@musictube369: ሃሳብ የለሽም 🤌🤤 ✍️ከልጅነት ዕድሜው አንስቶ ዕድገቱ በቤተክርስቲያን የተቃኘ ሲሆን፤ የቅዱስ ራጉሄል የሰንበት ት/ቤት መሪ ዘማሪ ሆኖም አገልግሎዋል። ምንም እንኩዋን ሙዚቃ ስሜቱን አሸንፋ ብትወስደውም ዛሬም ግን ከእምነቱና ከሃይማኖቱ የራቀ ሰው አለመሆኑ ይመሰከርለታል በ1990ዎቹ ከተፈጠሩ ልዩ ድምፃዉያን አንዱ ሲሆን ባቀረባቸዉ አራት የሙዚቃ አልበሞች እና በርካታ ነጠላ ዜማዎቹ የአድማጩን ቀልብ መሳብ የቻለ የጥበብ ሰዉ ነዉ ከቀላል የፍቅር ዘፈኖች ባሻገር የኢትዮጵያ ህዝቦች ስነዉበት የጋራ ህይወት ገፅ በሚስሉና በሚያስቃኙ ዜማዎች የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ዳስሷል ኢቫንጋዲ, ላሊበላ, ባላገሩ, ድሬ ድሬ, ኮያባባ, ኢትዮጵያዬ, አኬልዳማ የሚሉት ከብዙ በጥቂት ይጠቀሳሉ ከዚህ ባሻገር ድንቅ የዜማና ግጥምም ደራሲ ነዉ ከራሱ በተጨማሪ ለብዙአየሁ ደምሴ ግርማ ተፈራ ካሳ ኤፍሬም ታምሩ አለማየሁ ሂርጶ ና እዮብ መኮንን በልዩነት የተደመጡላቸውን ዉብ ዜማዎችን ደርሷል በተለይም በሚደርሳቸው ዜማዎች እጅግ ልህቀትን አሳይቷል መረዋ ድምፁን ወደድኩሽ አፈቀርኩሽ በማለት ብቻ አላባከነዉም ይልቁኑም የማህበረሰብ ህፀፅን በሚተቹ ዜማዎቹም ጭምር እንጂ የኤች አይ ቪ ኤድስ የትራፊክ ደህንነት የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን ያለእድሜ ጋብቻ ላይ ያተኮሩ ቁም ነገር አዘል ስራዎቹን ማንሳት ይቻላል ከዚህ ባሻገር ጎሳዬ በሙያዉ የተለያዩ ተደናቂነትን ና ተሰሚነትን እጩነትን ማግኘት የቻለ ሲሆን ለአብነት ያህል እንደ አዉሮፓዉያን አቆጣጠር በ2008 የሙዚቃ ትርኢቱን ለማሳየት ወደኒዉዮርክ ብቅ ባለበት ጊዜ ሰፊ ተነባቢነት ባለዉ ኒዉዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ስለመድረክ ብቃቱ በአምዱ ላይ አስፍሯል በሌላ በኩል እ.አ.አ በ2012 በዱባይ በተሰናዳዉና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተዉጣጡ ስምንት ዓለምዓቀፍ ምርጥ ድምፃዉያን በአንድ መድረክ በተጣመሩበት ቪቫ አፍሪካ በተሰኘዉ የታላቁ የመካከለኛዉ ምስራቅ አፍሪካ የሙዚቃ ፌስቲቫል ኢትዮጵያን በመወከል እጩ ለመሆን ችሏል ከሙያዉ ባሻገር የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ከሚሳተፉ ጥቂት ደግ ልብ ካላቸው ድምፃዉያን መካከል አንዱ ነው። የዛሬው ተመስጋኝ ባለታሪካችን እጅግ ተወዳጁ ድምፀ መረዋው የዜማ እና ግጥም ደራሲ ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ በ1991 Take Five በተሰኘው አልበም ፈንጥቆ ያንፀባረቀ ጊዜ.... ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ አሜሪካ ሆኖ ነበር......« ይህቺ ቅመምና ድንቅ የሆነች ክስተት ምናለ እዚህ ብትመጣ እና ባወኳት?» ሲል ነበር የተሰማውን የአድናቆት ስሜት በወቅቱ የተናገረው። ብዙም ድምፁ የማይሰማውና ራሱን ደብቆ የመኖር የተፈጥሮ ባህሪይ ያለው፣ ኤፍሬም ድምፃዊ ሲያደንቅ የመጀመሪያው ነበር ማለት ይቻላል። ምን ማድነቅ ብቻ.....