@hahu.digitals: ለገንዘብ ነፃነት የሚያበቁ 10 ቁልፍ መርሆችን ልንገርህ ወደ ስኬት የሚመሩህ  10 መርሆች 1.       ወጭህን ተቆጣጠር  (Live Below Your Means) ሀብታም መሆን ማለት ብዙ ማግኘት ማለት አይደለም—ከምታገኘው ያነሰ ማውጣት ማለት ነው። በ20ዎቹ ዕድሜህ ውስጥ የኑሮ ዘይቤህንና ወጪህን ካልተቆጣጠርክ፣ በ50ዎቹ ዕድሜህም መታገልህ አይቀሬ ነው። 2.      አንድ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ  ክህሎትን ጠንቅቀህ ዕወቅ (Master One High-Income Skill) ኮዲንግ (ፕሮግራሚንግ)፣ የሽያጭ ክህሎት፣ ስክሪፕት መጻፍ፣ ግራፊክ ዲዛይን ፤ ፐብሊክ ስፒች፤ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ክህሎት መርጠህ አበልጽገው። ከፍተኛ ገቢ የሚያስገቡ ክህሎቶች ከእጅ ወደ አፍ ከሆነ የኑሮ ሁኔታ ለመውጣት ቁልፍ ናቸው። 3.      በገቢ ላይ ብቻ ሳይሆን በሀብት/ንብረት ማፍራት ላይ አተኩር (Focus on Assets, Not Just Income) አንተ በቦታው ብትኖርም ባትኖርም ገንዘብህ እንዲሠራልክ በአክሲዮን፣ በሪል እስቴት ወይም በዲጂታል ምርቶች ላይ ኢንቨስት አድርግ። 4.      በርካታ የገቢ አማራጮችን ፍጠር (Create Multiple Income Streams) በአንድ ገቢ ላይ ብቻ መደገፍ  የለብህም። ትንሽም ብትሆን በትርፍ ሰዓትህ የምትሰራው ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ይኑርህ፡፡ በፋይናንስ ረገድ ጠንካራ ለመሆን የገቢ ምንጮችህን በሥራ፣ በትርፍ ሥራ (side hustle) ወይም በኢንቨስትመንት አማካኝነት ማብዛት አለብህ። 5.      መጥፎ ዕዳን/ብድርን  አስወግድ/ (Avoid Bad Debt) ለአላስፈላጊ የቅንጦት ዕቃዎችን ለመግዛት ብለህ መበደርህን አቁም፡፡ ብድርን ለይስሙላ  ሳይሆን ሀብት ለመገንባት በስትራቴጂ ተጠቀምበት። 6.      እንዴት መሸጥ እንዳለብህ መማር (Learn How to Sell) በአለማችን ላይ ያሉ ባለሃብቶች አብዛኛዎቹ ሲጀምሩ የሽያጭ ሰራተኞች ነበሩ፡፡የሽያጭ ክህሎት ለማንኛውም ሰው የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ልብ በል በአለም ላይ ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሱ ሰዎች ቁልፍ ምስጢር ሰዎችን አሳምነው ሞያቸውን ወይም የያዙትን ምርት መሸጥ መቻላቸው ነው፡፡  ገንዘብ የሚፈሰው ማሳመንና ተጽዕኖ መፍጠር ወደሚችሉ ሰዎች  ነው። ምርትን፣ አገልግሎትን ወይም ራስህን እየሸጥክ ቢሆንም፣ የሽያጭ ጥበብን ማወቅ በሕይወት ለመቀጠል ወሳኝ ነው። 7.      የኢንተርኔት ተደራሽነትን መገንባት (Build an Online Presence) ኢንተርኔት የመጨረሻው ትልቅ ሀብት ማፍሪያ መሣሪያ ነው። የፈለገ ግዙፍ ድርጅት ቢኖርህ ፤ የፈለገ ተፈላጊ ምርት ቢኖርህ በኢንተርነት ተደራሽ ካላደረከው እመነኝ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ከገበያ ውጭ ትሆናለህ፡፡ካለህበት አካላዊ ቦታ አልፈህ ሰፊ  ደራሽነት ለመፍጠር ብሎግ፣ የዩቲዩብ ቻናል ወይም የኢ-ኮሜርስ መደብር ጀምር። 8.      ዙሪያህን እድገት በሚፈልጉ ሰዎችና በስኬታማ ሰዎች  ክበበው (Surround Yourself with Growth-Oriented and successful People) በማኅበራዊ ሕይወትህ ዙሪያ ያሉ ጓደኞችህ ሊያደናቅፉህ አልያም ወደ ፊት ሊያራምዱህ ይችላሉ። ጊዜህን በሐሜትና ባለህበት መርገጥ ላይ ሳይሆን፣ በዕድገትና በስኬት ላይ ካተኮሩ ሰዎች ጋር አሳልፍ። በዙሪያህ ስኬታማ ሰዎችን ደርድራቸው፡፡እነሱን በማየት ብቻ ለስኬትህ መንገድ ትከፍታለህና፡፡ 9.      ጊዜህን ተቆጣጠር (Take Control of Your Time) ጊዜን በገንዘብ መለወጥ የገቢ አቅምህን ይገድበዋል። ሀብታም ሰዎች ጊዜያቸውን ነፃ የሚያደርጉላቸውን ሥርዓቶች (systems) ይዘረጋሉ ወይም ኢንቨስትመንቶችን ያደርጋሉ።ውድ ጊዜህን ለማይረባ ጥቅም አታባክን፡፡ለዚያ ነው ተቀጣሪ መሆን ማለት ለጊዜ እና ለአሰሪ ባሪያ መሆን ነው የሚባለው፡፡ 10.  ሳታቋርጥ ተማር (Keep Learning) በዕውቀት ማደግህን በፍጹም አታቋርጥ። መጻሕፍትን በማንበብ፣ ገበያዎችን በማጥናትና አዳዲስ ክህሎቶችን በመቅሰም የማወቅ ጉጉትህ አይጥፋ። ቀጣይነት ያለው ትምህርት ሁልጊዜ ከሌሎች ቀድመህ እንድትገኝ ያደርግሃል። ትኩረትን ለ1 ሰከንድ እንኳ መቆጣጠር በማይቻልበት ጊዜ  ይህን ጽሁፍ ትኩረት ሰጥተህና ተረጋግተህ በማንበብህ ለስኬት ያለህን ቁርጠኝነት ያሳያልና ግብህን እስከ ምታሳካው በርታ ወንድሜ፡፡     አመሰግናለሁ፡፡

Hahu Digitals
Hahu Digitals
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 01 June 2026 13:14:53 GMT
19220
745
31
159

Music

Download

Comments

joz6117
life furniture :
thanks
2026-07-26 18:26:13
1
ayiu_media
AYIU MEDIA :
keep it up!
2026-07-24 19:30:38
1
hailu.gebreyesus27gmail
Hailu Gebreyesus :
waw amazing idea💡 💡 💡
2026-07-18 17:28:09
1
alex.manebo
Alex Manebo :
thanks
2026-06-01 16:50:23
2
eneyew.hope
Eneyew dema hope :
thanks🙏
2026-07-18 12:50:59
1
www.tiktok.comyamitibeb
Yami Tibeb/ያሚ ጥበብ :
Amesegnalew i need more
2026-06-01 13:27:21
2
solomonayele24
3SHM :
አመሰግናለው ተምሬበታለው
2026-06-07 17:08:18
1
asf.gss
Alelign Sitotaw :
yes
2026-06-08 08:01:21
1
gadisa.ar
Gadisa Ar :
ፈጣሪ ይባርክህ 🙏🙏🙏🙏
2026-07-21 16:04:07
1
tarekegnbirega
tarekegnbirega :
አመሰግናልሁ
2026-06-19 11:01:05
1
.dawa.best
dawa best :
ameseginalew
2026-06-22 19:09:55
1
user7460053037543sh
የማይመለስ ግዜን እንጅ የማያልፍ ቀን የለም :
አመሰገናለሁ
2026-07-08 14:41:13
1
mengedegnawu8
መንገደኛዉ 1221 :
አመሰግናለሁ
2026-07-01 06:31:44
1
ketse75
Ketse :
thanks
2026-06-01 14:10:36
1
johnman382
Jo ❤ :
wow bexam temechitognal indayiquarexu🙏
2026-06-01 14:41:54
1
user9742327752057
Habtamu 🥀💚💛❤️🇨🇬 :
እናመሰግናለን በጣም ለአንተም ይጨመርልህ ትምህርትህ አስተማሪ ነው
2026-07-15 17:17:15
1
awtachew
Awtachew :
ኣመሰግናለው👍👍👍
2026-06-01 20:38:35
1
abiyeabuhay
ወንቅሸት ገብርኤል19 21 :
Thanks
2026-06-01 15:05:58
1
tat52472
Tat :
thanks
2026-06-01 14:41:06
1
mesfinmaru_official
Mesfin Maru178 Official :
እናመስግናለን🥰🥰🥰🥰
2026-07-27 13:22:25
0
gadisa.ar
Gadisa Ar :
🥰🥰🥰
2026-07-21 16:04:14
1
sitotaw.asefa
Sitotaw Asefa :
🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-28 07:22:18
1
bironaka4
Not Yet :
🥰🥰🥰
2026-06-13 10:24:43
1
mr_yo95
mr ዮ :
🔥🙏
2026-06-13 09:24:43
1
hintsa22
hintsa🖤🖤 :
🥰🥰🥰
2026-06-01 13:29:24
0
To see more videos from user @hahu.digitals, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About