@simakonemelake: የቱርክ መካከለኛ ቦታ ላይ የሚገኝ ከተማ ውብ ፈረሶች የሚኖሩበት ለማለት የወጣላት ስም ነው። በመጸ‍እሐፍ ቅዱስ ኬጢያውያን የሚባሉት ሕዝቦች ቦታ ናት። ኬጢያውያን የታወቁ ፈረስ ጋላቢዎች ነበሩ። በበዓለ ጰራቅሊጦስ በ ኢየሩሳሌም ተገኝተው ክርስትናን ከተቀበሉት መካከል የቀጰዶቅያ ሰዎች ይገኙበታል። ቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት የጻፈላቸው ምእመናን መካከልም የቀጰዶቅያ ምእመናን ይገኙበታል። ይሄ ማለት በ እስጢፋኖስ ሞት ምክንያት ተሰደው ከገቡባቸው አገሮች አንዷ ቀጰዶቅያ ነበረች ማለት ነው። የዋሻ ውስጥ ከተማ ይገኝበታል የጥንት ክርስቲያኖች የሠሩት ከተማ ነው። እጅግ አስደናቂ ነው። አስጎብኛችን እንደነገረን ከሠላሳ ሺህ በላይ ሕዝብ መያዝ የሚችሉ የፀሐይ ብርሃን የሚያገኙበት፣ ነፋስ የሚቀበሉበት ታስቦ የተሠራላቸው ክፍሎች ያሏቸው ናቸው። የጸሎትና የአምልኮ ስፍራዎችም አሏቸው። በመንገዳችን ያየናቸው ከወጥ ዐለት የተሠሩ ቤቶች በጣም አስገራሚ ነበሩ። ተራራውን ተጠግተው የተሠሩ ከተሞች ሁሉ ጥንታዊውን ቤት ከዘመናዊ ጋር አስተባብረው በመያዛቸው ለማየት አይጠገቡም። አየናቸው፣ አየናቸው፣ ተደመምንባቸው፣ ፎቶ ተነሣንባቸው። አሁን ኑሲስ NYSSA ተብላ በታሪክ ወደ ታወቀችው የቅዱስ ጎርጎርየ‍ኦስ መንበር ለማደር እየገባን ነው። ከ372-394 ቅዱሱ ሊቅ እንደ ምሰሶ ተተክሎ ዓለምን የሚመግብ ትምህርትን ያስተማረባት ከተማ ናት። ያች 372 ዓ.ም ዛሬ በሆነች ኖሮ ምን አለበት? ነገረ ሥጋዌን ጠይቀነው ቢመልስልን፣ መጻሕፍትን ሲተረጉም በጉባኤው ተገኝተን ብናደምጠው ብለን ተመኘን። ያን ጊዜ አርዮሳውያን ታጥቀው ቤተ ክርስቲያንን በሚዋጉበት ዘመን የሃይማኖትን ምሥጢር የሚገልጡ ሊቃውንትን ሲያስነሣ አንዱ ይህ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነበር። የኑሲስ መንበር የመጀመሪያው አባት እንደሆነ በታሪክ ይታወቃል። ኑሲስ ያለ ጎርጎርዮስ ትንሽ መንደር ናት። ዓለምን የሞላ ስም ያገኘችው ይህንን ሊቅ ተሸክማ ነው። ሐውልት ሳታቆምለት በመላው ዓለም ሐውልት ያቆመላት ሊቅ። በ እርግጥ እሷ ስሟንም ግብሯንም ለውጣ ሁሉንም ነገር ረስታለች። ኑ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዜና ሕይወቱ ለሙሴን The life of Moses ይንገረን፤ ስለተወደደችው እኅቱ ማክሪና ይተርክልን። ስለ ታላቁ ባስልዮስ ቅድስና ስለ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ይንገረን። ብሉያትን ሐዲሳትን ይተርጉምልን? ሚያዚያ -2018 ዒ.ም ቀጰዶቅያ / Cappadocia - ቱርክ ስምዓኮነ መልአከ / Simakone Melak

ስምዓኮነ መልአከ / Simakone Melake
ስምዓኮነ መልአከ / Simakone Melake
Open In TikTok:
Region: AE
Friday 08 May 2026 16:03:53 GMT
154628
26130
392
1498

