> ያሉት አስተውሉ ! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!🇪🇹🇪🇹🇪🇹 - @ethel369ethiopia888"/> > ያሉት አስተውሉ ! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!🇪🇹🇪🇹🇪🇹 - @ethel369ethiopia888 - Tikwm"/> > ያሉት አስተውሉ ! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!🇪🇹🇪🇹🇪🇹 - @ethel369ethiopia888"/>

@ethel369ethiopia888: "ሰኔ እና ሰኞ... አይግጠም" ሰኔ እና ሰኞ አይግጠም የሚለው የቆየ የአባቶቻችን አባባል ዘንድሮም በ 2018 ዓ.ም. በአይናችን ልናየው በትክክል ገጥሟል። ሰኔ 1 ቀን ሰኞ ይውላሎል። ከ 1979 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዛሬ... በከፊል እንይ እስኪ.. 1)1979 ዓ.ም. ( ዘመነ ማቲዎስ) በ1979 ዓ.ም. ሰኔ እና ሰኞ ሲገጥም አገሪቱ በከባድ ፈተና ውስጥ ነበረች የ1977ቱ ታላቁ ድርቅ መዘዝ እና በወቅቱ የነበረው የዝናብ እጥረት ተከስቶ ነበረ። 2) 1984 ዓ.ም.( ዘመነ ማርቆስ) በዚህ ወቅት ሰኔ እና ሰኞ በድጋሜ ገጠሙ። ህይ ዓመት የሽግግር ወቅት ቀውስ እንደነበረ የታሪክ መዛግብቶች በጥልቀት ያወሱናል። በዚህም ወቅት በመላው አገሪቱ ከፍተኛ የጸጥታ መደፍረስ ና ግጭት ነገሰ። 3) 1990 ዓ.ም. ( ዘመነ ማርቆስ) በዚህም ወቅት ሰኔ እና ሰኞ ሲገጥም በአገሪቱ ላይ ሊላ የደም ምዕራፍ ተከፈተ።በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተነሳው እጅግ አስከፊ የነበረው የባድሜ የድንበር ጦርነት በዚሁ አመት ፈነዳ። 4) 1997 ዓ.ም. ( ዘመነ ዮሐንስ) በ 1997 ላይ ደግሞ ታሪኩ ይበልጥ ልብ ሰባሪ ሆኗል።1997 ሰኔ እና ሰኞ ገጠመ። ያ ታዋቂው እና ውጥረት የበዛበት አገራዊ ምርጫ 97 የተካሄደው በዚህ ወቅት ነበር። 5) በ2007 ዓ.ም. (ዘመነ ዮሐንስ) ከ 10 ዓመታት በኋላ በ 2007 ዓ.ም. በድጋሜ በዘመነ ዮሐንስ ሰኔ እና ሰኞ ገጠሙ። 6) 2013 ዓ.ም. (ዘመነ ማርቆስ) በቅርብ ጊዜ ትውስታችን በሆነው በ 2013 ዓ.ም. ሰኔ እና ሰኞ በድጋሜ ገጠሙ። በዚህም ወቀት የጦርነት የጭንቀት የከበሮ ድምፅ የነበረ መሆኑን ሁላችንም እናስታውሳለን። የታሪክ ፍሰት አያችሁ? አሁን ደግሞ ወደ ዘንድሮ እንምጣ። ዘንድሮ 2018 ዓ.ም. ነው።አመቱም ድጋሜ ዘመነ ማርቆስ ነው! ሰኔ እና ሰኞ ገጥመዋል። እንደ 1997ቱ, እና 2007ቱ ሁሉ:ዘንድሮም ሰኔ እና ሰኞ በዘመነ ማርቆስ ላይ መውደቃቸው ታዘባቸሁ? ታሪክ እራሱን ይደግማል? ወይንስ እኛ ካለፈው ተምረን ራሳችንን እና አገራችንን እንጠብቃለን? የዘንድሮው የሰኔ እና ሰኞ ገጠመኝ ለኢትዮጵያ ወጣቶች የጥንቃቄ የማስተዋል እና የሰላም ጊዜ ይሁንልን። አባቶቻችን በምክንያት ነው << ሰኔ እና ሰኞ >> ያሉት አስተውሉ ! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ኢት-ኤል ዘ-ኢትዮጵያ🔝➌➏➒⛳️
ኢት-ኤል ዘ-ኢትዮጵያ🔝➌➏➒⛳️
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 01 June 2026 09:31:41 GMT
335076
6876
178
2391

