@tesfakiroslioul: ልዑል አለማየሁ ሚያዚያ 5 ቀን 1853 ዓ.ም በደብተረ ታቦር ከተማ የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ እና የወይዘሮ ጥሩወርቅ ውቤ ልጅ ተወለዱ። ልዑል አለማየሁ እንግሊዞች እጅ ከገባ ቡሀላ ከእድሜው ለጋነት የተነሳ የሚጠብቀው እና የሚንከባከበው ሰው ሊኖር ግድ ነበር፡፡ ይህንን የተረዳው ጀነራል ናፔር አማርኛ አዋቂውን ካፕቴን ስፒዲና አለቃ ዝርዓት እና አቶ ገብረመድህን የተባሉ ሁለት ኢትዮጵዊያን ሞዚቶች ተመድበውለት፣ በመርከብ በ1860 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝ ጉዞ ጀመሩ። በጉዞውም ከስፒዲ ጋር የጠበቀ ወዳጅነትን በመመስረቱ ጀነራል ናፒየር ኢትዮጵያውያንን ሞግዚቶቹ እንዲመለሱ በማድረግ የአለማየሁን ሀላፊነት ለስፒዲ እንዲረከብ ወሰነ፣ እዛ አንደደረሰም ከእንግሊዝ ንግስት ቪክቶሪያ ጋር ተገናኘ፣ ንግስቲቱም ልዑሉ የፈለገውና ያሻው ይደረግለት ዘንድ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈች። ልዑሉ በመቀደላ የነበረውን እልቂት በመጠኑም ቢሆን በማየቱና የአባቱና የእናቱ ተከታታይ ሞትም በልጅ አዕምሮው ሊቀበለው ከሚችው በላይ ታውኮ ነበር። አንድ እንግሊዝ ሀገር ውስጥ በሚገኝ ሙዚየም ውስጥ ባለ የንግስት ቪክቶሪያ የእለት ማስወሻ ላይም ንግስቲቱ፡ “ምስኪኑ ልጅ አሁንም ፍርሀቱ አለቀቀውም፡፡ መቅደላ የነበረው እልቂት እና የአባቱን ሞት ስላየ ያ ነገር በአዕምሮው ይመጣበታል፡፡ “ የሚል ቃል ፅፋ እናገኛለን፡፡ ልዑሉ እንግሊዝ ሀገር ከደረሰ በኃላ ጠባቂው የነበረው ካፕቴን ስፒዲ የእንግሊዘኛ ቋንቋን ያስተምረው ጀመር፡ ፡ ንግስቲቱም የልዑሉን ሁኔታ በቅርበት ትከታተል ነበር፡፡ ስፒዲ ልጁን እንዳይጎዳው በማሰብም በስፒዲ ላይ የልዑሉን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተል ተቆጣጣሪ አስቀምጠውበት ነበር ይባላል፡፡ አንድ ግዜ ንግስት ቪክቶሪያ ስለ ልዑሉ በእለት ውሎ መመዝገቢያዋ ላይ ከመዘገበችው መሀል “ልጁ ጨዋ እና ውብ ልጅ ነው፡፡ ኬክ መብላት ደግሞ ይወዳል፡ ፡ የሰጠሁትንም ኬክ ሁሉ ጨርሶ በላ፡፡” የሚል አረፍተ ነገር ተፅፎ እናገኛለን፡፡ ንግስቲቱ በተደጋጋሚ ለዚህ እናት ለሌለው ልጅ እናቱ እኔ ነኝ ስትል ትደመጣለች፡፡ ለልዑሉም የተለየ አክብሮት እና ፍቅር ፤ ልዩ ትኩረትም እንደነበራት ድርሳናት ዘግበውታል፡፡ ምንም እንኳን ከንግስቲቱ ጋር የነበራቸው ወዳጅነት ከግዜ ወደ ግዜ እየበረታ ቢመጣም ከሀገሩ ሲወጣ አብሮት የነበረውን ካፕቴን ስፒዲን ግን ለአፍታም አልዘነጋውም ነበር፡፡ በየትኘውም ስፍራ ሲሄድ ስፒዲ አብሮት እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ ግብዣም ሲሄድ ሆነ ከልዑላን ልጆች ጋር እንዲጫወት ሲጋበዝ ስፒዲን ትቶ መሄድ አይሆንለትም፡ ፡ ቤተ-መንግስት ሲገባ እንኳን ስፒዲን አስከትሎ ነው፡፡ ስፒዲ እና አለማየሁ አብረው ይበላሉ አብረውም ደግሞ ይተኛሉ፡፡ አለማየሁን ለብቻው ማሳደግ የከበደው ስፒዲ ልጁን በማሳደግ ትረዳው ዘንድ ሚስት ለማግባት ወሰነ፡፡ ከዛም ወ/ሮ ኮታንን አገኘ እና አገባት፡፡ አለማየሁ እና ወ/ሮ ኮታንም ለመዋደድ ግዜ አልወሰደባቸውም ነበር፡፡ በ1861 ዓ.