@yilugg: እኔም ቅኔ ልዝረፍ (ካልታተሙ የባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ ግጥሞች ውስጥ አንዱ ነው) እኔም ቅኔ ልዝረፍ - እስቲ ይመርብኝ ያፈር ግብር አሥራት - የሥጋ’ዳ አለብኝ፤ ጠኔ ሲያጥመነምን - መገን ይኼ ቅኔ - በምን ይገለጣል ስትሹ ‘እሹ!’ እያለ- የወዳጄ አበጋር -                             ቁርጮ ካንቀራጨ- መች ሃጃ ያወጣል? በጉባዔ ቃና - ዘ አምላክዬ ቤት-                       መድረስ አቅም ቢያንሰው ልቤ ዓይኔን ካልከዳው -     በዕምነት ከከነዳው ይለያል ሰዋሰው! ሰምና ወርቅ ፍቺ… ትርጉም ቢያሟዝዘው       የሰለጠው ላጤ - ጉድ ቢያገረዝዘው ለአንክ-እንክ ዕንቆቅልሽ - ማን ይሰጣል አገር? “ምን ዐውቅልህ?” ቢሉት                     ርዶ ተብረክርኮ- ጉበን ላይሻገር አዎን! እኔም ልዝረፍ ቅኔ             ከጉልበቴ መቅኔ     ይከፈት ፋይሉ - ቃል ይጥራ ዋስ ጥብቅ አንጀት እየላገ - ሆድ ሆድን ሲበላው -                                     ታጥፎ እንዳያሳብቅ ትዕቢቴ - እንደ ጸቢቴ… ተግባሬን ሲቀድመው ያ! ክፍ መሻቴ… የሥጋ ልክፍቴ…       ቢያሳርፈኝ ብሎ… ውድቀቴን ሲያደመው ዳግም ላንሠራራ - ልቆም ስንጠራራ -                                             ወገቤን ብቀጭም ታሞ መዳን ሳለ - ስቶ መታረሙ -               ተላቆ መጠገን ወትሮም አያስቆጭም። ታዲያ ይኸን ቅኔ - በነፍሴ ብራና - ምናለ ባሰፍረው                     ዕድሜ ቁና ሰፍቶ በወግ እስቲሰፍረው? መልከኛ ተመርቶት - ድልብ እያፈሰበት ድንግሉን ረባዳ                    በነጎዴ ቦዳ - በስም ቦላ ዝዬ ተለጉሜ ላዝምም - ሙሻ-ዘር አዝዬ? ሊቀ ካህናቱ - በከንቱ፣ ውዕቱ፣ መርተው ሲነርቱ                           በብር መቋሚያ - በወርቅ ፀናፅል ደበሎ ለብሼ - ሚስጥረ ኅቡዓን - ድጓዬን ብቀጽል “በህግ አምላክ!” ብሎ ማን ሊያቆመኝ ኑሯል? ለራሱ ሊወናይ - ዘርፎ ቢቀኝ እንጂ -          በነብሱ “ተክህኖ” ማን ማንን አስምሯል! ዓለም ሊያወዳድር - ወረትን ቢያበድር ፍንጁስ መች ቀን ሰጠ - በ‘እሪ’ እያጓሰጠ                      ሌት ሲያሳስብ ቢያድር? እጅ ታቹን ውሎ - ዓይንን-ዐይን በልቶት በቸነፈር ነፍሮ           እንደ ክፉ ገላ - ስም - ሙስናው ናሽሮ ምፅዋት ዋቶ - ቃቶ - ምጥ - ጠዋት ቢያበስለው በደም ተገሽሮ በእርም እንጀራ ቢገድፍ - ቅበላ እንዴት ሽሮ? ቸርስ ምን ቸር ነበር - አንዱን ዕጣው ገፍቶት… ቁልቁል ባያዳፋው ለማን ሰጥቶት ሊጠድቅ - አደግድጎ ሚሰግድ      እጅ ስሞ ሚቀበል - ለማኙን ቢያጠፋው የኔ ቢጤ ነገር - ዐይን ያለው ክብር አንጂ -                            ሌላ ማን ሊያውቅለት ላማ - ሰበቅታኒ - የቃል-አብን ስቅላት? © ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ)

𝙮𝙞𝑙𝑎𝑘 G-𝑔𝑖𝑜𝑟𝑔𝑖𝑠
𝙮𝙞𝑙𝑎𝑘 G-𝑔𝑖𝑜𝑟𝑔𝑖𝑠
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 17 May 2026 16:21:32 GMT
9951
652
18
139

Music

Download

Comments

ras.abel8
Ras abel :
2026-05-18 11:08:50
1
yared.abatye
ሔመን የባህል አልባሳት .. :
ክብረት ይስጥልን ወንድሜ ...እሱንም ነፍሱን ይማርልን 🙏🙏🙏
2026-06-15 16:06:49
1
gezi947
ከ_ገዛኸኝ 🦅 :
😍😍😍❤❤
2026-05-17 17:56:14
1
teddo006
ቴዳዬ + :
አንዳንድ ተሰጥኦ ከላይ ሲሰጥ ይገርማል የአንተ ከመሰጠት ከመዳበርም አለፎ ተዋህዶሀል ግጥምን አንብባት🙏💚💛❤
2026-05-18 09:37:28
2
abebe.chala.chew
Abebe Chala chew :
👍👍👍
2026-05-18 12:19:51
0
slameyab5
ሰሊና (የአባሰል ቅኝት) :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-17 19:51:05
1
mulukenahmed163
Muluken muhammed :
🥰🥰🥰🥰👌🙏
2026-05-18 06:02:21
1
annex____
Annex____ :
❤️❤️❤️
2026-06-12 20:56:30
1
abebe.chala.chew
Abebe Chala chew :
🤩🤩🤩
2026-05-18 12:19:51
1
teg444
teg :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-28 16:29:27
1
shanbelkasaye1
ቤተ አማሀራ :
😳😳🥰🥰💪👍
2026-07-22 11:17:54
1
To see more videos from user @yilugg, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About