@musictube369: እወድሻለሁ 🫠🤎 ✍️በመዝሙር የተቀደሰው የቅንብር ጅማሮ ነፍሱን ይማረውና የከተማው መናኝ ታላቁ ኤልያስ መልካ 🎸 አሁን ወደ አለበት የዝና ከፍታ ላይ ከመውጣቱ በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ማቀናበርን የተለማመደው በመዝሙር ነበር፡፡ ዝማሬዎችን ለማቀናበር የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቱ በሩን ቀስ በቀስ አስፍቶለት ነበር። በየመድረኩ ላይ ከጓደኞቹ ጋራ በሚያቀርቡት የመዝሙር ማጀብ ሥራ ታዋቂነትን ያገኙበት ዘመን ነበር። ጊዜው በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ውስጥ ሙዚቃ የሚጠናበት እና የጃዝ ሙዚቃዎች የሚደመጡበት ስለነበር ጠንካራ የኾኑ «ኮርዶችን» እያስገቡ መጫወትን እንደ ጀብድ እና ከበድ ያሉ ነገሮችን በመቀላቀል ሰዎችን ለማስደመም ጥረት የሚደረግበት እንደነበር ይገልጻል ኤልያስ። ✨ውድ ቤተሰቦቼ ኤልያስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስተኛውን የአገኘሁ ይደግን መዝሙር እንዲያቀናብር ሲጋበዝ ይህንኑ የመደነቅ እና የማስደመም ፍላጎት ተንተርሶ ቀላቅሎ በማቅረቡ በመዝሙሩ ላይ ተገቢ ያልኾነ የቅንብር ሥራ ማከናወኑን እስከዛሬም ይጸጸትበታል። 📌፤፨፠፨፤ ― በመዲና እና በኮንኮርድ ይኹን እንጂ ያንን ያደረገው ከቅንነት ማጣት ወይም ኾነ ብሎ ለማበላሸት አስቦ አልነበረም። «የወጣትነት እና የፍንዳታ ዘመን ስለነበረ ነው።» ይላል፡፡ በጊዜው ቤት ውስጥ የነበሩት ሰዎች እናቱን ጨምሮ መዝሙሩ አልዋጥላቸው ሲል መባነን እንደነበረበትም ያወሳል፡፡ ወቅቱ ስለ ኤልያስ የጊታር ችሎታ የሚጠራበት ስለ ነበር እርሱን እና ጓደኞቹን እና ዮሐንስ ጦናን ለማጫወት የሚፈልጉ ባንዶች ነበሩ። ኤልያስ ቀልጣፋ እና ራሱን መሸጥ የሚችል ዐይነት ሰው አልነበረም፡፡ ከአዋሳ የመጣው ዮሐንስ ጦና ግን ችሎታውን ለማሳየት እና ራስን ለማስተዋወቅ የማይፈራ ልጅ ነበር። ይላል ኢልያስ። ኤልያስ የአራተኛ ዓመት ተማሪ እያለ ከመዲና ባንድ ጋራ የመጫወትን ዕድል አገኘ፣ አጨዋወታቸውን ያየው የመዲና ባንዱ እዝራ አባተ የባንዱ ሰዎች በማይኖሩበት አጋጣሚ እነ ኤልያስ እየተኩ እንዲሠሩ አደረጋቸው። በአንድ አጋጣሚ ትዕግሥት በቀለ መድረክ ላይ ስትጫወት የባንዱ ጊታሪስት አልተገኘም ነበር። ኤልያስ ያን አጋጣሚውን ተጠቀመበት። «ሙዚቃው የጃዝ ዐይነት አጨዋወት ስለነበረው ልምምድ ባላደርግም አብሮ በተለመደ አጨዋወት ለመጓዝ ያን ያህል አዳጋች አልኾነብኝም» ይላል ኤልያስ። ከዚያ በኋላ ኤልያስ ቀጥታ የተዛወረው መዲና ባንዶች ይሠሩበት ወደነበረው ኮንኮርድ ሆቴል ነበር፡፡ ትንሹ ልጅ ኤልያስ በተቀጠረበት ሰዓት የኮንኮርድን ናይት ክለብ በሮች አልፎ ለመግባት የሚያስችል ዕድሜ ላይ አልነበረም፡፡ ኻያ አምስት ዓመት ያልሞላው ሰው ወደ ውስጠኛው የናይት ክለብ ክፍል መግባት አይችልም፡፡ ኤልያስ በመዲና ባንዶች ዕገዛ ወደ ውስጥ ዘለቀ። ኤልያስ በዚያ ዐይነቱ ደብዛዛ ብርሃን ወስጥ የሚያያቸውን ትዕይንቶች ለማመን ተቸግሯል። ይህ ዐይነቱ ሕይወት ለእርሱ በጣም ሩቅ እና ሰምቶትም እንኳ የሚያውቀው አልነበረም፡፡ ለወጉ ያህል ጨርቅ ጣል የተደረገበት የሴት ገላ የወንዶች እቅፍ ውስጥ ኾነው መዚቃ እየሰሙ የሚውረገረጉ ጉብሎች ሲጋራ እንደ እጣን የሚትጎለጎለበት እና ሲጋራ ካልተጨሰ ቆሌው የማይታረቀው የሚመስለውን ምሽት መመልከት ለኤልያስ በሕልም እና በእውን መካከል እንደመቃዠት ነበር፡፡ 📌፤፨፠፨፤ ― የኤልያስ የዕንቅፋት ደንጎች ቀስ በቀስ ግን ኤልያስ ለራሱ እንግዳ በነበረው የጨለማው ዓለም ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ መኾን ጀመረ፡፡ «የባንዱ መሪ እዝራ ሙዚቃውን ከተጫወትን በኋላ በቀጥታ ወደ ቤታችን እንድሄድ ርምጃችንን ሳይቀር ለመቆጣጠር ጥረት ያደርጋል፡፡ ነገር ግን እኔ እየተደበቅኹ ማጨስ ጀመርኩ።» ይላል። ለኤልያስ የጥፋት የሚባሉት ግመታት የተጀመሩት ያኔ ነበር፣ በመድረክ ላይ የሚወራው ሙዚቃ እና የሚያቀናብረውን መዝሙር ከኢትዮጵያ የዘፈን ሙዚቃ ጋራ እንዴት አድርጎ ማጣጣም እንዳለበት ማሰብም ጀምሮ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የመሐሙድ አሕመድን «ሁሉም ይስማ» እና አንድ የጉራጊኛ ዘፈን አቀናበረ፣ ከዚያ በኋላ የቴዲ አፍሮ - «አቡጊዳ»ን ሙሉ ካሴት ሠራ፣ ኤልያስ ከመድረክ አልፎ ወደ አደባባይ እና ወደ ሕዝብ ጆሮ ሲገባ «ያሳደግኹት ልጄ እና ንብረቴ ነው።» የሚለው የፕሮቴስታንት አማኞች ጥያቄ የሚዲያዎች ትልቁ የመወያያ ርዕስ ሆኖ ነበር፡፡ ከዚያም ባሻገር በቴዲ ሥራ ላይ ስሜ አልተጠቀሰም የሚለው ኤልያስ በአደባባይ የወቅቱ ዜና ኾኖም ነበር። የፕሮቴስታንት መጽሔቶች ኤልያስን ቃለ መጠይቅ እያደረጉ «ስለምን ወደ ዓለማዊ ሙዚቃ ገባህ?» እያለ ይሞግቱታል። ስለ ድካሙ የሚከፈለው የገንዘብ ጥያቄም የርእሰ ጉዳዩ አንዱ አካል ነበር፡፡ ኤልያስ ያን ጊዜ የሰጣቸውን አብዛኞቹን ቃለ ምልልሶች «ከጉርምስና እና ከጀብደኝነት ጋራ የተያያዘ» ሲል ይገልጻቸዋል፡፡ ያኔ ለሚነሱት ጥያቄዎች ሁሉ የመሰላቸውን መልስ መስጠትን እንደ ግዴታ የሚቆጥሩበት አጋጣሚ ትክክል አለመኾኑንም ያወሳል። «ገንዘብ ያስፈልገናል የሚል ጥያቄ አስቀድሜ ሳላነሳ የገንዘብ ችግር አለ ብዬ ቤተ ክርስቲያንን መውቀስ አግባብ አልነበረም።» ይላል፡፡ ፤፨፠፨፤ ― ምዑዝ ኤልያስ ― ፤፨፠፨፤ ኤልያስ ሕይወቱን በሙዚቃ ቅንብር ባሳለፈባቸው ዓመታት ውስጥ የራሱ የኾኑ ዘመናት ነበሩት፡፡ የእነ መሐሙድ አሕመድ እና ቴዲ አፍሮ ዘመን፣ የእነ ጎሳዬ ተስፋዬ እና የእነ ይርዳው ጤናው ዘመን እንዲኹም የእነ አብነት አጎናፍር፤ የእነ ዘሪቱ ከበደ እና የእነ ኢዮብ ዘመን ብለን ልንከፍላቸው እንችላለን ይላል ሰርፀ፡፡ ለኤልያስም እነዚህ የዘመን ክፍፍሎች ይስማሙታል ዘፈኖቹን ወደ ኋላ ተመልሶ ባደመጣቸው ቁጥር የቅንብራቸው መዓዛ ዜማዎቹን የሠራባቸውን ዘመናት ያስታውሱታል። ለዜማ ትኩረት የሚሰጥባቸው ጊዜያት ነበሩት:: የትኛውንም ግጥም ከዜማው ጋራ እንዴት አድርጎ ሊያሰናስለው እንደሚችል ብቻ ያስባል፡፡ ዘፋኞቹም የመጣውን መልእክት ሳይነካባቸው ማስተላለፍ ይሻሉ፡፡ ዜማን በቅንብር ክሂሉ የሚያጣፍጠው ምዑዝ ኤልያስ ዜማውን የሚያደናቅፍ ነገር እስካልገጠመው ድረስ የግጥሞቹ ይዘት እና መልእክት ያን ያህል አያስጨንቀውም ነበር፣ አሁን ግን እንደዚያ ማሰቡን እቁሟል፣ በፈን ውስጥ የሚተላለፉ መልእክቶች የአድማጭን ብሶት የሚያጠናክሩ ያዘነውን የሚያስለቅስ፤ መለያየትን የሚያበረታቱ እና ዝሙትን እና ኃጢያትን የሚያሞካሹ መኾን የለባቸውም የሚል አቋም ላይ ደርሷል፡፡ ከዚህ መለኪያ ፈቀቅ የሚል ካለም ሌላ አቀናባሪ እንዲሠራለት ይልከዋል እንጂ በዚህ ላይ መደራደርን አይመርጥም፡፡ «ይህ አቋም ኤልያስ ከአቀናባሪነት ወደ ፕሮዲዩሰርነት ራሱን ያሸጋገረበት ነው።» ይላሉ የሙዚቃ ባለሞያዎቹ። «ራሱ ፕሮዲዩስ ያደረጋቸው የኢዮብ እና የዘሪቱ ሥራዎች ስኬታማ ሆነውለታል።» ይላል ሰርፀ።የኤልያስ ወደ ፕሮዲውሰርነት ማደግ ከዜመኝነትም ባሻገር ወደ ገጣሚነት ከፍ ከማለቱ ጋራ ይያያዛል። የኢዮብን ዐሥሩን ሥራዎች በግጥምም በዜማም የሠራው እርሱ ነው። የግጥሞቹ አብዛኞቹ ቃላት እና የመልእክት ይዘታቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ያ ቀጥተኛ ተጽእኖ በኤልያስ ላይ የታየው ለማንበብ የሚመርጠው ብቸኛ መጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ስለኾነ ነው። አንዳንዶች ይህ ምርጫው «ዘፈኖችን በዘፈን እና በመዝሙር መካከል የሚዋልሉ» እንዲኾኑ አድርጓቸዋል ብለው ያምናሉ። 📌........ ይቀጥላል🙌 🗣️ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 #fyp #አብነትአጎናፍር #እወድሻለሁ #musictube369

