@smiruhe2k: #creatorsearchinsights #foryou #fyp #❤️ #loveyou

𝒮𝓅𝓇𝒾𝓃ℊ 𝒢𝒾𝓇𝓁🦢
𝒮𝓅𝓇𝒾𝓃ℊ 𝒢𝒾𝓇𝓁🦢
Open In TikTok:
Region: EG
Wednesday 20 May 2026 15:27:34 GMT
26739
2867
2
592

Music

Download

Comments

ibr4d
ibr4d :
I’m gonna keep wishing for that
2026-05-21 21:13:27
4
dstvd9725
dstvd777🌬️💭👑 :
sdds meu amor🤍💙💜🪄
2026-06-24 20:35:39
1
To see more videos from user @smiruhe2k, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

#post 918 | #ስጠኝ_ስትሰጥ_አይቼሃለሁ፦   የእናቴ የሁልጊዜ ጸሎት ነች። አንድ ቀን እንዲህ ብዬ ጠየኳት? “የሽዬ ይችን ጸሎት ትወጃታለሽ ለምንድን ነው የምትደጋግሚያት?” አልኳት፤ “አይ ልጄ ይስጠኝ ሲሰጥ.... አይቸዋለሁ” አለችኝ “አምላክን ነው ?” አልኳት፣ “እና አባትህን ነው ?” አለችኝ! በመልሷ ስቄ ዝም አልኩ፤ ከትንሽ ቆይታ በኋላ እንዲህ ተረከችልኝ..... “ድሮ ነው ያኔ በደጉ ዘመን አንድ ድሃ ገበሬ ነበር። ጫካ ገብቶ እንጨት ሰብሮ ተሸክሞ ከተማ አምጥቶ ሸጦ ቤተሰቡን የሚያስተዳድር፤ አንዴ ታዲያ እንደተለመደው እንጨቱን ሰብሮ ተሸክሞ ወደ ቤቱ ሊሄድ ሲል ይደክመውና አንዱ ዛፍ ስር ደገፍ ይላል። ከቆይታዎች በኋላ ሙዳ ስጋ የያዘ ትልቅዬ አሞራ ሰውዬው ከተቀመጠበት ዛፍ ፊት ለፊት ካለ ዛፍ ያርፍና በማንቁርቱ ሊበላ ሲጣደፍ ድንገት ስጋው ይወድቃል፤ ይሄኔ እጥፍጥፍ ብሎ ተኝቶ የነበረ አንድ ከሲታ ውሻ አይኖቹን ባለማመን ሙዳ ስጋው ላይ ዘሎ ይከመርና እየተጣደፈ መብላት ሲጀምር ያ ምስኪን ሰው ይመለከታል። ወደ ሰማይ አንጋጦም እንዲህ ይላል። “አይ እግዚአብሔሄር አንተኮ ታላቅ ነህ! በርሃብ ሊሞት የነበረውን ውሻ እንዲህ በጥበብ ትመግበው? ....ስራህ ግሩም ነው። እግዚአብሄር ሆይ እንግዲህ ስትሰጥ አይቼሃለሁና ለኔም ስጠኝ፣....ስጠኝ ስትሰጥ አይቼሃለሁ” ብሎ ተናግሮ በብዙ ልፋት ያጠራቀመውን እንጨቱን ትቶ ባዶ እጁን ቤቱ ይደርሳል፤ ባለቤቱም ያየችውን ባለማመን “አንተ ሰውየ ቤት ውስጥ የሚበላ ነገር እንደሌለ እያወክ እንዴት የሚሸጥ እንጨት ሳትይዝ ትመጣለህ?” አለችው።  እርሱም “አይዞሽ አትፍሪ ይስጠኝ ሲሰጥ አይቸዋለሁ” ብሎ ጠፍር አልጋው ላይ ወጥቶ ተኛ:: ሚስት በቁጣ እየለፈለፈች ቀኑ መሸ:: ሊነጋጋ ሲል በአቆማዳ የሞላ ጠገራ ብር ሰርቆ ሲሮጥ የነበረ ሌባ አባራሪዎቹ እየደረሱበት እንደሆነ ሲያውቅ ከሰውዬው ጎጆ በራፍ ላይ የሰረቀውን አቆማዳ አስደግፎት ይሮጣል። በማለዳ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ የምትወደው የምስኪኑ ገበሬ ሚስት የጎጆዋን በራፍ ስትከፍት በአቁማዳ የሞላው ጠገራ ብር ወደቤቷ ግልብጥ ብሎ ይደፋል።  ይሄኔ ሃይለኛ እንቅልፍ ላይ የነበረውን ባለቤቷን በል ተነስ ፈጣሪ ጸሎትህን ሰምቶሃል ተነስ ብላ ቀሰቀሰችው፤ ምስኪኑም ያየውን ባለማመን “እግዚአብሄር ሆይ አመሰግንሃለሁ .... አሁንም ስጠኝ ሰትሰጥ አይቸሃለሁ” አለ ይባላል።  ውዶቼ በህይወታችን ውስጥ ብዙ ጊዜ ፍላጎታችንን የሚረዱ፣ ነገር ግን የመርዳት አቅም የሌላቸው ሰዎች ያጋጥሙናል። እግዚአብሔር ግን ፍላጎታችንንና የልባችንን ስብራት የሚያውቅ ብቻ ሳይሆን፣ የለመኑትን ለመስጠት እጁ ሁልጊዜ የተዘረጋ ሩህሩህ አባት ነው። ​እግዚአብሔር አምላክ ምድራዊ ወላጅ ልጅ እንጀራ ሲለምነው ድንጋይ እንደማይሰጠው ሁሉ፣ እርሱም በታመነ ልብ የሚለምኑትን ልጆቹን ባዶ እጃቸውን አይመልስም። የሰው ልጅ ሰጥቶ ሲሰለቸው፣ እግዚአብሔር ግን በለመኑት ቁጥር የሚደሰት፣ ምህረቱና ደግነቱ የማያልቅ ባለጠጋ ነው። ​ውዶቼ ጸሎታችን ወዲያው የተመለሰ ባይመስል እንኳ፣ እርሱ የሚሰጠው በራሱ ጊዜና ለእኛ በሚበጀው መንገድ ነው፤ ምክንያቱም ከእኛ በላይ ስለእኛ የሚያስብ ደግ አባት ነውና።  የከበዳችሁን ነገር ሁሉ በእምነት ወደ እርሱ አምጡት። የማይሰማ ይመስል ይሆናል፤ ነገር ግን ሩህሩሁ አባታችን እያደመጣችሁ ነው:: በሩን አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ ለምኑ ይሰጣችሁማል! አይደል የሚለው!!! ውዶቼ እኛ የለመነውን የጠየቅነውን እንረሳ ይሆናል እንጂ እግዚአብሔር አባታችን የጠየቁትን የማይረሳ ድንቅ አባት የዘላለም መመኪያ ነው ስሙ ይክበር ይመስገንም🙏🙏 {[ስጠኝ ስትሰጥ አይቼሃለሁና!]} #አሼ_ነኝ✌ #ቤቱን_like_share_follow_copylink_repost_ማድረጋችሁን_አትርሱ🙏

About