@hahu.digitals: ብድር የሃብት ምስጢር መሆኑን ታውቃለህ ብድር የሃብት ምስጢር ከሆነ ለምን ድሮ ስንማር ትምህርት ቤት ውስጥ አላስተማሩንም? መልሱ ያስደነግጣል፡፡ ምክንያቱም ብድር/ዕዳ በትክክል እንዴት እንደሚሰራ በተረዳችሁ ቅጽበት፣ ከፍተኛ ግብር ከፋይ መሆናችሁ ያበቃል።መቀጠርን እምቢ ትላላችሁ፡፡እናንተ አልቀጠርም ካላችሁ ባለሃብቶች እና ድርጅቶች ማንን ቀጥረው ያሰሩ?ትምህርት ቤቶች የሚያዘጋጁህ እንዴት ተቀጥረህ እንደምትሰራ ፤እድሜ ልክህን እንዴት ለገንዘብ እንደምትሰራ እንጅ እንዴት እንደምትነግድ ወይም ገንዘብ ራሱ ለአንተ እንዴት እንደሚሰራ አይደለም፡፡ አብዛኛው ሰው ብድርን/ዕዳን እንዲፈራ ነው የሰለጠነው።ሀብታሞች ግን እንዲጠቀሙበት ነው የሰለጠኑት። ለምን እንደሆነ ላስረዳህ። ገንዘብ ስትበደር፣ አንድ ሳንቲም እንኳን ታክስ አትከፍልም ለምን? ምክንያቱም መንግሥት የተበደርከውን ገንዘብ እንደ "ገቢ" አይቆጥረውም።ታክስ አይጣልበትም። ቅጣትም የለበትም። ትምህርት ቤት ውስጥ ፈጽሞ የማንማረው ነገር ይሄ ነው ፡፡ ብድር/ዕዳ ማለት በትክክለኛው ትርጉሙ ገንዘብ እንዴት እንደሚፈጠር የሚያሳይ ቁልፍ ነው። ባንክ በየጊዜው ገንዘብ በሚያበድርበት ጊዜ፣ አዲስ ገንዘብ ወደ ሥርዓቱ ይገባል። ለዚህ ነው ባንኮች ተበዳሪዎችን በጣም የሚወዱት። ዕዳ /ብድር ሥርዓቱ እንዲያድግ ይረዳል።አሁን የሚገርመው ክፍል እዚህ ላይ ነው... ገንዘብ ስትበደር፣ ለጥሬ ገንዘብ ፍሰት (Cash Flow) መገንቢያ ትጠቀምበታለህ፡፡ እንዴት እንደሆነ ላሳይህ ፡፡ከታክስ ነጻ የሆነ ብዙ ገንዘብ ተበደር እና በገንዘቡ ወርሃዊ ገቢ ሚያስገኝ ንብረት ግዛበት፡፡ ከዚያ ንብረቱ በየወሩ ጥሬ ገንዘብ እንዲያመጣ አድርግ፡፡ዕዳውን ለመክፈል በየወሩ የምታገኘውን ጥሬ ገንዘብ ተጠቀም፡፡ አየህ ያልተቋረጠ ወርሃዊ ገቢ የሚያመጣልህ አንድ መሳሪያ አገኘህ ማለት ነው፡፡ ገንዘብ ለአንተ ይሰራል ማለት ይህ ነው፡፡በቃ የገዛኸው ንብረት እራሱ ለገንዘብ ይሰራልሃል እንጅ አንተ ለገንዘብ አትሰራም፡፡ ከአንተ የሚጠበቀው ትክክለኛ ብድር መውሰድ ነው፡፡ እውነተኛ እሴት ለመፍጠር ባለሀብቶች ዕዳ /ብድር በብዛት ይጠቀማሉ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የፋይናንስ እውቀት የሌላቸው ሰዎች እዳን/ብድርን የሚጠቀሙት የበለጠ ደሃ ለመሆን ነው፡፡ አብዛኛው የፋይናንስ እውቀት የሌለው ሰው ዕዳን የሚጠቀመው መኪና ለመግዛት፤ለመዝናኛ፡ለሰርግ፤ለሌሎች ድግሶች ፤ለፍጆታ ዕቃዎች፤አቅም የማይፈቅድላቸውን እና ምንም ገቢ የማያስገኙ ትልልቅ ቤቶችን ለመግዛት በአጠቃላይ ገቢ ከማስገኘት ይልቅ ገንዘብ ከኪስ የሚያስወጡ ነገሮችን ለመግዛት ይጠቀሙበታል፡፡ ለምሳሌ እኔ የማውቃቸው ብዙ ሰዎች ተበድረው ሰርግ የደገሱ አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች እድሜ ልካቸውን ብድር ሲከፍሉ ከመኖር ውጭ ምንም አማራጭ የላቸውም፡፡ይህ የፋይናንስ ትምህርት እጥረት ችግር ነው። ታዲያ ትምህርት ቤቶች ለምን ይህን አያስተምሩም? በጣም ቀላል ነው፡፡ትምህርት ቤቶች የተነደፉት ሠራተኞችን ለመፍጠር እንጂ ባለሀብቶችን ለመፍጠር አይደለም። ሠራተኞች ለገንዘብ ይሠራሉ።ባለሀብቶች ገንዘብ ለእነሱ እንዲሠራ ያደርጋሉ። ሠራተኞች ከፍተኛውን ታክስ ይከፍላሉ።ባለሀብቶች ዝቅተኛውን ይከፍላሉ። ትምህርት ቤቶች ዕዳ/ብድር እንዴት እንደሚሠራ አስተምረው ቢሆን ኖሮ ሰው ብድርን/ዕዳን አይፈራም ነበር። በደሞዝ ላይ ጥገኛ አይሆንም ነበር። የውሸት ገንዘብ አያጠራቅምም ነበር። ለመንግሥት ብቻ በሚመች ስሥርዓት ውስጥ አይቆይም ነበር። ድሆች ይበደራሉ፤ ይበልጥ ይደኸያሉ።ሀብታሞች ይበደራሉ ፤ ይበልጥ ይበለጽጋሉ። ችግሩ ዕዳው አይደለም።ችግሩ በዕዳው የምትገዙት ነገር ነው። ስለዚህ የፋይናንስ ነፃነት ከፈለጉ ከዚህ በኋላ "ብድር ጥሩ ነው ወይስ መጥፎ?" ብለው መጠየቅ ያቁሙ። ይልቁንስ ይህን ይጠይቁ፦"ይህ ዕዳ ወደ ኪሴ ገንዘብ ይጨምራል ወይስ ከኪሴ ያወጣል?" ይህ አንድ ጥያቄ ድሆችን ከሀብታሞች ይለያል።ትምህርት ቤቶች ይህን ፈጽሞ የማያስተምሩት ለዚህ ነው። አንድ ነገር አስታውስ ይህ ሁሉ በዙሪያህ ያለው ባለሃብት ሃብታም የሆነው በራሱ ገንዘብ እንዳይመስልህ፡፡በብድር ነው፡፡ነገር ግን ብድሩን ከወሰደ በኋላ የተበደረውን እጥፍ በአጭር ጊዜ የሚያመጣለት ቢዝነስ ላይ ኢንቨስት ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ምትበደር ከሆነ በጭራሽ ለወጭ መሸፈኛ ብለህ እንዳትበደር፡፡ለቢዝነስ እና ለኢንቨስትመንት እንጅ በል ፎሎው አድርግ
Hahu Digitals
Region: ET
Saturday 30 May 2026 08:51:31 GMT
Music
Download
Comments
ሱላማጢስ {Leli} :
what about ወለድ ..?
2026-05-30 19:46:26
86
mesu ye hana :
ብድር ከማይፈሩት አንዱ ነኝ ተጠቅሜበትም አለሁ አመሠግናለሁ🙏
2026-05-31 15:12:27
63
Wubneh Betru :
በሚገባ አደርግልርሁ።🥰🥰🥰
2026-05-30 14:30:54
41
Human Health (የሰው ጤና) :
I would like to thank you for your best information .