የትውልድ ክፍተት ሳያግደው ከጎሳዬ ጋር አብሮ አላቀነቀነም? ኤፍሬምን የሚያክል ለስሙም ሆነ ለክብሩ የሚጨነቅ ስብዕና ያለው ድምፃዊ፣ ከጎሳዬ ጋር ድምፁን አጣምሮ የዘፈነው እኮ ብቃቱ ከይፎት እንጂ ድርድር የፈጠረው ጥምረት አይደለም። የኤፍሬም ትውልድን ትተን ጎሳዬ ሳይወለድ በሙዚቃው የነገሰው ጋሽ ማህሙድ እኮ የዝናውን መጠን ለጥጠን ካየነው ከጎሳዬ ጋር አንድ ዘፈን ተጣምሮ አብሮት ሊሰራ ይቅርና፣ በግል ማውራቱ በራሱ ትልቅ አጋጣሚ ነው። ግን የጎሳዬ ድምፅን በአክሲዮን ሸሪክ አርጎ በጋራ ቅኝት ማዜም የታሪክ አንዱ አካል ሆኖ ስምን ይበልጥ ማተለቅ ነው። ይህ ብቻ ግን አይደለም ..... ከአንድም ሶስቴ «የኮንሰርት ተጣማሪሽ ማን ይሁን?» ተብላ የሶል ንግስቷ አስቴር_አወቀ በፕሮሞተሮች ስትጠየቅ ደጋግማ «ጎሳዬ ይምጣልኝ!» ያለችው ግዙፉ ዝናዋ ግርዶሽ ሆኖ ሳይከልላት ነው። የጎሳዬ ድምፅ ምንም ነገር ያስረሳል!.... የዕድሜ፣ የትውልድ፣ የዝና እና አንጋፋ የመሆን ክባድን ደርምሶ ማንንም ባለሙያ እጅ እንዲሰጥ የሚያደርገው የጎሳዬ ድምፅ የማይወጣው አቀበት፣ የማይወርደው ቁልቁለት የለም። ልጅ እያለን በፒያኖ «I Will always Love You» የተሰኘውን የዊትኒን የቦዲጋርድ ፊልም ማጀቢያ ሙዚቃን ሲያንጎራጉር ያወጣው የነበረው ቅላፄና_እንጉርጉሮን ባስታወስኩት ቁጥር «ምናለ ከዊትኒ ጋር ይሄን ዘፈን በቅብብሎሽ የሚያቀነቅኑበት መድረክ ቢፈጠር ኖሮ?» የሚል አድማስ ነጠቅ ምኞት ይፀናወተኛል! ይሄን ምኞት የፈጠረብኝ ተራ ቅዥት ሳይሆን የጎሳዬ ድንቅ ክህሎት ነው። «ይችላል!!» ብቻ አይገልፀውም። የፈለገውን ዘፈን ጎሳዬ ራሱ ባለቤቱ እስኪያጨበጭብለት ድረስ አስመስሎ ሳይሆን ሆኖ የመጫወት ብቃቱ ይገርመኛል። አንዳንዴ « ይሄ ልጅ በጉሮሮው ውስጥ ስንት የድምፅ ቀለማት አሉ?» እስክል ያመራምረኛል። አንድ ሰው የሆነ ሰው ዘፈን ቢያምርበት፣ የሌላው ደግሞ «ተው ይቅርብህ» ተብሎ ሊገሰጽ ይችላል። ጎሳዬ «ተዉ» የሚሉት ልጅ አይደለም። የትኛውንም ዘፈን ከፈለገ በድምፃዊው ከለር፣ ካሻም ራሱ ከለር ሰጥቶት አድማጭን መቆጣጠር ይችላል። የጋሽ ጥላሁንን «የጠላሽ ይጠላ!» የሚለውን ለስላሳ ዜማ በፊት ናይት ክለብ ውስጥ ሲጫወት የቤቱን ንግድ ፈቃድ አስቀይሮ ሱፐር ማርኬት ያደረገው ይመስል ነበር! ቤቱ ፀጥ ይላል!..... እስኪበቃው ጠጥቶ የሰከረው ሰው ጎሳዬ ይሄን ዘፈን ሲጫወት ኖርማል ይሆናል። ቤቱ በጠብደል ጋርዶች ሥርዓት አልይዝ እንዳላለ በጎሳዬ የጋሽ ጥላሁን ዜማ በአንዴ ፀጥ ይላል😁። ከየትኛውም ጫፍ ብርጭቆ «ቃ» እስኪል በሚሰማበት የተመስጥዖ አየር ውስጥ፣ ጎሳዬ ድምፁን ከፕላኔት ፕላኔት በሚመስል አኳሃን እንደመንኩራኩር ያመጥቀዋል። አንዴ ዝቅ! አንዴ ከፍ! በሚል የሜዞና_ሶፕራኖ የሙዚቃ ስልት የተቃኘውን ይሄንኑ «የጠላሽ_ይጠላን!» የጋሽ ጥላሁን ዜማን..... እንደተፈቀደለት ዲፕሎማት ሳይጨንቀው የሚንሸራሸርበት ጎሳዬ ዘፈኑን የሚገልፅበት ድራማቲክ ዘዬው በራሱ ይማርካል። አንድ ቦታ ቆሞ ዘፈኑን አይዘፍነውም! ገመድ አልባ ማይኩን ይዞ የምሽቱ አድናቂዎቹ ያሉበት ወንበርን በሙሉ ያካልላል። ዘፈኑን እንደምታውቁት መሀል ላይ የሽግግር መነባንብ ያለበት ሲሆን፣ ጎሳዬ ይሄን በንግግር ሲገልፀው ፀጥ ብለው የሚያደምጡት የናይት_ክለቡን ዕድምተኞች የዝምታ ገፅታ ለታዘበ ሊዝናኑ የወጡ ሳይሆን፣ የነብስ አባታቸውን የሚያደምጡ ምዕመናን ይመስላሉ። የሙዚቃ ጉልበት የዚህን ያህል መሆኑን የሚያሳይ ውብ ጉሮሮ ፈጣሪ ለጎሳዬ ችሮታል። ከዚህ በላይ ጎሳዬን ባደንቀው ከሀቅ አልሸሸውም። ዲጄ ኪንግስተን «ለጎሳዬ ያለኝን አድናቆት አውርቼ ካለመጥገቤ የተነሳ፣ አንዳንዴ የሌላ ሰው ታሪክ እስኪመስል ለራሱ ለጎሳዬ.....ስለጎሳዬ እነግረዋለው!» አይደል ያለው?አዎ በእውነት ለሙዚቃ የተሰጠ ልዩ ድምፃዊ ነው።🙌 📌ዛሬም እኔ ታዲያ....... ለመጨረሻ ግዜ በ2011 ካደረሰን 'ሲያምሽ ያመኛል' ከተሰኘው 4ተኛ አልበሙ ላይ እጅግ የምወደውን በራሱ ግጥም እና ዜማው የተደረሰውን 'ሃሳብ የለሽም'ን ለትውስታ ጋብዤያቹ እግረ መንገዴን ታላቁን ሙዚቀኛ ከብዙ በጥቂቱ አንስተን አመስግነነዋል🙏🥰 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 musictube 🇪🇹 #fyp #Ethiopianmusic #musictube369 #ጎሳዬ_ተስፋዬ #ሃሳብየለሽም

