@sarwitegetagiram: #ፆመ_ሐዋርያት #እንኳን_አደረሳችሁ ቴሌግራም ፔጅ👇 https://t.me/MoaeTewahedoB 💦ሐዋርያት ፆም ቅድስት ቤተክርስቲያን በአዋጅ ከምትፆማቸው ሰባት አፅዋማት አንዱ እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ ክርስቲያን ቢፆመው እጅግ በርካታ በረከቶችን ያገኝበታል ከነዚህም ጥቂቶችን እነሆ፣ 💦፩.በረከተ ሐዋርያት ይገኝበታል 💦ይህን ፆም መጀመርያ ፆመው እንድንፆመው ሰርዐት የሰሩልን ሐዋርያት ናቸዉ ስለዚህም ፆሙ መታሰቢያነቱ የሐዋርያት ነው የጻድቅ መታሰቢያ ደግሞ ለበረከት ነው ። ምሳ.10፥7 እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም የሐዋርያቱን በረከት እናገኛለን ሐዋ.13፥1-3 ሐዋ.14፥23 💦፪. በስራችንና በአገልግሎታችን በረከት እናገኛለን 💦ሐዋርያት ይህን ፆም የፆሙት አገልግሎታቸው እንዲከናወንላቸው እንዲባረክላቸው ነው ነብዩ ነህምያም እየሩሳሌምን የመስራት ተግባሩ እንዲባረክለት በፆመው ፆም ስራው ሁሉ ተባርኮለታል። ነህም.1፥4። እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም በዕለት ተዕለት ተግባራችን በረከት እናገኛለን። 💦፫. ዝናብ ምህረትን ጠለ በረከትን እናገኛለን 💦የሰኔ ፆም በአገራችን የክረምቱ መግቢያ ላይ የሚፆም ፆም ነው ይህም መጪው የክረምቱ ወራት የተስተካከለ የምህረት ዝናም እንዲኖረው ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል ዘመን ዝናብ ጠፍቶ ዛፎቹ ሳይቀር በደረቁ ጊዜ በፆም በፀሎት ወደ እግዚአብሔር በተማፀኑ ሰዓት ዝናመ በረከትን አግኝተዋል። ኢዩ.1፥13-14 💦፬. በረከተ ምርትን እናገኛለን 💦የሰኔ ፆም በሃገራችን ገበሬው ዘር መዝራት በሚጀምርበት ጊዜ የሚፆም ፆም ነው ሰለዚህም በዚህ ሰዓት የሚፆመው ፆም ዘርን እንዲባረክ በረከት እንዲበዛ ያደርጋል ይህም አገር ወገን ከረሃብ ከችግር ነፃ እንዲወጣ ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል እንደተገለጸው በፆም የዕህል የመጠጥ በረከት ይገኛል ። ኢዩ.2፥12-14 💦፭. የነፍስ በረከትን እናገኛለን 💦ፆም በመንፈስ የደከመች የዛለች ነፍስን ያበረታል የነፍስን ቁስል ይፈውሳል ስጋዊ ኃይልን ያደክማል የሥጋን ፈቃድ ለነፍስ ያስገዛል መዝ.108፥24 ፤ ገላ.5፥24 የዓለምን ሃሳብ ያስወግዳል ከእግዚአብሔር ያስታርቃል ማቴ. 17፥21 ሚስጥር ይገልጣል ዘስ.34፥27-28 ፤ ዳን. 10፥1-3 "በአምላካችን ፊት እራሳችንን እናዋርድ ዘንድ ከርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ ...... ፆምን አውጃለሁ " መጽሐፈ ዕዝራ.8፥21 ከመዋዕለ ፆሙ ረድኤት በረከት ያሳትፈን 💦ፆሙን የኃጢአት መደምሰሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን አሜን። 💦አምላከ ቅዱሳን ቅድስት አገራችን ትንሳኤዋን ያቅርብልን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን #capcut #creatorsearchinsights #1millionviews
@sarwite Geta Giram የተዋህዶ ልጆ
Region: BH
Monday 01 June 2026 10:05:30 GMT
Music
Download
Comments
እግዚሃብሄር ብርሃኔና መድሃኒቴ ነው🙏🙏🙏🙏 :
አሜን አሜን አሜንንንንንን
2026-06-01 10:25:44
1
ገብረኤል አባቴ :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-02 16:23:54
0
🆑1️⃣9️⃣ :
🥰🥰🥰
2026-06-01 16:40:39
0
Obsee Orth ²¹ 💒🙇♀️❤️🥷 :
🥰🥰🥰🥰🥰❤️❤️❤️
2026-06-01 15:42:31
0
ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር✨️ :
🙏🙏🙏
2026-06-01 11:52:39
0
ነገም ሌላ ቀን ነዉ🌹😘 :
🙏🙏🙏
2026-06-01 11:10:48
1
To see more videos from user @sarwitegetagiram, please go to the Tikwm
homepage.