Music

Download

Comments

mosisatiye
Mosisa Tiye :
የዘንድሮ ሰኔና ሰኞ የእድገትና የለዉጥ ዘመን ይሆናል አትጠራጠሩ ጎበዝ 🥰🥰🥰🥰
2026-06-03 08:58:14
135
senaitandualem4
ጎጃም መርዓዊ :
ግን 2012 ሰኔ ሰኞ ሁኗል
2026-06-03 08:03:39
14
enbebaykalo
ብዕድላ 😎❤️ :
🙏🥹 amen
2026-06-04 10:52:17
0
mengistu.ewnetu
Mengistu Ewnetu :
የዘንድሮ ሰኔና ሰኞ የእድገትና የለዉጥ ዘመን ይሆናል አትጠራጠሩ ጎበዝ 🥰🥰🥰🥰
2026-06-04 07:37:31
5
yamese21
yamese :
ለምን ሸኔ ና ፋኖ አንድላይ አይዉሉም🥺😁
2026-06-04 17:51:10
2
hiwi159
Hiwot zenbaba :
አሜን እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ
2026-06-03 16:19:13
5
semahegnegizer
Semu :
የትኛውም አመት ካለ ጭንቅ አላሳለፈችም ሁሌም ሰኔ እና ሰኞ ነው
2026-06-03 14:33:07
8
bilew55
ሉዕል :
እረ 2012 ውሏል
2026-06-03 14:56:58
5
miyk41
miyk :
1997 ሰኔ 1 እሮብ ቀን ነው የዋለው
2026-06-03 18:18:55
3
abdrjelil.abdo
THE GUNERRSSSS :
የምን ሟርት ነው
2026-06-04 12:31:05
1
endaluroba
My Life Is Sweet :
ምንድነው አልገባኝም
2026-06-04 17:43:36
1
.yilie
Habesha :
ሟርተኛ
2026-06-03 17:12:04
1
zerhiun1
zerhiun :
ስኔ እና ስንዴ
2026-06-02 04:51:13
7
user3425485906844
👉ልኑር በተስፋ💚💛❤️🇪🇹😏 :
ሰኔ እና ሰኞ ከገጠመ ወበከቱ ነው
2026-06-03 13:32:13
3
antex89223
ante :
first please ck the dates before doing such posts
2026-06-04 14:06:22
0
sura.53367
💞surafel Getu💞 :
2013 ሰኔ 7 ነበር ሰኞ
2026-06-03 16:50:12
1
user292308294850
user292308294850 :
በየ አምስት አመት ነው ሰኔና ሰኞ የሚገጥም
2026-06-03 18:18:14
2
melakhailu7
መልዓክ🌹🥀 :
🥰🥰🥰 ግሩም ነው
2026-06-03 19:12:09
1
yebnahu8
Yebnahu :
ሰኔ 1 2013 ማክሰኞ ቀን ነው የዋለው ሰኔ 1 1997 ዕረቡ ቀን ነው የዋለው ሰኔ 1 1977 ቅዳሜ ቀን ነው የዋለው
2026-06-03 18:01:06
5
h.m346515
ዕፀ -መለኮት በ ዕፀ -መግስት :
ዘንድሮዘመንዮሐንስ ነው እንዴ
2026-06-02 20:02:16
1
mnalbat4
ኣንድ ቀን :
ፈጣሪ ራሱ ሰላም ያረግልናል🙏🙏🙏🙏
2026-06-03 18:01:30
2
user53801428115615
ከተፃፈ አይቀርም :
አሁን ደግሞ እሁድ ነው 30 የሚሆነው
2026-06-03 15:27:51
0
dukeasde12
mesfin A :
ዳግማዊ 2012 ሆነ
2026-06-03 16:34:04
1
yetefa21
shigult yetefa :
መድሃኒያለም አለ የኛ ጌታ 🙏🙏🙏
2026-06-03 17:59:15
1
abel.tapiseri
Abel tapiseri :
በጣም የሚያስፈራ ይመስላል
2026-06-03 12:46:11
1
To see more videos from user @ethel369ethiopia888, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About