ም ስፒዲ ህንድ ሀገር በምትገኝ አንዲት ከተማ አዛዥ ሆኖ ስለተሾመ የ8 ዓመቱን አለማየሁን እና ሚስቱን ይዞ ወደዛው አቀና፡፡ በሄዱበት ሀገርም አለማየሁ ትምህርቱን መከታተሉን ቀጥሎ የነበረ ሲሆን ከመደበኛው ትምህርት በዘለለም ፈረስ ግልቢያ እና ሌሎች ስፖርቶችንም ያዘወትር ነበር፡፡ ልዑሉ በዚህ አይነት ከቆየ በኃላ ቻንስለር ሮበርት ሉዊ ልዑሉ የቀለም ትምህርት ላይ ከሚያዘወትር ይልቅ የወታደር ትምህርት ቤት ገብቶ የፈረስ ውትድርናን እንዲማር መደረግ አለበት ሲሉ ያቀረቡት ሀሳብ የልዑሉን ህይወት እስከወዲያኛው የለወጠ ነበር፡፡ ይህም ሀሳብ ተቀባይነትን ስላገኘ አለማየሁን ከስፒዲ ነጥሎ በመንግስት ቁጥጥር ስር ለማድረግ እና የውትድርና ትምህርቱን እንዲከታተል ተወሰነ፡፡ ይህ ውሳኔ ግን ለአለማየሁም ሆነ ለስፒዲ ከባድ ግዜ ነበር፡፡ ስፒዲ እና ሚስቱ አለማየሁን ላለመስጠት ከባድ ትግልን አደረጉ፡፡ ነገር ግን ትግላቸው ውጤትን አላስገኘላቸውም፡፡ ይልቁኑም አለማየሁ ወደ እንግሊዝ ሀገር እንዲመለስ ተወሰነ፡፡ ስፒዲም አለማየሁን ይዞ ወደ እንግሊዝ መጣ፡፡ የአለማየሁ አዲሱ አስተማሪ እና ጠባቂ እንዲሁኑ የተመረጡትም በአስተማሪነታቸው የተመሰከረላቸው እና በደግነታቸው የታወቁት ቄስ ብሌክ ነበሩ፡፡ ንግስት ቪክቶሪያም የአለማየሁን እና የስፒዲን ፍቅር ያውቁ ስለነበር ሁለቱን ቶሎ መነጣጠል አልፈለጉም፡፡ ይልቁኑም አለማየሁ ከቄስ ብሌክ ጋር እስኪላመድ ድረስ ስፒዲ አብሮት ይቆይ ስትል ፈቀደች፡፡ አዲሶቹ የአለማየሁ ጠባቂዎች አለማየሁ ስራ እንዲሰራ ወሰኑ፡፡ በወጣለትም ፈረቃ መሰረት በሳምንት ለ 31 ሰዓት ተኩል ያህል ማንኛውንም አይነት ስራ እንዲሰራ ተወሰነ፡ ፡ የስፒዲ ሚስትም ይህንን በመቃወም ጠባቂው ለነበሩት በቢዶልፍ ደብዳቤ ላከች፡፡ ቢዶልፍም ለሉዊ አለማየሁ አንዳንድ ግዜ እየሄደ ከስፒዲ ሚስት ጋር ግዜ እንዲያሳልፍ ሲሉ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ በትዕዛዙም መሰረት የስፒዲ ሚስት ከአለማየሁ ጋር እንድትውል ተፈቀደላት፡፡ ሚስቱም አብራ ውላ ያየችውን እንዲህ ስትል በደብዳቤ ገልጣለች፡ “ማደጉን ቁመቱ አድጓል፡፡ መልኩ ግን ገርጥቷል፡፡ አካላቱም ከስቷል፡፡ ዝምተኛ እና ጭምትም ሆኗል፡፡ ከወንዶች ልጆች ጋር እንዳይገናኝ እና ከእኩዮቹም ጋር እንዳይገናኝ ተደርጓል፡ ፡ ውጪ እየወጣም እንዳይዘል ታግዷል፡፡ እየደጋገመም ‘አብረውኝ የሚጫወቱ ልጆች አጣሁ፡፡ ቅዳሜ እና እሁድ ብቻ ከሁለት ልጆች ጋር አንድጫወት ይፈቀድልኛል፡፡ ሊያጫውቱኝ የሚመጡትም እነዚህ ልጆች ሁልግዜ እነሱ ብቻ በመሆናቸው ተሰላችተናል፡፡ በሌላ ቀን ግን የሌሎች ልጆችን እጅ አንኳን ጨብጬ አላውቅም’ ብሎኛል፡ ፡ ይህንን የመሰሉት