@kalukal90: #ሰኔና ሰኞ ሲገጥሙ ... የሚገርመው ዘንድሮ ሰኔ ሰኞ የሚገጥመው በእኛ #በኢትዮጵያኖቹ የቀን ቀመር ብቻ ሳይሆን #በፈረንጆቹም June 01,የሚውለው በእለተ ሰኞ ነው። ነገር ግን ይህ " ሰኔና ሰኞ " ገጠመ ሲባል ታሪካዊ ዳራው ምንድ ነው? ሲገጥምስ ምን ይፈጠራል? ምንስ ተፈጥሯል ብዬ በኖርኩበት ዘመን ወደ ዃላ ተጉዤ ባስብ ባሰላስል የተፈፀመ አዲስ ነገር የለም። #በአጋጣሚ ለሚውል የቀን ግጥምጥሞሽ ለምንድነው ታዲያ፣" ሰኔና ሰኞ" ገጠመ ወይንም ሊገጥም ነው ተብሎ ቦታ ተሰቶት የሚየወራውና የሚታመነው? #እንግዲህ የዚህን የ" ታሪካዊ ዳራ ለማወቅ፣ጉልጉል ሳደረግ የሚከተለውን አነበብኩ፣ ሰኔና ሰኞ ሲገጥሙ ማለት የኢትዮጵያ አቆጣጠር የሰኔ ወር መጀመሪያ (መባቻ) ቀን ሰኞ ላይ ሲውል ማለት ነው። ይህ አገላለጽ በአማርኛ ባህል ውስጥ በሁለት መልኩ ይተረጎማል፣ 1ኛው አጋጣሚ፡ በምሳሌያዊ አነጋገር ሳናስበውና ሳይታሰብ ሁለት እጅግ አዳጋች ወይም አስቸጋሪ ነገሮች በአንድ ላይ ሲገጥሙ ለመግለጽ ይጠቅማል። 2ኛው እምነት፡ አመለካከት ሰኔ 1 ሰኞ ቀን ከዋለ ያ ዓመት ወይም ያ ወቅት እንደማይሆን፣ ችግርና አለመረጋጋት እንደሚበዛበት ተደርጎ ይፈራል። በአጠቃላይ፣ ድንገተኛ፣ አስቸጋሪ ያልተጠበቀ ክስተት ሲፈጠር እንደ ምሳሌ የሚነሳ የአማርኛ ተረት ወይም ብሂል ነው። ሰኔና ሰኞ" ምን ማለት ነው? በቀጥታ ትርጉሙ የሰኔ ወር መጀመሪያ (መባቻ) በሰኞ ቀን ሲውል ማለት ነው። ግን ሰዎች የሆነ ነገር ሲገጥማቸው " ሰኔና ሰኞ" ገጠመኝ ይላሉ በተለምዶ ልክ በኛ ሀገር ሰኔና ሰኞ ሲገጥም ሰዎች እንደ ሚሰጉት ሁሉ በሌላው ዓለም ማህበረሰብ ዘንድም ሲገጥሙ የማይወደዱ ቀንና ቁጥሮች አሉ። በምእራባውያን 13 ቁጥር የመጥፎ ገድ ምልክት ተደርጎ ይታመን ነበር። ለዚህ ማሳያው ስለ እውቁ ብራዝላዊው ተጨዋች ስለፔሌ አቶ ይድነቃቸው በፃፉት መፅሀፍ ውስጥ ስለ 13 ቁጥር መጥፎ ገድነት ተፅፏል። አነበብኩት ከሆነ በወቅቱ የብራዚል ቡድን በባለጋራው ቡድን እየተመራ እየተጫወተ ነበር። በወቅቱ ፔሌ ተጠባባቂ ነበር ያኔ ፔሌ ለሳንቶስ ክለብ ተሰላፊ ስለነበረ ለአገሩ ወክሎ የመጣው ያን ቀን ስለ ነበረ ዝናኛ አልነበረም። ያአጋጣሚ ሆኖ አንድ የብራዚል ተጫዋች ተሰብሮ ሲወጣ ፔሌ እንዲገባ ሲደረግ ፔሌ ለብሶት የነበረው የማለያ ቁጥር "13" ቁጥር ነበር። 