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 07 May 2026 19:51:05 GMT
70680
5955
30
487

Music

Download

Comments

yonithe1st
Yo_ሐንስ :
It's ጎሳዬ after ቴዲ ለኔ he is soo talented 🔥
2026-05-08 15:07:49
19
gezish_21
𝗚𝗘𝗭𝗜𝗦𝗛 ♐ መድፈኛው ⚪️🔴 :
My favorite music 🥺🥰
2026-05-08 10:01:50
14
kinghayatu1993
አቡ ኡነይስ :
ሀሳብ የለሺም ስለኔ🥺🥺🥺
2026-06-02 19:52:58
0
imdbus
Imd buseiry :
K 2000 wadi k woto album yane top 3 wost ehegnaw album andu nw
2026-05-08 07:03:36
4
tesfaethiopia
Tesfa :
underrated album...😭
2026-05-11 21:12:22
0
nevalove4
Nebyat333 :
why this video is 2 hour
2026-05-08 17:30:25
1
user86976120047464
(19 84) (2014) :
ወይኔ ይህን ዘፈን ስወደው
2026-05-12 10:10:46
1
ye_arsemalij1
sol :
Caption 🔥
2026-05-08 08:01:04
1
.......yasu
Møøñ🎀 :
uffff 🔥🔥🔥
2026-05-08 23:24:51
1
biruk1627_biruk
biruk1627 :
🥰🥰💖💖🥰💖🥰🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖🥰💖💖🥰💖💖💖💖💖🥰💖🥰💖🥰💖💖🥰💖💖💖🥰
2026-05-08 10:15:27
1
baruiking
Barui King :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-08 15:12:24
1
honey.swee0
ሀና የቲዬ እናት :
❤❤
2026-05-08 09:44:04
1
ms937312
ms olds :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-08 18:05:44
1
ermiyas_t
Ermiyas_t :
🥰🥰🥰
2026-05-08 17:42:14
1
userna3256
አቡሽ ፍቅረ🎧🇱🇷 :
🥰🥰🥰
2026-05-08 06:31:42
1
kesanet19
kesanet19 :
🥰🥰🥰
2026-05-08 07:00:21
1
yonaaa_94
Godblessme :
🥰🥰🥰
2026-05-08 05:31:56
1
user38930975
Mico corleone :
🥰🥰🥰
2026-05-07 21:09:27
1
wwwwsedaw
CR7🇵🇹🇵🇹🇵🇹 :
❤️❤️❤️
2026-05-07 20:38:55
1
melattesga
ሜላት ተሰጋ :
❤️❤️❤️❤️❤️
2026-05-08 03:31:46
1
myyyyy272727
someone🤷 :
🥰🥰🥰🥰
2026-05-07 21:13:41
1
ashebir.shifera
Ashebir Shifera :
🥰🥰🥰
2026-05-07 21:14:47
1
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About