ነገሮች ያበሳጩታል፡፡ እኔም ብሆን ይህን የሚበሳጭበትን ጉዳይ ለማስተው ጓደኛ ልፈጥርለት አልቻልኩም፡፡ እየደጋገመ የነገረኝም ‘ወንዶች ልጆች እፈልጋለሁ፡፡ የበለጠ እንድንዛመድም እፈልጋለሁ’ እያለ ነው፡፡ በምግብ አበላሉ በኩልስ እንዴት ነህ ብዬ ብጠይቀው ‘ምግብ አሁን አይበላልኝም፡፡ ምክንያቱም ውጪ ወጥቼ ስለማልዛለል እና ስለማልጫወት አይርበኝም፡፡ የምበላው በትንሹ ነው’ ብሎ መለሰልኝ፡፡ እኔ እንደማስበው አለማየሁ ደስተኛ እና በሚደረግለት የረካ ልጅ አይደለም፡፡” የስፒዲ ሚስት የፃፈችው ይህ ደብዳቤ ከንግስት ቪክቶሪያ ዘንድ ደረሰ፡፡ ንግስቲቱም ትንሹ ልዑል አብሮአቸው ሊጫወት የሚችሉ ጓደኞች እንዲፈለጉለት አዘዘች፡፡ እንደተባለውም ተደረገ፡፡ 1867 ዓ.ም አለማየሁ ወደ ራግቢ ትምህርት ቤት ተዛወረ፡ ፡ በዚህም ከቄስ ብሌክ ቤት ወጥቶ ወደ ሊው ዋርነር ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በዚህ ግን ደስተኛ ስላልነበር በቀጣዩ አመት ሚስተር ድራፐር ቤት እንዲኖር ተደረገ፡፡ ቄስ ብሌክም ካዩት የልዑሉ ባህሪ በመነሳት ልዑሉ ወታደርነት ላይ ቢያተኩር የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ተናገሩ፡፡ በዚህም ንግግር መሰረት የወታደር ትምህርት ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በአንድ ወቅት አለማየሁ ወደ ሊድስ በመሄድ በሰር ራምሰን ቤት ተቀምጦ በነበረበት ወቅት በመርዝ ተመረዘ። መርዙ ህዳር 5 ቀን 1872 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3 ሰዓት ከሩብ በተወለደ በ19 ዓመቱ ከዚህ አለም እንዲሰናት አደረገው፡፡ አስከሬኑም ዊንድሶር ባለው የነገስታት መቀበርያ በክብር አረፈ፡፡ በመቃብሩም ላይ “የሀበሻው ልዑል አለማየሁ” የሚል ፅሁፍ ሰፍሮበት እስካሁን በእንግሊዝ ሀገር ይገኛል፡፡#CapCut

Tesfakiros Lioul
Tesfakiros Lioul
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 04 May 2026 10:00:04 GMT
42052
1783
36
418

Music

Download

Comments

amaremolla16
Tewodros Vision :
thanks bro,,, the flow of the story with the classical is so amazing! plus to that this story is not lay man story rather this is one for his mother hero Emperor Tewodros's son Prince Alemayehu....thanks once again...God bless u 🙏🙏🙏🙏✍️
2026-05-05 21:19:04
4
dessuzbetta
Estif & Yoni :
I feel his pain and stress
2026-05-14 14:38:06
3
mengistudeg
money speaks :
i feel bad
2026-05-06 18:20:54
