@arsu..21: የሄድሽ ቀንኮ አደለም!!! ልትሄጂ እንደሆን ያሰብኩ ቀን ራሱ እጨነቅ ነበር።ስትሄጂ ምን እንደምሆን ሳስብ እፈራ ነበር።ተደግፌሽ እንደቆምኩ ያላንቺ ማንም እንደሌለኝ ስለማስብ ይሆን???እኔንጃ!! ብዙ ቀን ግን ስሜቴ ትሄዳለች እያለኝ አልቅሻለሁ ብዙ ቀን ልቆጣሽ ብዬ እንዳትተዪኝ ፈርቼ ትቼዋለሁ ኩርፊያሽ አለም ያኮረፈኝን ያህል እንዲሰማኝ ስለሚያደርግ ኩርፊያሽን እፈራዋለሁ ካንቺ ጋ የተገናኘሁበትን ቀን እስክረግመው ተጨንቄያለሁ የሌላ ሆነሽ አስቤ ብዙ ቀን ብቻዬን አብጃለሁ ምን እያሰበች ይሆን??ደብሬያት ይሆን??እንደድሮ ትወደኝ ይሆን??ልቧ ውስጥ ሌላ ሰው አለ ይሆን እያልኩ ተብሰልስያለሁ.. ፈርቻለሁ ምድር ላይ ሰው እንዳልተፈጠረ ያህል ሁሉን ረስቼ አንቺን ብቻ አስቤሻሁ አንቺን ብቻ አፍቅሬሻለሁ ...ካንቺ ከመለየት ሞቴን መርጫለሁ ግን አንድ ቀን ደወልሽልኝና ፈጥኜ አነሳሁት..ደና እንደሆንኩኝ እንኳ አልጠየቅሺኝም "መለያየት አለብን" አልሺኝ ያን ቀን ፍሪጅ እንደከረመ ውሀ በረዶ ሆንኩኝ እንደሬሳ ቀዘቀዝኩኝ ቀጥሎ የሚፈጠረውን ሳስብ መብራት እንደጨበጠ ደርቄ ቀረሁኝ ለምን?እንዴት?አላልኩሽም።ዝም እንዳልኩሽ ስልኩ ተዘጋ።በቀናት ውስጥ አዲሱ ፍቅረኛሽን እየሳምሽው እኔን እንደተውሺኝ ለማሳበቅ ለህዝቡ አወጅሽ አሁን ሲያይ ምን ይሰማዋል?? አላልሽም!!!ይከፋው ይሆን??አላልሽም!!ለሚጠይቁት ሰወች ያስጨንቁት ይሆን??አላልሽም!!ብዙ በሳሳውልሽ ልክ ጨከንሽብን!!ባከበርኩሽ ልክ አዋረድሺኝ!!የት ሄደች እያሉ የሚጠይቁኝን ለመሸሽ ቤቴን ትቼ ወጣሁ።ሰፈሩ ደበረኝ ።አንድ ቀን ሰበብ ፈልጌ መንገድ ዳር አደርኩኝ ።እኔ ብቻ ሳወራ ደስ አለኝ ..ነፃነቴን ያገኘሁ መሰለኝ... በሁለተኛው ቀን እሳት አነደድኩኝ ሰው ሁሉ እየመጣ ሲያየኝ አብዶ ነው የሚል ስያሜ ተሰጠኝ አልደበረኝም ማህበረሰብ ተስማምቶ ስም ሲለጥፍ በኔ አልተጀመረ እኔም አመንኳቸው መሰል ጥልቅ ፍርሀት እብደት ይወልድ የለ የፈራሁት ሲደርስ ቬሎ ለብሰሽ ስታገቢ እኔ ድሪቶዬን ለብሼ አበድኩልሽ ታድለሽ አንድ እብድ አለሽ

𝑠𝑎𝑟𝑖 የጃንደረባው ትውልድ 🇺🇸
𝑠𝑎𝑟𝑖 የጃንደረባው ትውልድ 🇺🇸
Open In TikTok:
Region: SA
Tuesday 12 May 2026 00:21:34 GMT
91827
4390
3
1891

Music

Download

Comments

arsu..21
𝑠𝑎𝑟𝑖 የጃንደረባው ትውልድ 🇺🇸 :
ታድለሽ አንድ እብድ አለሽ🥰🥺
2026-05-14 12:25:37
19
demess3
Ashu 𝑚𝑦𝑘𝑜 17 19 16 :
❤️❤️❤️
2026-05-13 09:01:55
12
antsokiya3
ሳሚ :
❤️❤️❤️
2026-05-14 02:28:46
4
To see more videos from user @arsu..21, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About