@goldenadvise4: 🗯️ትክክለኛ እና እውነተኛ የህይወት አስተማሪዎች ልባችንን አድምተው፣አቁስለው፣ጎድተውና ሰባብረው ዞር ያሉ ሰዎች የህይወትን ትክክለኛ ትምህርት አስተምረውን ያልፋሉ። 🗯️አንዳንድ ሰዎች ትክክለኛ ማንነታቸውን አሳይተው ትክክለኛውን የህይወት ትምህርት አስተምረውን ያልፋሉ።ህይወታችሁ ውስጥ ገብተው በጎዷችሁ ሰዎች በፍፁም አታልቅሱባቸው፣አትናደዱባቸው፣አትዘኑባቸው ፣አታማሩባቸው። 🗯️ ይልቁንስ የህይወታችሁ ምርጥ አስተማሪ በመሆናቸውና ድጋሜ እንዳትሳሳቱ አድርገው ሊያስተምሯችሁ ከፈጣሪ ስለተላኩ አመስግኗቸው።ምክንያቱም ፈጣሪ ከሰጠን ነገር ውስጥ መጥፎ የለም፤ከከለከለን ነገር ውስጥም ጠቃሚ ነገር የለም።ፈጣሪ በስራው ሁልጊዜ ትክክል ነው። 🗯️በዚች ምድር ብዙዎቹ የማያጡ መስሏቸው አጥተው አይተናል፣የማያማቸው መስሏቸው ታመው አይተናል፣የማይወድቁ መስሏቸው ወድቀው አይተናል፣የማያረጁ ውበታቸውም የማይረግፍ መስሏቸው አርጅተውና ውበታቸውም እረግፎ አይተናል። 🗯️ከፀሃይ በታች ምንም አድስ ነገር የለም።ቀን ምን እንደሚያመጣብን ወይም ምን እንደሚያመጣልን አናውቅም።ባለን ነገር ሳንመካ፣ሰውን ሳንንቅና ማንንም ሳናቋሽሽ በፈርሃ እግዚአብሔር እንኑር።ሁልጊዜም በጨዋነት እንኑር፤ዛሬውኑ መጥፎ አመላችንን አስወግደን የጥሩ ባህሪ ባለቤት እንሁን!!! 🗯️በዚህ አለም ላይ ያለ ነገር ሁሉ ጠፊ ፣ሁሉ አላፊ ነው።ከዚህ አለም ከነፍሳችን ጋር ይዘነው የምንሄደው ብቸኛ ነገር ባህሪያችን፣ምግባራችንና ስራችን ብቻ መሆኑን አንርሳ።ጥሩ ሰው ለመሆን ጊዜና ምክንያት አትፈልግ።ጥሩ ሰው ለመሆን ካሰብክ በልብህ ቅን ማሰብ የመጀመሪያ ተግባርህ ይሁን።ፈጣሪ ፊት ይዘኸው የምትቀርበው ድግሪ፣ኘሮፌሰር ወይም ፒኤችዲ ሳይሆን በንስሃ የታጠብክበትን ስጋውና ደሙን ብቻ ነው። 🤌🏾 ሁሉም ሰው ይማርበት ዘንድ ሸር አድርጉት🙏🏽 እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን 🙏እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኒቴ ነው። ሰናይ ምሽት ይሁንላችሁ ❤️❤️እወዳቹሃለው❤️❤️ #fyp #fypシ #foryoupage #foryou #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 @Manyazewal Eshetu @adonaymada444
ወርቃማ ምክሮች
Region: ET
Thursday 28 May 2026 15:50:48 GMT
Music
Download
Comments
haymi :
amen
2026-05-29 11:26:20
1
Shwa :
አሜን
2026-05-28 17:18:22
1
senkensh :
amene🙏🥰❤️
2026-05-31 16:55:15
0
🇪🇹brukti ✝️የድንግል ✝️ማርያም ✝️ልጅ :
🙏🙏አሜንንን አሜንንን
2026-06-02 20:38:44
0
Ayle Setegn :
አሜን
2026-06-19 22:18:52
0
farxiyaxashi3 :
ትክክል 🙏🙏🙏🙏💞💞💞💞💞💞🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-31 04:35:51
0
farxiyaxashi3 :
አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏
2026-05-31 04:25:27
0
Baye 27 :
🙏🙏🙏
2026-06-04 17:04:19
0
ናፍቆት :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-06 10:16:55
0
To see more videos from user @goldenadvise4, please go to the Tikwm
homepage.