@2146efirata: ዋልድባ ፡ ዋሊ-ዱባ፡ ታላቁ ገዳም #ዋልድባ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በጸለምት ወረዳ የሚቀኝ ቆላማ እና ታሪካዊ ስፍራ ነው። ዋልድባን በሰሜን በኩል የተከዜ ወንዝ ከሽሬ ሲለየው የዘሬማ እና ትንሳኤ ወንዞችም ያዋስኑታል። ይህ በቆላማናቱ እጅጉን ለወባ ተጋላጭ እንደሆነ የሚታወቅ ስፍራ ይበልጥ ታዋቂነትን ያተረፈው በአከባቢው ባለ ዝነኛ ገዳምና በብርቱዎቹ ገዳማዊያን አባቶች ነው። ዋልድባ ስያሜውን ያገኘው “ዋሊ” ከሚል ቃል እንደሆነ በአፈ ታሪክ ይነገራል። ዋሊ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገነት ያመጣት እጽ ስያሜ ነው ተብሎም ይታመናል። የርሷም ቅጠሎች ሰፋፊና ቅርንጫፎቿ የበዙ፣ሁል ጊዜ ጠዋት አብባ በ፱ (9) ሰዓት የምታፈራ ዕፅ ናት፡፡ ዋሊ ዱባ የሚያክል ፍሬ በመያዟ በተለምዶ ዋሊዱባ በማለት ስትጠራ ቆይታ በኋላ “ዋልድባ” ለመባል በቅታለች፡፡ ድንግል ማርያም ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ ካረችባቸው ቦታዎች መካከልም አንዱ ነው የዋልድባ ገዳም። ይህንን ታሪክ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንዲህ ሲል ገልጾታል… “እመቤታችን በኪደተ እግሯ ከባረከቻቸው ቦታዎች አንዱ መሆኑ፡ የዋልድባ ገዳም እመቤታችን ወደኢትዮጵያ በስደቷ ጊዜ መጥታ በኪደተ እግሯ ከባረከቻቸው እና ጌታችን በሕፃንነቱ ትንቢት ከተናገረላቸው ቦታዎች አንዱ ነው፡፡” የዋልድባ ገዳም ታሪክ ሳብ ብሎ ወደ መጀመርያው የክርስትና ዘመናት ይጓዛል፡፡ በ5ኛው መክዘ በአካባቢው በተባሕትዎ ይኖሩ የነበሩ መናንያን እንደነበሩበት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በ485 ዓም ከሰሜን ሸዋ የተነሡ ምእመናን ወደ አካባቢው ተጉዘው መጋቢት 27 ቀን ዋልድባ መግባታቸውን የቦታው ታሪክ ያሳያል፡፡ በ574 ደግሞ ሌሎች ከቡልጋ መጥተው ተቀላቅለዋቸዋል፡፡ በዘመነ ዮዲት ቦታው ከጠፋ በኋላ እንዲሁ ሲኖር አሁንም ለሦስተኛ ጊዜ ከሰሜን ሸዋ ቡልጋ የመጡ ክርስቲያኖች አንሥተውት ነበር፡፡ በኋላ ግን በንጉሥ አግብዐ ጽዮን ዘመን (1278 - 1286 ዓም) ለጊዜው ባልታወቀ በምክንያት ገዳሙ ጠፍ ሆነ፡፡ ዋልድባ እንደገና የቀናው እና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስ ቲያን ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ የያዘው በንጉሥ ዓምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት በተነሡት በአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ነው፡፡ በ1319 አካባቢ ከደብረ ሊባኖስ የተንቀሳቀሰ አንድ የመነኮሳት ቡድን (አባ ሙሴ፣ አባ እስጢፋኖስ፣ አባ ገብረ መስቀል እና አባ ገብረ ክርስቶስ) ዋልድባ በመግባት ሥርዓተ ገዳሙን አጽንተውታል፡፡ በገዳሙ እህል መመገብ የቀረው ከእነርሱ መምጣት በኋላ መሆኑ ይነገራል፡፡ የዚህ ሃሳብ አመንጭም አባ ሙሴ መሆናቸውን የገዳሙ ታሪክ ያትታል፡፡ እነዚህ መነኮሳትም የእርሳቸውን ሃሳብ በመቀበል የገዳሙ ምግብ ቋርፍ እንዲሆን ወሰኑ፡፡ በገዳሙ እህል የሚበላው ለልደት፣ ለትንሣኤ እና ለካህናተ ሰማይ በዓል ብቻ እንዲሆንም ደነገጉ፡፡ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት (1426-1440 ዓም) የዋልድባ ገዳም ክልል በአራቱ ወንዞች መካከል እንዲሆን ዐዋጅ ተደንግጎ ነበር፡፡ ዐዋጁ ማንኛውም የሀገር ገዥ እና አራሽ ወደ ክልሉ ገብቶ ምንም ዓይነት ሥራ እንዳይሠራ የሚከለክል ነበር፡፡ የዋልድባ ገዳም እስከ ግራኝ ወረራ ጊዜ ቆይቶ በመከራው ሰዓት ጠፍ ለመሆን ደርሶ ነበር፡፡ በኋላ ግን ከወረራው የተረፉ መነኮሳት ተሰባስበው እንደገና አቀኑት፡፡ በመካከልም እየጠፋ እየቀና ለብዙ ዘመናት ኖረ፡፡ በተለይም በዘመነ መሳፍንት በነበረው የእምነት ክርክር የዋልድባ መነኮሳት ዋነኛ ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡

@Efi...21🙏
@Efi...21🙏
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 22 May 2026 07:59:38 GMT
8048
621
11
13

Music

Download

Comments

abebe.waga
🌾በረከት 🌾የራያዉ🌾ብለሺ🌾ነይ :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልሎሎሎልሎሎሎሎልልልልልሎልልልሎሎሎሎሎሎሎ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-05-22 08:15:29
1
.21934946
እናቴ እወድሻለው❤❤❤❤ :
ንገሮኘ
2026-05-22 09:39:26
1
temsgenaemlak
k"የድግልማርያምልጅ" :
ጠባቂአለኝ ክርስቶስመቸምየማይተወኝ
2026-05-22 12:13:18
1
kal22541
Kal :
🥰🥰🥰
2026-05-22 08:08:16
1
user9662704949151
dghh :
🙏🙏🙏🙏🙏
2026-05-27 12:51:34
0
birkti06
birkti :
🙏🙏🙏
2026-05-24 10:30:56
0
user4075270849716
የሚካኤል❤ልጅ :
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
2026-05-23 07:56:22
1
birkti06
birkti :
🙏🙏🙏🙏
2026-05-24 10:31:09
0
betelhemazanewu
Betelhem Azanewu :
🙏🙏🙏🙏🙏💝💝💝💝💞💞💞💞💋💋💋💋💖💖💖💖💖💖
2026-05-27 01:06:17
0
mercythe21
mercyThe➋➊ :
🥰🥰🥰
2026-07-05 08:22:01
0
habtamutsega145
habtamu :
🥰🥰🥰
2026-07-23 03:41:34
0
To see more videos from user @2146efirata, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About