም እሚያስተውል አዕምሮ ይስጠን 🙏 🙏🙏🙏 🙏 አሜን🙏🙏🙏
2026-05-02 22:55:03
2
__107926
✝️የዮሐንስ ፍሬ✝️ :
ቃለ ህይወት ያሠማልን አባታችን በእውነት እርሜ ከጤና ጋር እግዚአብሔር ይስጥልን አሜን ፫🥰🥰🥰💐💐💐✝️✝️✝️
2026-05-03 06:28:09
1
tade.mlka
tade mlka :
አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር
2026-05-28 22:04:19
0
selamsisay85
Selam Sisay,(ጎንደሬዋ) :
አይ ወዮሽ ነፍሴ😳😭😭😭💚🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-05-17 18:00:32
1
user90669985320954
user90669985320954 :
amen amen amen ❤️❤️❤️❤️🙏🙏🙏
2026-06-01 13:44:10
0
fjvthf0
ማርያም እናቴ💒🙏 :
አምላኬ ሖይይቅር ይበለኝ
2026-05-03 04:18:52
1
gech.man341
Gech man 👨 :
አሜን በእዉነት ድንቅ ነዉ ቃለ ህይወትን ያሰማልን 🥰🙏
2026-05-26 08:43:02
0
samrawit.asegid
ሳምሪ የድንግል ማርያም ልጅ :
ቃል ህይውት ቃል በረከት ያስማልን 🙏🙏🙏🙏 መምህራችን 🙏🙏🙏🙏
2026-05-02 20:43:00
1
khadejh52
አርሴምዬ እናቴ :
ቃለህይወት ያሰማልን🥰🥰🥰🥰
2026-05-02 22:44:06
1
leul.t3
ኣብ ዝክሪ ሓሳበይ😌 :
ቃለ ሂወት ያሰማልን 🙏🙏🙏
2026-05-03 09:36:01
0
helaf23
helaf :
እግዚአብሔር ሆይ ማረን
2026-05-02 14:30:31
1
sewmolt1
የዳዊት ቤት እየበረታ ሄደ :
ጌታሆይ ይቅር በለኝ🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-17 10:53:38
0
ez.xc
የክርስቶስ እስረኛ ✝️🥰 :
ቃለ ህይወት የሰማልን🥺🙏
2026-05-12 22:44:12
0
ancseef
አምላኬሆይልባምሴትአድረገኝ :
🥰🥰🥰🥰ጌታሆይይቅረበለን
2026-05-11 17:51:58
0
shime12127
shime1212 :
አምላካችን ሆይ ይቅር በለን 🙏🙏🙏🙏
2026-06-01 08:04:54
0
user8852710234908
guesh gidey 26 :
ቃል ሂወት ያሰማልን 🥰🥰🥰🥰
2026-05-16 11:21:44
0
tzta12190
እመቤቴ ማርያም ምልጃሽ አይለየኝ 🙏🙏⛪⛪ :
ቃለ ህይወት ያሰማልን 🙏 እግዚአብሔር ምህረቱን ይላክልን🙏 አስተዋይ ልቦና ለሁላችንም ይስጠን 🙏
2026-05-16 06:40:28
0
ateyalekwyehun
🥀ተስፈኛዋ😘🥀 🛫🥀✈️ነኝ 💒ከ44 ደብር :
ቃለ ሀይወት ያሰማልን🥰🥰🥰🥰
2026-05-16 11:16:20
0
tit32221
ሚካኤል አባቴ ✝️❤ :
ማረን ይቅር በለን እግዚአብሔር ሖይ🥺😥😥
2026-05-03 10:23:00
0
To see more videos from user @user2472469328662, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About