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 24 May 2026 20:07:57 GMT
132553
11080
84
2209

Music

Download

Comments

tizitanegash
Luuna🌙✨ :
this is deep eko🥰 elaye🔥
2026-05-24 20:49:09
51
abdiabdu842
ብሩክ :
caption☺️
2026-05-29 05:30:56
6
nihilisthabesha
You Live and You Learn :
Abnet and Elias really complimented each other. This album and the next were magnificent.
2026-06-06 21:30:13
3
jossymichaele555
Jossy :
ኤልያስ the Goat 🙏🙏🙏🙏
2026-05-25 20:45:51
6
memehouse_2
Nature 🌿 :
eli melka 👑
2026-05-25 05:45:47
18
liyu_awit
liyu :
Here u are, to impress us as always 👏
2026-05-27 20:30:38
2
ocote27
mule :
its my ringtone
2026-05-26 09:35:33
9
thodore121
Ţěďį :
The best music forever 👌👌👌✌
2026-05-26 18:50:01
4
yedaddyfitsum1328
Fitsumyeee🐼 :
2026-05-25 17:29:47
7
ermiyas_t
Ermiyas_t :
👑🎸🎹🎶🔥♾️🇪🇹🐐ela
2026-05-25 04:12:00
3
yabesrajosefeame
ቤተልሔም :
ኤላ❤
2026-05-25 09:52:15
2
frozicool24
𝖋𝖗𝖔𝖟𝖊𝖓🕊 :
🥰🥰
2026-05-25 11:55:52
5
ermiamdwuwd
ERMIAS :
አሜን አሜን አሜን 🙏🙏
2026-05-27 17:07:02
1
k_rise0
K_Rise :
90s የተባረከ ዘመን 🥰🥰
2026-05-25 20:38:41
5
addisnegash_edudu
Addis negash :
I love u people 🥰
2026-05-26 16:14:49
1
miko1520ys
Miko xo :
letest music 🎶 🔥
2026-05-25 21:04:51
1
yefedlu1
yefedlu1 :
ዘመኔ
2026-05-25 18:24:58
1
emaye210
Endu✌ :
jordi🥰
2026-05-25 17:08:41
2
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About