@3in1liy: ዛሬ ከጓደኛዬ ጋር ተቀምጠን ስለ ሕይወት እና ስለ ውስጥ ስሜታችን እናወራ ነበር። ሰው አንዳንዴ ታሪኩን ሲነግርሽ የምትሰሚው ቃላቱን ብቻ አይደለም… ከቃላቱ ጀርባ ያለውን ሕመም፣ ዝምታ፣ ጥንካሬ እና እምነት ነው። በወሬያችን መካከል ከሆስፒታል የለቅሶ ድምፅ ተሰማን። ያ ድምፅ እንደ ብርቱ ንፋስ ልብን የሚነካ ነበር። በዚያ ቅጽበት እሷ የተኛችባትን አክስቷን አሰበች… እኔም ያጠውትን ያሳደገኝን አባቴን አሰብኩ። በዝምታ ተሞልተን ነበር… ግን ያ ዝምታ በውስጡ ብዙ ታሪኮችን ይዞ ነበር። እኔ ስለ አሳደገኝ አባቴ ፍቅር ነገርኳት… ስለ ጥሩነቱ… ስለ ቀልዶቹ… ስለ እንክብካቤው…ስለ ጠረኑ እና ስለ አባትነት ሙቀቱ። ግን ያ ቃል ብቻ አልነበረም… ከልቤ ውስጥ የተቀመጠ ትውስታ ነበር። ልጅ ሲናገር የማይታይ ፍቅር፣ ግን የሚሰማ ሙቀት። እሷ ግን በጸጥታ አዳመጠችኝ። አይኖቿ ብዙ ነገር ይናገሩ ነበር… ግን ቃላት አልነበሩም። ከዚያም ቀስ ብላ እንዲህ አለችኝ፦ “እኔ የአባቴን ጠረን አላውቅም… የማውቀው የጌታዬን ጠረን ነው።” ያ ቃል ብቻ አልነበረም… ዝምታን የሚሰብር ህመም ነበር። በአንድ ቃል ውስጥ የተደበቀ ሕይወት ነበር። ከዚያ በኋላ ታሪኳን ስትነግረኝ ተረዳሁ… እናቷ በብዙ መከራ እንዳሳደገቻት… ብዙ እንባ እንዳለፈባት… ብዙ ነገር እንደጎደላት። ግን በዚያ ጉዳት መካከል አንድ ነገር አልጠፋም ነበር… 'እምነት'!! ሰው የልሞላላትን ቦታ ጌታ ሞልቶላታል… ሰው ያልሰጠውን ፍቅር ጌታ ሰጥቷታል… ሰው ያልቆመበትን ጥላ ጌታ ሆኖላታል። እኔ ግን በዚያ ቅጽበት ራሴን አሰብኩ… እኔም በእውነተኛ አባቴ እጅ አላደግኩም። ግን እንክብካቤ ያየሁበት ሌላ መንገድ አለ… ፍቅር እንደሚጠፋ አልሆነም። ብቻ ግን ቅርጹ ይለዋወጣል! እና ዛሬ 1 ነገር ተማርኩ… ሰው በውድቀት ውስጥ ሀይል የሚያገኘው ከአጽናኙ ሰው አይደለም … በልቡ ከሚገኘው በዝምታ ከሚሰራው ከጌታ እንጂ.. እና በዚህ ሕይወት ውስጥ ብዙ ነገር ሊጠፋ ይችላል… ግን እምነት እና ጥንካሬ ከለ ከጌታ ጋር ይታለፋል!😊 luv you my girl🫶🏾🤌🏿🧠 #ethiopian #እግዚአብሔር #FaithOverFear #Jesus
liy📜
Region: ET
Saturday 30 May 2026 17:40:07 GMT
Music
Download
Comments
ribka birhanu :
yene ehit yemtsifiw neger lene menarya weym metsnagna new berchilign🥰🥰🥰
2026-05-30 19:57:49
3
𝕙𝕒𝕨𝕖𝕟𝕚🌸 :
ewnet new 😍🙏
2026-06-13 19:52:54
1
selina🥰 :
enem endezach guadegnash negn🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-31 13:57:30
1
t;;k :
🥰🥰🥰
2026-05-30 17:46:07
2
To see more videos from user @3in1liy, please go to the Tikwm
homepage.