4
pa_pa.com
የእብድ መንደር :
😳 ohhhhh shit
2026-05-20 19:02:26
0
adkebraraw29
AD Kebraraw :
Thank you
2026-05-25 14:09:12
0
mule38093
mule :
i feel sorry
2026-05-24 07:07:11
0
fake.life6664
kal Gonderew :
i feel sorry 🥰🥰
2026-05-22 19:00:05
0
muhabawgedefaw
Muhabe :
Amazing expression
2026-05-11 23:49:26
1
endrisyasuf
@ahmed266 :
ያሳዝናል
2026-05-27 19:39:30
0
zelalem.niber.zol
zelalem niber belay :
berta
2026-06-06 02:50:46
0
yohannes.mebratie0
Yohannes Mebratie :
I admire
2026-05-10 15:01:10
1
21..23gg
user21232729 :
በርታ
2026-05-08 17:44:56
1
bereket.sitotaw
Bereket Sitotaw :
thanks
2026-05-06 20:38:36
0
gizelekuku
ጊዜ (gize) :
የኔ ከርታታ😭
2026-05-11 09:15:16
1
oneday.fentie
Oneday Fentie :
i ethiopia
2026-05-04 19:37:42
2
usergebriye
Gebriye Keskis :
አይ ጉድየ!😭😭😭😭 ያኔ ጀግና አባቱ ይህን አለማየቱ😭😭😭
2026-05-25 17:17:36
0
user15172279490857
Abebe smada :
በርታ፡ወድሜ
2026-06-10 05:34:40
0
mesfine2323
Mesfine23 :
እግዚአብሔር ያክብርህ። የሚገርም እውቀት ሸመትኩኝ🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰ምናለበት አድጎ የሆነ ዘር ቢተካ ኖሮ😭😭😭😭😭😭
2026-06-01 07:14:11
0
mikiyas.ayalew6
Birtu :
😭😭😭😭😭😭😭
2026-05-07 08:43:54
1
tige1234q
tige :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-06 07:11:33
1
dastal080818
Gafat(Sevastopol) :
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-05-06 18:14:06
1
ashenafi.melese50
Ashenafi Melese :
😭😭😭😭😭😭
2026-05-06 06:14:01
1
petros.asnakew
ሁሉ በእርሱ ሆነ :
😭😭😭😭😭
2026-05-05 20:10:03
1
black.man2629
black man :
😭
2026-05-05 19:19:28
1
getachewbante12
gonderew💪💪👈 :
🥰❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-05-05 08:25:45
1
To see more videos from user @tesfakiroslioul, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About