@yilugg: በስንቱ እንበጥበጥ አለች አሉ በሶ በስንቱ እንበጥበጥ ጎበዝ በማንም የመንደር ጉርባ ተረግሞ ሽንቱ እንዳይረባ ማፈሩን እንደኩራት ቆጥሮ በጅብ ቆዳ በተለጎመ አታሞ አስረሽ ምችው እየደረባ ጎናችን ምኝታ እንጂ እንቅልፍ ጠግበ'ንኳ እንዳይደነድን ይደልቅብናል በድን አፈ ድስት አፉን ሳይከድን እማንታዘብ መስሎታል እንዴ ነውሩን ብንጠየፍ እንጂ እጅ አለን የሚያደባይ የሚያስበረግግ እንደፈንጂ ምነው አደብ ቢገዙ ኪሳቸው የደለበ እነሱ ያገር እጅ እየቆረጡ በተራቸው ለላኳቸው እጅ እሚነሱ እንዲህ ብሎ ጋዜጣ እንዲህ ብሎ ኪነ ጥበብ ለመጋሸብ ነው ወይስ ለማበብ በደዌ ገንዘብ መፈንጠዝ በላይ እንደገዳይ ዓይናችን እያዬ አፈ ቀላጤ እየቀጠሩ በድለላ በሽለላ መጠዝጠዝ ለዚያውም በመነዝነዝ አገር'ኮ የጋራ ነው በአጽምና በደም እኩል ወደን እኩል ፈቅደን በፍቅር የማገርነው ታዲያ ምን የሚሉት ብልጠት ነው ወይስ የምንግዴ አጉል ድፍረት ስቀን'ኳ ባንኖርበት ግብራችን እንዳይንቀሳቀስ እንዲህ የምትነሱን እረፍት በሴራ ትብታብ ጠፍሮ መላወሻ ማሳጣት ማን ስልጣን ሰጣችሁ ያለፍትህ ሰውን መቅጣት ? ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው ሲያልቅ የናንተ ነው ብሎ መልሶ በኛ ላይ ስላቅ....! በጋጡበት እየገለፈጡ ፊጡ ምን ይሉኝ እናንተ ሰፈር የለም ወይስ ሳታስፈቱ ቀበራችሁት እንዲህ ነፍሳችሁ እስቲወጣ ከባቢሎን ዘንዶ ጋር እጅና ጓንት ሁናችሁ ያበራችሁት የበላችሁበትን ወጪት ባደባባይ የሰበራችሁት ውርድ ለራሴ ሁሉም ቆርሶ በጎረሰው ሁሉም አንድም ፈትሎ አንድም ገዝቶ በለበሰው ነውና የሚያዘው ሰው ፍሩልኝ ይኸን ማለትለት የሰው ሥጋ አጋድሞ መበለት ፍሩልኝ ይህን ስብጥር የናት ወጉ እንዳይቀርበት በፈንታው ባልሰፋው ሰፌድ በየካፌው ወሬ እሚያበጥር ፍሩልኝ ይኸን አለሁ ባይ ባንድ ጀምበር የጀምበር ያህል አባይ ከዚያ ከዚህ አሳቅሎ የማታ ማታ ጠቅሎ ካገር ዕድር ስሪት ነቅሎ በፈረንጅ ቅራቅንቦ አጅሎ አዬ ልብ አያ አዬ ሞኞ አዬ ጅሎ በኮኮስና በጁባ በመለከትና በጥሩምባ እስከሚዘለቅ ዕድሜ አይነሳንም ያሳየናል እነሱ ይቀድማሉ ቀድመው ሱሪ ለማውለቅ እበላ ባይ ምን አሞት አለው ዓይኑ ከሞሰብ እጁ ከመሰብሰብ ምላሱ ከማለሳለስ ሆዱ እንደድስተ ፈጅ ያደረ ወጥ ከመከለስ በዋድያት መሸታ ከመቸለስ ያለፈ ምን ቁምነገርታየበት ንስሐ አይገባው ቶበት ለመሆኑ ፈጣሪ አለው ? አለኝ የሚለው ዋስ ጥብቅ እንደሱ የማያሳብቅ ቃሉን አይደለም ውሉን የማይስት እንደሱ የማይሰስት ከዚህ የከፋ ቅስፈት የለም በቁም ሰብዕናን መገፈፍ ካፈርኩ አይመልሰኝ ብሎ የራስን መርዶ መለፈፍ አስተምሩን ብለን ድርጎ እየከፈልን ብናሸረግድ ደሞ እመኑ ብሎ በግድ አጨብጭበን ሹመን ብናቀማጥላቸው የነሱን ነፍስ ዕድሜ ከራሳችን አንስተን እንዴት እንቀጥልላቸው "ማንም የወሰደውን ሳይመልስ የሰጠውን ሳይቀበል ከዚች ዓለም ፍልክ የለም" ነበር ያለው ያ ጅብራን ምነበር ይኸ ሥነ ቃል ኪዳን ሆኖ ሁላችንንም ቢመራን እንዴት ሰው በወንድሙ እንዴት ሰው በወገኑ እንዲህ ጠንቶ ይከፋል እንዴት አስክሬን ግጦ እንዴት አብጦ ይፋፋል ? ግድ የለም ይኸም ያልፋል ሲያልፍ ግን ብድር በምድር አይቀርምና ደም ያስተፋል ! ወስብሐት ለእግዚአብሄር ለዘበናይ ተዋናይ ! ሚስት እዚህ ባል እዛ ምነው ሲባል ሥራ ስለበዛ እህ ሲባል ጨዋታው ሌላ መጨረሻው ዋኔን እኔን ትንፋሽና ገላ ተክለ ሐይማኖት መስከረም ፲፱፻፺፮ © ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ)
