@mezgebu077: አራት አይናው ሊቁ ጓደኛየ ክቡር ሊቅ፣ የድሮ ዋካ የዛሬው ጽጌ አስተርአየ፣ የአቋቋም መምህር፣ የቅኔ ፈጣሪና መምህር፣ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት አስተማሪ፣ የሊቃውንትና የመነኮሳት መምህር፣ አራታይናው መምህር ጽጌ አስተርአየ፤ ሰላምታዬ ባሉበት ይድረስዎት። ዛሬ የድሮ ትውስታዎች በልቤ ሲመላለሱ እርስዎን ማስታወስ ግድ ሆነብኝ። ድሮ በመንደፈራ ኪዳነ ምሕረት ከየታ መርሐ ጽድቅ ጋር በአቋቋም ቤት ሁለት ዓመት፣ ከየኔታ ሞገስ ጋር ደግሞ በቅኔ ቤት ሁለት ዓመት፣ በአቧሮ ማርያም በአጠቃላይ አራት ዓመታት ያሳለፍናቸው የልጅነት ዘመኖች ምንኛ ውብ ነበሩ! ያ ዘመን እስከ ዛሬ ድረስ በልቤ ጽላት ላይ እንደተጻፈ ይኖራል። በተለይም የእርስዎ ልዩ የአእምሮ ጥልቀት ዛሬም ይታየኛል። አንድ ጊዜ ቀልም ቢነገርዎት ደግመው የማይጠይቁት ያ የአእምሮ ብርታትና የማስታወስ ጸጋ እስካሁን ድረስ በአድናቆት ያስታውሰኛል። አሁንስ እንዴት ነዎት? ጤናዎት እንዴት ነው? በጎንደር አበራ ጊዮርጊስ በመጻሕፍት መምህርነት እያገለገሉ እንደሆነ መረጃዎች ይደርሱኛል፤ ይህም ልቤን ደስ ያሰኛል። በድጋሚ ሰላምታዬ ባሉበት ይድረስዎት። እግዚአብሔር በጤና፣ በጸጋና በረጅም ዕድሜ ይጠብቅዎት።
መኑ የሐድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ ከክርስቶስ ፍቅር
Region: ET
Saturday 16 May 2026 13:47:04 GMT
Music
Download
Comments
💠 አነ ዘክርስቶስ 💠💠💠 :
2026-07-19 13:28:31
0
fsha939 :
ወጣቱ አራት ዐይና የኔታ ጽጌ🥰
2026-05-22 17:13:42
0
ሲራክ :
የኛ ሊቅ
2026-05-17 06:45:50
1
Memhr Mahitot :
እኔም የተማሪ ቤት ጓድኛዬ ነበሩ
2026-05-19 13:16:57
0
አጶሮግዮን :
እናደርሳለን የኔታ
2026-05-17 06:08:55
1
Bliken :
እሽ የኔታ
2026-05-17 19:16:05
1
Rozaa :
🙏🙏🙏🙏🙏
2026-05-17 12:22:02
1
Heri xaeda 👑💞💞💞 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-17 10:58:55
1
ሲራክ :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-17 06:43:31
1
fasik@lp :
🥰🥰🥰
2026-05-17 06:52:17
1
hawaz :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-17 05:13:48
1
hana :
🥰🥰🥰
2026-05-16 14:33:15
1
ጳዝዮን ዝክረ ቅዱሳን🦅⚡️ :
🥰
2026-05-16 15:50:18
1
Be your self🦜 :
✔️🥀🥀🥀
2026-05-17 17:31:20
1
እምየ ኢትዮጵያ :
❤️🥰❤️🥰❤️🥰❤️🥰❤️🥰❤️🥰
2026-06-20 05:35:03
0
To see more videos from user @mezgebu077, please go to the Tikwm
homepage.