@sot_media33: በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው የሱዳን 'ብሉ ናይል' ግዛት ከሰሞኑ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ይገኛል። በዚሁ ግዛት በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መሸጋገሪያ የሆነውን አንድ ከተማ ትናንት አርብ አመሻሽ ላይ መቆጣጠሩን የሱዳን መደበኛ ጦር አስታውቋል። የሱዳን ጦር ትናንት የተቆጣጠረው ይህ አካባቢ፣ ከኢትዮጵያ ጋር በቀጥታ ወደምትዋሰነውና ቁልፍ ወደሆነችው የኩርሙክ ድንበር ከተማ ለመገስገስ እንደ መሸጋገሪያ የሚያገለግል ነው። ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላት የድንበር ከተማዋ ኩርሙክ፣ ባለፈው መጋቢት ወር በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF) እና በሱዳን ሕዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) ቁጥጥር ስር መዋሏ ይታወሳል። ይህ የድንበር መስመር፣ "የሱዳን ጦር ከኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ድጋፍ ያገኝበታል" በማለት ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ክስ የሚያቀርብበት ቀጣና ነው። በአሁኑ ወቅት የሱዳን ጦር አካባቢውን መልሶ ለመቆጣጠር ጠንከር ያለ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን፤ በአንጻሩ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ይዞታውን ላለማስለቀቅ ጠንካራ የመከላከል እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። የድንበር ቀጣናውን ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ እና አካባቢውን ጠቅልሎ ለመቆጣጠር ወታደራዊ እርምጃውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የሱዳን ጦር አስታወቀ።

🎦SOT media
🎦SOT media
Open In TikTok:
Region: CH
Saturday 16 May 2026 17:01:45 GMT
301
4
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @sot_media33, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About