Music

Download

Comments

genet.birhanu00
Genet Birhanu :
በረከታቸው በረከታችሁ ይደርብን አባቶቻችን 🙏🙏🙏
2026-05-09 01:36:27
69
user3877167603824
ፍቅርን ከክርስቶስ ትትናን ከማርያም 💒🥀🌹 :
አባቶቻችን እረጅም እድሜ ከጤናጋ ይስጥልን 🤲🥰❤
2026-05-09 00:19:21
27
meski272829
የመድኃኔዓለም ልጅ (ምህረተ ስላሴ) :
♥️♥️♥️በረከታችሁ አይለየን አባቶቻችን🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-10 14:08:02
8
wedosen.minda
ክብር🌹 ለሴት🌹 ልጅ 🥰 እናቴ ኑረልኝ ዘ/ም :
በረከታችሁ ይደርብን 🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-11 06:50:51
7
user6562094979969
ፍቅር ከራያ ልጅ♥️🦋 :
አባቶቸ በረከታችሁ ትድረሰኝ🥰🥰🥺🥺🥺
2026-05-12 15:22:28
0
tizita.mare8
ልባምን ሴት ማን ሌገኛት ይችላል❤️👌🌹😍 :
እረጅም እድሜን ከሙሉ ጤናጋር ይጠብቅልን ቅዱስ እግዚአብሔር 🙏😍😍😍አባቱቻችን🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🙏🙏🙏
2026-05-09 06:25:19
7
seregute22
tigist tawoderos amare :
bereketachew yedereben 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🌹🌹🌹🌹❤️🥰
2026-06-06 21:48:14
1
tiruesate
Tiruset የተክልዬ ወዳጅ🙏 :
የኔ እንቁ አባቶች በረከታችሁ ይድረሰኝ!!ዕድሜና ጤና ይስጣችሁ🥰🥰🥰
2026-05-09 08:14:14
7
tigue86
ወይኩን ፈቃድከ :
ሰላማችሁ ይብዛልኝ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-05-08 21:55:50
2
k1692102
የገብረኤል ልጅ :
አባቶቻችን እረጅም እድሜና ጤና ይስጣችሁ በረከታችሁ ይደርብኝ 🤲🤲🤲🤲🙏🙏🙏🙏🥰🥰🥰
2026-05-11 15:05:40
2
alam.burgale
Alem :
በረከታችሁ ይደርብን አባቶቻችን እድሜይስጥልን ከሙሉጤናጋ🙏🙏🙏🥰🥰🥰🙏🙏🙏🙏🙏
2026-05-10 15:36:12
1
kirkos15161923
🔯HzkiaS🔯🌟1623🌟19🌟🌹 :
🥰
2026-05-09 09:37:33
2
user8328519674561
Abayinesh :
በረከታችሁ አይለየን አባቶቻችን🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-09 11:08:00
5
meron.ke.shewa
Meri Getacher 19 አባቴ :
🥰🥰🥰🥰በረከታቸው በረከታችሁ ይደርብን አባቶቻችን 🙏🙏🙏🥰🥰🥰
2026-05-11 19:10:58
1
userkswly1w0hh
ራሔል ሽፎንና የባህል አልባሳት :
አባቶቻችን እረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን 🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-12 19:12:28
1
beza8886126106177
beza :
my best🥰🥰❤️❤️❤️
2026-05-10 12:22:13
1
burte.burte5
Brtukan⛪️❤G🦅ዬ♥️🇪🇹 :
አባቶቻችን በረከታችሁ ይደርብን🙏🙏🙏🙏🙏🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-11 13:49:07
1
kidist9900
kidist ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን :
አባቶቸ በረከታችሁ ትድረሰን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-05-09 15:41:04
1
user8165388762771
✨ኢቫና💜🦋✝️ :
አበዊነ🙏🥰
2026-05-09 08:22:35
1
liqwufost
እኔው ራሴ :
አባቶቼ በረከታችሁ ይደርብኝ 🙏🙏🙏
2026-05-09 09:26:35
1
tiru12316
21 Tiru 21💝☦️💝 :
በረከታችሁ ይደርብን ስወዳችሁ🥰
2026-06-19 20:18:26
0
ashu2665
ሠናይ :
የተክልዬ ወዳጅ🙏:የኔ እንቁ አባቶች በረከታችሁ ይድረሰኝ!!ዕድሜና ጤና ይስጣችሁ🥰🥰🥰
2026-06-29 09:00:10
0
user178165947762
ቅዱስ ነኝ ከሽዋ :
በረከታችሁ ይደርብን አባቶቸ🙏🙏🙏
2026-06-23 12:26:04
0
elsaman328
elsa :
ሰላማቹ ይብዛ ❤❤❤❤
2026-05-11 05:54:43
0
To see more videos from user @simakonemelake, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About