2026-05-30 17:28:36
32
v1 ✌️⚡️💸 :
አረፈድክ አሁን ለምን ነገርከኝ 🥺
2026-05-30 19:59:51
27
Maereg Moges :
100%
2026-05-30 15:15:33
14
Famu :
10x copy link
2026-06-05 07:38:53
3
21 :
ተባረክ ኣይኔን ነው የገለጥክልኝ
2026-05-31 05:38:41
15
Eba K. :
Thanks
2026-05-30 20:40:28
5
Next :
WOW👏👏👏 የምገርም ትምህርት ነው 👍እሄንን ሃሳብ እና ትምህርት ላኔ እንድዴርስ post ስላደረጋችሁት የምር ከልብ አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏መጀመርያ እንደ እኔ ብድርን ምፈራው አለ ብዬ አላስብም ነበር ነገር ግን በ 1 video post እራሴን ታዘብኩኝ ደፋርም ሆንኩኝ 👍እንደ ምመስለኝ ከ ሆኔ የ ወደ ፊት ህዎቴ ካሁን ቡሃላ ቁጭ ብዬ የማማሪርበት ህዎት ሳይሆን ከ ሌሎቹ እኩል የምሆንበት ህዎት ይመስለኛል 👍ግን አሁንም ደግሜ ደጋግሜ ለናንተ ምስጋና አቀርባለሁኝ 🙏🙏🙏 ለ ሁሉም ነገር ግን እግዚአብሔር ከ ጎኔ ከሆኔ እኔም እንደ ሰው ስራ ፈጥሬ ለ ሌሎች የ ስራ ዕድል ምፈጥርበት ሰው እሆናለው thanks👍👍👍 መረጃዉን ወድጀዋለው ህዎቴን ምቀይርልኝ ነገር ነው ብዬዋለው 👍ሌሎቹም እንዲደርሰን እና እንድንማርበት ቪዲዮዉን ቶሎ ቶሎ ልቀቁልን 😘👍🙏🙏🙏🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝
2026-06-10 16:43:50
6
Amar wedi Raya :
የምገርም ኣሪፍ ምክር ነዉ 🥰🥰🥰
2026-06-01 08:48:41
6
Ephrem Yohannes :
እናመሰግናለን
2026-05-30 16:24:34
5
zola@ride :
ጥሩ ትምህርት እናመሰግናለን 😍
2026-06-10 16:42:09
4
Ⓐነኝ የእናቴ አፍቃሪ⓯🔐☪️🇪🇹💞🎧 :
አቦ ፈጣሪ ይሰጥልን በጣም እናመሰግናለን👏
2026-06-07 19:33:59
3
emon :
2026-05-31 07:13:10
2
Mark A :
ሌላ ሀሳብ ጨምርልን
2026-06-07 11:24:17
2
yemiifashion👗👚👙🥼🧣👕 :
🙏🙏🙏🙏 Tebedire mekina ligeza nbr hasaben endastekakil sileredahegne tnx
2026-06-13 06:35:35
3
Abrshi ማን :
ዘመንህ ይባርክ
2026-06-07 07:04:07
2
እመን እጂ አትፍራ❤❤❤1930 :
አመሰግናለው በጣም በጣም ማንም yalnegeregnn እውነት slenegerkegn❤️
2026-05-30 18:51:59
6
B12@ :
1ኛ 🙏🙏🙏
2026-05-30 15:57:28
5
Abinet blke mane :
ተባረክ
2026-06-09 07:42:39
1
Iskee smart🇪🇹 :
Thanks bro
2026-06-06 21:36:50
1
Diro :
wow thanks
2026-06-09 20:18:56
1
wubet@@@ :
Thanks bro👌
2026-06-08 16:33:38
1
Mulugeta abera Yigzaw :
2026-06-01 15:45:47
1
To see more videos from user @hahu.digitals, please go to the Tikwm
homepage.