@israel.du: በጸፍጸፈ ሰማይ ለሄኖስ ተጽፈው የተገለጹ ናቸው በሇላም መዝሙረኛው ዳዊት ጸልዮባቸዋል ነቢዩ ኤርምያስም እንደ ዳዊት አመስግኖባቸዋል ። 22ቱ የአሌፋት ፊደላት የእግዚአብሔር ህቡዕ ስሞች ሲሆኑ ከግእዙ ፊደላት ጋር የተጣመሩ ናቸው 1. አሌፍ ፡ አሌፍ ብሂል አብ ፈጣሬ ኩሉ ዓለም ዓለምን ከነጓዟ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። 2. ቤት፡ ቤት ብሂል ባዕል እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሁሉን መስጠት የሚችል ቸር ለጋስ ባለጸጋ ነው ማለት ነው። 3. ጋሜል ፡ ጋሜል ብሂል ግሩም እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሊመረመር የማይችል ግሩም ድንቅ ነው ማለት ነው። 4. ዳሌጥ ዳሌጥ ብሂል ድልው እግዚአብሔር እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሮ ያዘጋጀ ነው ማለት ነው። 5. ሄ፡ ሄ ብሂል ህልው እግዚአብሔር እግዚአብሔር በአንድነቱ በሦስትነቱ ለዘለዓለም ይኖራል ማለት ነው። 6. ዋው ፡ ዋው ብሂል ዋህድ እግዚአብሔር እግዚአብሔር በመንግሥት በሥልጣን በአገዛዝ በባህርይ አንድ አምላክ የሆነ ማለት ነው። 7. ዛይ ፡ ዛይ ብሂል ዝኩር እግዚአብሔር እግዚአብሔር በሥራው ሁሉ እየታሰበ ሲመሰገን የሚኖር ፈጣሪ ነው ማለት ነው። 8. ሔት ብሒል ሕያው ሔት እግዚአብሔር በመንግሥቱ ሽረት በባሕርዩ ኅልፈት የሌለበት ለዘለዓለም ሕያው የሆነ ነው ማለት ነው። 9. ጤት ፡ ጤት ብሂል ጠቢብ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ጥበብን የሚገልጽ ከጥበበኞች ይልቅ ጥበበኛ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 10. ዮድ፡ ዮድ ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለ እሱ ኃያልና ጽኑዕ የሆነ ነው ማለት ነው። 11. ካፍ ፡ ከሀሊ እግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የሌለ ሁሉን ማድረግ የሚቻለው አምላክ ነው ማለት ነው። 12. ላሜድ ፡ ላሜድ ብሂል ልዑል እግዚአብሔር እግዚአብሔር ልዑለ ባሕርይ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 13. ሜም ፡ ሜም ብሂል ምዑዝ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ንጹሕ ባሕርይ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 14. ኖን፡ ኖን ብሂል ንጉሥ እግዚአብሔር እግዚአብሔር የነገሥታት ንጉሥ የገዥዎች ገዥ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 15. ሳምኬት ፡ ሳምኬት ብሂል ሰፋኒ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ አምላክ ነው ማለት ነው። 16. ዔ፡ ዔ ብሂል ዓቢይ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ታላቅና ገናና የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 17. ፌ፡ ፌ ብሂል ፍቁር እግዚአብሔር እግዚአብሔር ተወዳጅ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 18. ጻዴ፡ ጻዴ ብሂል ጻድቅ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሐሰት የሌለበት እውነተኛ አምላክ ነው ማለት ነው። 19. ቆፍ፡ ቆፍ ብሂል ቅሩብ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ለልበ ቅኖችና ለየዋሃኖች ቅርብ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 20. ሬስ፡ ሬስ ብሂል ርኡስ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ክብሩ ከእርሱ ለእርሱ የተገኘ የሁሉ ጌታ በሁሉ የሰለጠነ ነው ማለት ነው። 21. ሳን፡ ሳን ብሂል ስቡሕ እግዚአብሔር እግዚአብሔር በሥራው ሁሉ የተመሠገነ ነው ማለት ነው። 22. ታው፡ ታው ብሂል ትጉህ እግዚአብሔር እግዚአብሔር እንቅልፍ የሌለበት ትጉህ፤ ድካም የማይሰማው ጽኑዕ የሆነ ፈጣሪ ነው ማለት ነው። 202 የግእዝ ፊደላት ትርጓሜ ከሚለው መጽሐፌ ላይ የተወሰደ 2006 የታተመ መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
እስራኤል
Region: ET
Sunday 17 May 2026 16:29:58 GMT
Music
Download
Comments
Marta :
ቃለ ሕወት ያሰማልን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-05-21 19:14:59
4
ቀሲስ_በላይነህ_ባንዳው_28 :
🥰🥰🥰
2026-05-18 05:41:29
2
waquma :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰❤️❤️❤️
2026-05-19 10:16:28
1
𝓼𝓮𝔀 𝓷𝓮𝓰𝓷 :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🥰🥰🥰🥰
2026-05-17 19:24:48
1
ተስፍ :
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-05-17 16:57:29
1
zerfu mesele :
🥰🥰🥰
2026-06-16 13:18:56
0
Gammee💞 :
🥰🥰🥰
2026-05-24 08:10:07
0
መዝሙር :
🥰🥰🥰
2026-06-21 17:50:03
0
To see more videos from user @israel.du, please go to the Tikwm
homepage.