𝙮𝙞𝑙𝑎𝑘 G-𝑔𝑖𝑜𝑟𝑔𝑖𝑠
Region: ET
Wednesday 20 May 2026 15:51:59 GMT
Music
Download
Comments
Germa :
ተባረክልኝ አቦ🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-12 07:48:53
2
ሠናይ-X@05 :
ፐ
2026-06-11 20:23:44
1
Żémálíc___🍂🦅 :
ውይ...ኣይ አያ ሙሌ❤️❤️❤️❤️
2026-05-24 11:08:29
1
Ras abel :
2026-05-20 16:29:24
1
ጊ~ሳልስ ፯,፲፮,፲፪ :
tichilaleh🥰
2026-05-20 17:22:08
2
kg :
ይሉ🥰🥰🥰🙏🙏🙏
2026-06-13 16:07:18
1
ሰሊና (የአባሰል ቅኝት) :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰ወንድሜ
2026-05-20 16:52:53
3
ወርቅዬ :
ይሉዬ💙💙
2026-05-22 15:59:36
2
zewdu :
2026-05-28 13:45:22
1
Alpha Mike :
አያ ሙሌን በነብስ ነው የምወደው 👌👌👌
2026-06-18 06:14:00
1
abel 24 :
አይሙሌ
2026-06-18 17:29:37
1
መራሂቡ :
አያ ሙሌ ጅብ አይበላሽ 🥰🥰🥰🥰
2026-05-21 10:36:59
1
yoni :
1 ...ay
ba senda...
2026-05-30 20:39:31
1
ንሥር :
ቅኔውን ይዘርፈው ያበጥረው ነበር🥰🥰🙏🙏
2026-07-02 19:04:17
1
Alene Molla 17 :
እኮ ማን ሆናችሁ ?!!
2026-06-27 17:30:39
1
@mekasha.27 :
❤️❤️❤️❤️❤️
2026-06-19 20:50:36
1
zershart :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰😇😇😇😇😇👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼🥰🥰
2026-07-04 02:00:15
2
bezasolomon895 :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-15 19:03:48
1
Herip0 Jegema :
😳😳😳
2026-05-21 08:37:22
1
Abebe Chala chew :
🤩🤩🤩
2026-05-21 17:29:37
1
YARED :
🥰🥰🥰
2026-05-21 19:15:54
1
eskndr :
😍😍😍😍😍😍😍😅😂🤣😋😄😀😘😍
2026-05-20 20:37:18
1
ይታገሡ :
👌👌👌🥰🥰🥰
2026-05-20 16:29:27
1
ናታኔየም ጎጃም=✟🌹12🌹21🌹27🌹✟ :
🥰🌹🥰🌹
2026-07-01 06:43:59
1
solomontesfaye432 :
❤️❤️❤️
2026-07-11 14:42:29
1
To see more videos from user @yilugg, please go to the Tikwm
homepage.