13 ቁጥር በዚያን ግዜ የመጥፎ ገድ ምልክት ተደርጎ ይታይ ስለነበረ የቢራዝል ህዝብ ይበልጥ ተስፋ ቆረጠ። ምክንያቱም 13 ቁጥር ገደቢስ ተደርጎ ስለሚታመንበት። ግን ፔሌ በዛን ቀን ከመግባቱ ሁለት ተከታታይ ግቦችን አስቆጥሮ ብራዚል አሸንፋ እንድትወጣ በማድረጉ የ13 ቁጥር ገድ እምነት እንዲከሽፍ አደረገ። ደግሞ " ብቀላን" መፅሀፍ ከአነበባችሁ ፋቢዮ የተባለው የመፅሀፉ ዋና ተዋናይ ጓደኛውን ጉዶ ፌራራን ለመበቀል እሱኑ ጨምሮ 15 እንግዶች እራት ግብዣ ጠርቶ ነበር። ነገር ግን እራት ግብዧ ላይ የተገኙት 13 ብቻ ነበሩ። እንዳልኳችሁ በምእራባውያን 13 ቁጥር በወቅቱ የመጥፎ ገድ ምልከት ተደርጎ ይታመንበት ስለነበር ነው። ምን ለማለት ፈልጌ ነው የዚህ አይነት እምነቶች በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ይኖራል። ነገር ግን ዛሬ ነጮቹ ከዚህ አይነት እምነት ወተው በኢኮኖሚ አድገው ተገኝተዋል። ሰኔ አንድ ሰኞ ቀን ከዋለ መጥፎ ነው የሚል ምንም ሳይንሳዊም ሆነ ኃይማኖታዊ መሠረት የሌለው አጉል... እምነት መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። አንድ ዘመዴ የተወለደበት ቀንና ወር ሰኔና ሰኞ የገጠመ እለት ነበር። ይህ ሰው ታዲያ እድሉ ያማረ ከማናችንም የተሻለ ህይወት ላይ እየኖረ ይገኛል በአሁን ሰዓት። ዛሬ እኛ ኢትዮጵያኖችን ከሌላው ዓለም በእውቀትም ሆነ በእድገት ወደዃላ ያስቀረን የዚህ አይነት እምነቶች፣ተረቶች እና አጉል ትርክቶችን በማመናችንና በመከተላችን ነው። ህዝባችን ባልተጨበጡ ትርክቶችና ባህላዊ እምነቶች ታስሮ ከመስራት ይልቅ በአጉል ብሂል እያሳበበ ዘመኑን በከንቱ እያሳለፈ ይገኛል። ሁሉ የአላህ ናቸውና የሰው ልጅ ማመን ካለበት በፈጠረው ፈጣሪ እንጅ በአጓጉል እምነቶችና የቀን ገጠመኞች መሆን የለበትም እላለሁ።
user67282596597
Region: ET
Sunday 31 May 2026 04:19:05 GMT
Music
Download
Comments
የመድሀኒዓለም ፍሬ :
በትክክል ነው
2026-06-01 05:40:51
1
ፍቅር :
ማክሰኞ ነው እኮ ሰኔ አድ ።
2026-06-02 10:13:12
0
Mestawot Dabi :
እግዚአብሔር አሉ 👏👏👏
2026-06-02 11:15:23
0
ENdu807455358021 :
ውሉንም ቀን በፈጣሪ ፍቃድ ነው ሚሆነው በአባባል አይደለም
2026-05-31 19:27:49
5
TG :
ለምን ሀምሌና ሀሙስ ሲገጣጠሙስ ምን እንበል በክፉ አትዩት እንደሀሳብ ነው
2026-06-01 11:18:44
0
Firehiwot Molla833 :
good
2026-06-01 12:57:10
0
Tigisti sanoqa :
🥰
2026-05-31 07:24:08
3
Teklay ttt :
🙏🙏🙏
2026-05-31 04:54:38
1
To see more videos from user @kalukal90, please go to the Tikwm
homepage.