@yilugg: ልጄ ሆይ … ጠቢብ ሁን፣ ልቤንም ደስ አሰኛት! ልጄ ሆይ … ቃልህን ጠብቅ … ዕምነትህን አጥብቅ … የሰው ልጅ የውበቱና የጉልበቱ ምንጭ ከከናፍሮቹ እንደሚቀዳ አትዘንጋ … ማስተዋል ብቻ ነው የህያው ዓይኑ … ሌላው ብሌንም በለው ምንም … ያው የኖርክበት በብረቱ ነው … ትላንት ሸኝቶሃል … ዛሬም ተቀብሎሃል … ነገም የሞት ቀጠሮ ብሎ በክብር አድሞሃል … ጀምበር‘ንኳ የምትፈልቅበት የምትጠልቅበት ጉዳይ ውስጥ አንተም አለህበት … ክቡር ነህና ባምሳሉ የተፈጠርክ … በባህሪው እስኪሰርፅህ ድረስ ጭራሽ እንዳትቦዝን … በእንቅልፍ ሳይዛመድ መልአከ ሞት ማንም ቤት ገብቶ አያውቅም… ስትነሳ ብቻ ተጠንቀቅ … ስትጀምር ብቻ አረጋግጥ፣ መነሻህ ልክ ከሆነ መድረስህ አያጠያይቅምና - ማንስ ቢሆን የዘራውን እንጂ ምኑን ያጭዳል … ከመማር በላይ ጽድቅ ካለ ጭራሽ አልመኝም … ፊደል ውስጥ ገድል አለ … ፊደል ውስጥ ዕድል አለ … ፊደል ውስጥ ድልድል አለ … ብሎም ፊደል ውስጥ ድል አለ … ቀኑን ተማርበት ሌቱን ዘምርበት … ይህን ያልሳተ ነው ሁሌም የሚያምርበት ያለውን አዝማሪ መቼም አልረሳውም … ከጎራ ወዲያ ያለውን አገር ስንቅና ትጥቅ ከምፈጅ … አስቀድሞ ገልጦልኛል … ይኽውልህ ልጄ ሆይ … ያደለው ለሌላውም ብርሃን ይሆናል … ግር ሲለው ደግሞ ቁልፉን በቀኝ እጁ እየወለወለ አገሩን ቀውጢ አርጎ ውደዱ እያለ ያምሳል … ከልብህ አትራቅ፣ ከሙክራብህም አትውጣ … ይኽ ጽንፍ አልባ የሚታይህ ገፋፊ አለም ማንም በሰፋው ቁና ልስፈርህ ቢለው የሚቀመስ እንዳይመስልህ … በዕድሜ ዘመኔ ያየሁት አንድ ሃብታም ሰው ብቻ ነው … የዚያም ሰው ንብረቱ … “ሁሉም ከድካም ይታጨዳል” የሚለው መቼም የማይናወጥ ጽኑ ዕምነቱ ነው … ከስስት በላይ የሥጋ ደዌ በሽታ አለ ቢሉኝ እያየሁት‘ንኳ ቢሆን አላምንም … ለገስኩ ብሎ ደሞ ለውዳሴ ከንቱ እየዘራ፣ እያጨደ፣ ቤቱ ወስዶ ሊወቃ እንደሚያግዘው ግን ሲኦል የለም … ይህ የኔ የግል ነው ብለህ በባለቤትነት የያዝከው አንዳችም ነገር እንደሌለ ልቦናህ ጠንቅቆ እያወቀው … በግልባጩ ደሞ አንተ እንዴት ሁሉም የኔ አልሆነ ብለህ ካልሆነ የምትጨነቀው … ቋንቋህ ፍቅር ከሆነና ውሎና አዳርህ ሰላማዊ ከሆነ … ቢያንስ በሕይወት መንገድ ላይ ነህና ዕድለኛ ነህ … ቸር እንሰንብት ሙሉጌታ ተስፋዬ #onthisday
𝙮𝙞𝑙𝑎𝑘 G-𝑔𝑖𝑜𝑟𝑔𝑖𝑠
Region: ET
Sunday 24 May 2026 21:05:34 GMT
Music
Download
Comments
Sandeepa basorya :
አያ ሙሌ🥰🥰🥰
2026-07-17 10:10:33
1
Aminu :
ሸክ አብዱ 🥰🥰🥰 መገን አያ ሙሌ 🥰🥰🥰🥰
2026-06-13 11:38:38
0
Biruk S :
አያ ሙሌ
2026-06-25 18:58:25
1
og :
abo seneke eske genete dejafe!!!
2026-07-15 08:31:01
0
Reset :
🥰🥰🥰🥰
2026-05-26 02:59:41
2
yaአfaሯ🌙 :
❤️🥰
2026-05-26 06:43:40
2
shaftshaft118 :
🌷🌷🌷
2026-06-07 02:16:18
1
Yalelet Ababaw Abebe :
🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-25 01:50:01
1
meko :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰❤️❤️❤️
2026-06-06 03:06:25
1
worku moges :
🙏🙏🙏
2026-06-19 21:54:58
1
Abebe Chala chew :
👍👍👍
2026-06-12 18:57:59
1
gediyon daniel gedi betera :
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-06-22 12:35:08
1
@ tesfaye :
🥰🥰🥰
2026-06-29 20:32:17
0
Elias Helem :
🥰🥰🥰
2026-07-17 22:11:09
1
BMW man :
🥰🥰🥰😏😏😏😳😳😳
2026-05-25 11:46:54
2
To see more videos from user @yilugg, please go to the Tikwm
homepage.