@kibrekidusan15: የታሪካዊው ምሁር ኢየሱስ ገዳም አዲስ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ። ለዘመናት የሊቃውንት መፍለቂያ ሆኖ የቆየው ጥንታዊው የምሁር ኢየሱስ ገዳም፤ በዛሬው ዕለት ሚያዚያ ፳፬ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ ያስገነባውን ዘመናዊ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት አስመርቋል። የሊቃውንት መፍለቂያና የታሪክ ማኅደር የሆነው በታላቁ አባት በአቡነ ዜና ማርቆስ የተገደመው ይህ ገዳም፤ በቅኔ፣ በድጓ፣ በቅዳሴና በመጻሕፍት ትርጓሜ ጥልቅ ዕውቀት ያላቸውን ሊቃውንት በማፍራት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለውለታ ሆኖ የቆየ መንፈሳዊ የከፍተኛ ትምህርት ማዕከል ነው። ገዳሙ በርካታ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍትንና ንዋያተ ቅድሳትን በውስጡ አቅፎ ይዟል። ገዳሙ ከመንፈሳዊ ተልዕኮው ባሻገር፤ በሐዋርያትና በወልቂጤ ከተማዎች ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ ፲ኛ ክፍል የሚዘልቁ የትምህርት ተቋማትን እንዲሁም የእንግዳ ማረፊያዎችን በማስገንባት የአካባቢውን ማኅበረሰብ በስፋት እያገለገለ ይገኛል። በዛሬው ዕለት የተመረቀው አዲሱና ሰፊው ቤተ ክርስቲያንም፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የገዳሙ ቤተ ሰቦችና በጎ አድራጊዎች ባደረጉት ከፍተኛ የገንዘብ፣ የዕውቀትና የጉልበት ድካም ለፍሬ የበቃ መሆኑ ተገልጿል። በምረቃው መርሐ ግብር ላይ፦ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናንና እንግዶች ተገኝተዋል። የበዓሉን ድምቀት ልዩ ያደረገው ከአካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል በተጨማሪ፣ ፖሊሶችና የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የሚጥለውን ዝናብና ነፋስ ተቋቁመው ያደረጉት ደማቅ የአጀብ ጉዞ ነው። ከምረቃው ጎን ለጎንም የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ካልኣይ የመታሰቢያ ሐውልትና የገዳሙን ቅርሶች የሚጠብቅ ቤተ መዘክር ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
kibrekidusan tekle
Region: ET
Thursday 07 May 2026 11:55:11 GMT
Music
Download
Comments
የተዋህዶ ልጅ :
2026-05-17 09:10:16
0
Nati የልደታ ሊጅ 2119 :
እግዚያብሄር ይመስገን 🙏🙏🙏
2026-05-07 15:30:22
1
27 መድዬ 21 እምዬ :
እግዚአብሔር ይመስገን 🥰🥰🥰
2026-05-08 04:46:32
1
Mussie Haile :
የአቡነ ዜና ማርቆስ በረከት ይደርብን🥰🥰🥰
2026-05-07 12:01:30
1
mekdi@16እናቴ :
ተመስገን❤️
2026-05-08 04:29:36
1
SA :
ተመስገን ጌታዬ ክብር ለአንተ ይሁን!!!
2026-05-07 14:14:11
1
መ/ር ሄኖክ ገ/ማርያም :
እጅክ ይባረክ ክቡር ወንድሜ፥ፍጻሜክ ያሳምር።
2026-05-08 03:28:58
1
ተክለ አብ ንቤነ :
አድሜ እድሜ ይስጥልን
2026-05-08 05:38:36
1
Gedamuuu t2g :
mdrawi genet🥰🥰🥰
2026-05-08 08:17:44
1
mastewal yfatu :
hedeh neber wendm alem
2026-05-07 12:38:11
2
REDI YEMEDEN :
🥰🥰
2026-05-08 06:25:04
1
bina 133🤬 :
🙏🙏🙏
2026-05-07 12:02:04
1
Esube :
🙏🙏
2026-05-07 12:09:02
1
𝐌𝐞𝐤𝐝𝐢♏ :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-07 13:14:04
1
The sky :
❤️❤️❤️
2026-05-07 17:47:08
1
bina 133🤬 :
🥰🥰🥰
2026-05-07 12:02:09
1
የ ማር ያም ት ከ :
❤️❤️❤️❤️
2026-05-23 19:26:39
0
To see more videos from user @kibrekidusan15, please go to the Tikwm
homepage.