@bersiqhcfia: 💒✝️ቅድስ ክርስቶስ ሰምራ✝️💒 💒ወር በገባ በ24 የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ትታሰባለች። ✝️ በክርስቶስ ፍቅር ተስባ ገዳማዊ ሕይወትን የመራች፣ በበዓቷም የጸናች ቅድስት እናት ። ዓለምን ንቃ ለማያልፈው ሰማያዊ የዘለዓለም መንግሥት በጸሎት፣ በቅድስና የኖረች እናት! ✝️ምንኩስናዋን እስከ ዕረፍቷ ድረስ ጠብቃ እግዚአብሔርን አክብራ ኖረች ። ✝️የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ተዐምር✝️ ✝️እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ያደረገኝው ታአምር ይህ ነው ። የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ የጸሎቷ በረከት ከመላው ህዝበ ክርስቲያኑ ጋር አድሮ እና ጸንቶ ይኑር። በሸዋ ክፍለ ሀገር የሚኖር ጥበበኛ ወይም ዐዋቂ የሆነ የንጉሥ ጭፍራ ወይም ወታደር ነበር ሰውየው መካን ነበረና ልጅ ባለመውለዳቸው ከሚስቱ ጋር ለብዙ ጊዜ ሲያዝኑ ኖሩ፡፡ ከዕለታት በአንደኛው ቀን በጥቡዕ ልቡና በፍጽም መታመን በእናታች በቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ሥዕል ፊት በብዙ ለቅሶ ልጅ ብንወልድ ለቤተክርስቲያን የሐር መጋረጃና የወርቅ ጃንጥላ መብዓ እናቀርባለን ሲሉ ብፅዓት አደረጉ፡፡ እንዲህም ብለው የሎሚ ወይም የለውዝ ፍሬና ከቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ዐፈር ወይም እምነት ይዘው ወይም ወስደው ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወይም ጊዜ በኃላ የዚያ ሰው ሚስት ፀነሰች። ወንድ ልጅም ወለደችና ታላቅ ደስታ አደረጉት። እግዚአብሔር አመሰገኑ። እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን አከበሯት ከፍ ከፍም አደረጓት፡፡ አስቀድመው ስለተሳሉት መብዓ የወርቅ ጃንጥላ የቤተ መቅደስ መጋራጃ ለእናታችን ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቤተክርስቲያን አምጥተው ሰጡ፡፡ከዚያም ከአበ ምኔቱ ወይም ከገዳሙ አስተዳደር ከአባ ዘመንፈስ ቅዱስ ቡራኬና ታላቅ በረከት ተቀብለው እግዚአብሔንና እናታችን ክርስቶስ ሠምራን እያመሰገኑ በሰላም በታላቅ ደስታ ወደቤታቸው ሄዱ፡፡ ✝️የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ፀሎቷ በረከቷ እና አማላጅነቷ ከሁላችን ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን🙏 ምንጭ፦ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ

የእመብርሃን ፀጋ
የእመብርሃን ፀጋ
Open In TikTok:
Region: NL
Monday 01 June 2026 16:25:05 GMT
3669
475
8
80

Music

Download

Comments

m.negni94656
M💝💝 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-10 07:36:56
0
getu.ta3
Getu Ta :
🙏🙏🙏
2026-06-02 07:31:30
1
seratigabu
seratigabutiktok.com/@seratiga :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-07 06:28:11
0
dn.jalata.shifara
Dn Jalata shifara :
🥰🥰🥰
2026-06-01 17:11:09
1
saddmunrtii.abdoo
abshaa daraa :
🙏🙏🙏
2026-06-03 05:31:43
1
To see more videos from user @bersiqhcfia, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About